Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 15, 2018

የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ለህወሃት አስደንጋጭ ሆኗል ተባለ



ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚላኩ የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦን በተመለከተ በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ይፋዊ ምላሽ መስጠቱ ሁኔታው ያስደነገጠው መሆኑን እንደሚያሳይ የዘመቻው አስተባባሪ ገለጸ።
አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የውጭ ምንዛሪ እቀባ ዘመቻው ዋነኛ አላማ የሕወሃትን አገዛዝ በማዳከም የኢኮኖሚና የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ መክተት ነው።
የአገዛዙ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ለእርሳስና ለእስክሪብቶ የሚውል ነው በማለት ማናናቁን ምላሽ መስጠቱ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ያመላክታል ብሏል ግብረሃይሉ።
አለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይልኩ እያስተባበረ ይገኛል።
ይህም ዘመቻ አላማው የአገዛዙን እድሜ በማሳጠር የሕዝብን መከራ ለማስቆም መሆኑን ነው የሚገልጸው።
እናም ዘመዶቻቸውን ለመርዳት፣ለንግድና ለግንባታ ወደ ሀገር ቤት የሚልኩትን የውጭ ምንዛሪ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን እንዲያቆሙ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል።
እንደ ግብረሃይሉ ገለጻ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚልኩት ምንዛሪ በተዘዋዋሪ መገድ ለሕወሃት አገዛዝ የአፈና መሳሪያ መግዣ የሚውል ነው።
ግብረሃይሉ ይህንኑ አስመልክቶም አዲስና የተጠናከረ የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ዘመቻ ጀምሯል።
ጉዳዩ ያሳሰበው የሕወሃት አገዛዝ ግን ዘመቻውን በማቃለል ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ለእርሳስና ለእስክሪቢቶ ብቻ የሚውል ነው ሲል አጣጥሎታል።
የሕወሃት አገዛዝ በውጭ ጉዳይ ቃለቀባዩ በኩል ዘመቻውን ለመጣጣል ቢሞክርም አለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል ግን ምላሹ አገዛዙን እንዳበሳጨው ያሳያል ሲል መግለጫ አውጥቷል።
እንደ ግብረሃይሉ ገለጻ በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ለዘመቻው ይፋዊ ምላሽ መስጠቱ ሁኔታው ያስደነገጠው መሆኑን ያመላክታል ነው ያለው።
እናም ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይበልጥ ሃይላቸውን በማስተባበር የውጭ ምንዛሪ እቀባውን እንዲያጠናክሩ አለምአቀፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሃይል ጥሪውን አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials