Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, January 29, 2018

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀመሩ! ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ተቀስቅሷል!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀመሩ!
ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ተቀስቅሷል!
ልዩ ሃይል/አጋዚ ጋር ግብግብ ገጥሟል!
ጥር 22 2010
ዛሬ ማክሰኞ ጥር 22 የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በወልድያ፣ ቆቦ፣ መርሳና ሌሎች ከተሞች ላይ ወያኔ እየፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ ነው። ወያኔ ሌባ ነው! የሚል ሞፈክር ጮክ ብለው እያሰሙ ነው። የተማሪው ተቃውሞ ዛሬ ከጧቱ 6:30 ጀምሮ በቴዎድሮስ ካምፓስ ነው የጀመረው። ተማሪዎቹን ለማፈን ከሚሞክሩ አጋዚዎች ጋር ግብግብ እንዳለና ተማሪው ባለው አቅሙ እራሱን ለመከላከል እየሞከሩ መሆኑ ተናግሯል። በተመሳሳይ መልኩ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞውን ትናንት መጀመራቸው ታውቋል። በትናንትናው ዘገባችን እንደተገለፀው እሁድ እለት ደግሞ በጎንደር ስታድየም ህዝቡ ለወልድያ ያለውን አጋርነት አረጋግጦ በወያኔ ላይ ደግሞ ቁጣውን አሰምቷል።
ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተልነው ነው።
AsnakewAbebe
Image may contain: one or more people

No comments:

Post a Comment

wanted officials