የኢሕ አዴግ ድርጅቶች አዲስ መግለጫቸውን መስጠት ተከትሎ በዓማራ ክልል የሚገኘው የፌዴራል ጦርና ፖሊስ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ መታዘዛቸውን የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ብሎ ራሱን የሚጠራው የኢሕ አዴግ ድርጅት ውስጥ የሚገኙ ምንጮች አስታውቀዋል። ምንሊክ ሳልሳዊ በዚህም መሰረት ተጨማሪ መሳሪያዎች እና የደህንነት ሓይሎች እንዲጨመሩ ተብሏል። በባህር ዳር ጎንደርና ደሴ በተለየ መልኩ ጥበቃዎችና የደህንነት ክትትሎች እንዲደረጉ ታዟል።
አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ምንሊክ ሳልሳዊ የፖለቲካ አስረኞችን እፈታለሁ ያለው የኢሕአዴግ አገዛዝ አስክንድር ነጋ ። አንዱአለም አራጌ ፣ አንዳርጋቸው ጽጌን ፣ ኮሎኔል ደመቀን ጨምሮ አማራ የሆኑ እስረኞች ላለመፍታት እያንገራገረ መሆኑ የፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ቢሮ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ይናገራሉ። ለፕሬዝዳንቱ ቢሮ የቀረበው የስም ዝርዝር ውስጥ ከላይ ስማቸው የተዘረዘረው ታሳሪዎች የሌሉ ሲሆን ተስተካክሎ እንዲመጣ ወደ ማረሚያ ቤቱ የስም ዝርዝሩ መመለሱ ታውቋል።
ጥቂት በሚል በቁጥር የተወሰኑ እስረኞችን ፈትቶ የሕዝብን አመጽ ለማረጋጋት ጊዜ ለመግዛት ይጠቀምበታል የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ ።
Minilik Salsawi
No comments:
Post a Comment