Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, January 4, 2018

የተጠማ ሰዉ ጥሩ ዉኃ ለማገኝት ማመን ያለበት ምንጩን ወይስ ቱቦዉን? (ሙላት በላይ)











ወያኔች ሥልጣን እነደያዙ የጦር መሣሪያወችን ወደማረሻ እንለዉጠዋለን በአሉ በአጭር ጊዜ የነበረዉን የጦር መሣሪያ አጠናክረዉ ከ70ሺህ በላይ ህዝብ መጨረሳቸዉን፤ ማንኛዉም ኢትዮጵዊ በኢትዮጵያ ተዘዋዉሮ ሰርቶ መኖር ይችላል በአሉ በአጭርጊዜ አማራዉን ከየአለበት አገርህ ከልል ሦስት ነዉ ብሎ ማባረራቸዉን፤

ነፃ ፍርድ ቤት በለዉ ሰይመዉ በደህንነት ዉሳኔ ህዝብን እያሰሩ ማሰቃየታቸዉን፤ ማንም ሰዉ ሳይመሰከርበት አይያዝም ያለፍርድም አይታሰርም ብለዉ ያለምንም ጥፋት እና ያለፍርድ ከአሥር አመታት በላይ አስረዉ ጥፋተኛ እደለህም ብለዉ መልቀቃቸዉን፤ እያየንና እየሰማን

በአጠቃላይ ወያኔዎች በወሸት ተወልዶዉ በዉሸት አድጎዉ በዉሸት ነገሰዉ ለ27 አመታት አገር ከፋፍለዉ ነገድን ከነገድ እያጣሉ ተፋቅሮና ተባብሮ ተረጋግቶ በየሥራ መስኩሠርቶ እንዳይኖር በማድረግ ሕዝቡን በድህነት አዘቅት ከተዉ እራሳቸዉን አበልጽገዉእኖሩ መሆናቸዉን፤

እራሳቸዉን የትግራይ ነፃአዉጭ ብለዉ ሰይመዉ አንድም ቀን የኢትየጵያ መንግሥት ነን ሳይሉ እኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ብለን በየአደባባዩ ስለጨሁንላቸዉ ብቻ በእኛ እሳቤ እንደመንግሥት እንደሚሠሩ ማመናችን እከአሁን በህዝብላይ እነደፈነጩ አደረግን ፡፡ አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ በነሱ በኩል የሚፈጸመዉ ሁሉ ነገር መሮት አመጽ ሲያካሂድ እና ወያኔወች ከሞት አፋፍ ላይ ሲደርሱ ከነሱ በስተጀርባ ተሰልፈዉ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከሚዶልቱት አማካሪዎቻቸዉ በሚለገሳችዉ የጥገና ዘይቤ የዉም ለማይቀበሉት የፖለቲካ እስረኞችን እንፈታልን የሚል የህዘብ አመጽ ማብረጃ ዘዴ ሲፈጥሩ እነሱ የህዝብ አመጽ አንድ ጊዜ መብረድ ከጀመረ እንደገና ለማገርሸት ጊዜና ቀስቃሽ እንደሚፈልግ በዚህ ክፍተት የሚፈራዉን በማሰፈራራት የሚጋፈጠዉን እየሰሩበት በመጡበት የአገዳደል ዘዴ በጓደኛ በሴት ወዳጅ፣ በሆቴል ቤት ሰራተኛ፣ ወዘተ በኩል ምግብን መርዞ በማብልትእና በህክምና በመረፌ በመስጠት ካለተቻለም በድብቅ በደህንንት በማስገደል የሕዝብን አመጽ ለማኮላሸት አስበዉ ሲነሱ የተቃዋሚ ድርጅት ነኝ ባይወች አከቲቪስቶች እና አጃቢወቻቸዉ ምንድን ነዉ? የሚያወሩት ለመሆኑ የፖለቲካ እስረኞች እነማን ናቸዉ? በማንስ ትርጓሜ እሰረኞችስ በቁጥር የሚታወቁ ናቸዉን?

አቶ ስብሀት የኢትየጵያ ህዝብ ወደድክም ጠላህም በኛ ትገዛለህ እቢ ካለክም ትታሰራለህ ምነአለባት እሥርቤት ቢጠብ ባትታሰርም የቁምእስረኛ ነህ ያለዉን ሰናሰታዉስ እስረኛዉ እነከሌ ተብለዉ የሚዘረዘሩ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵዊ ነዉ፡፡ የትግሉም ዓላማ በዉስጥም በዉጭም የታሰረዉን ኢትየጵያዊ ሁሉ ለማስፈታት ሞሆኑን አንዘንጋ፡፡ አሱ በቻ አይደለም እየታገልን ያለነዉ ለታሰረዉ ለአሁኑእስረኛብቻ ሳይሆን ለተተኪዉም ተዉልድ ነዉ፡፡ በምሆኑም የምንታገለዉ ለመታሰር ምክያት የሆነዉንና እና ባለቤቱን ለእንድ ጊዜ ና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት መሆኑን አንዘንጋ፡፡

አቶኃይለማርያም ደሳለኝ የሚያቀርቡትን ሀሳብ በእወነተኛነትና በቋሚነት እንዴት አምኖ መቀበል ይቻላል ምክንያቱም እሳቸዉ የሚነግሩን እራሳቸዉ አመንጭተዉ ሳይሆን ከሌላ ወይም ከወያኔዉ ቁንጮወች የሚመነጨዉን ለማሰትላለፍ እንደ ቧንቧነት አገልግለዉ ነዉ ፡፡ በመሆኑም ወያኔወች ሰያደፈርሱት በአቶ ኃይለማርያም በኩል የምናገኘዉ ያለምንም ጥርጥር ድፍርስ ስለሚሆን ነዉ፡፡ ስለዚህ የወያኔወች አቋምኢትዮጵያን አጥፍቶ ትግራይን ማልማት በቻ መሆኑን አዉቀን የሕዝቡን ዐመፅ በማጠናክር ተባብረን እንስራ፡፡ ቀስቅሳቸዉ

No comments:

Post a Comment

wanted officials