Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 10, 2018

በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ተፈረደ ፡ እናም ቀጣዩ ህዝባዊው ትግል መቀጣጠል ብቻ ነው ህዝባችንን ነጻ የሚያወጠው!

በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ተፈረደ ፡ እናም ቀጣዩ ህዝባዊው ትግል መቀጣጠል ብቻ ነው ህዝባችንን ነጻ የሚያወጠው!
[ወንድወሰን ተክሉ]
የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋትና በሀገሪቷ ውስጥ የተነሳውን አመጽን እንፈታለን የሚለውን ዲስኩር ባሰማን 9ኟ ቀኑ ላይ አንድም እስረኟን ሳይፈታ በአንጻሩም የኦፌኮ አመራር አባላት የሆኑትን አቶ በቀለ ገርባን እና ሶስት ተከሳሾችን የክስ ጉዳይ ላይ ሀሙስ በዋለው ችሎት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አላስፈላጊ ናቸው በማለት ውድቅ ካደረገባቸው በሃላ በችሎት መድፈር ብሎ የስድስት ወር እስር እንደፈረደባቸው ማወቅ ተችላል፡፡
ለእነ አቶ በቀለ በችሎት መድፈር 6 ወር ያስፈረደባቸው ተከሳሾቹ ለመከላከያ ምስክርነት የጠቆማቸው አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፡አቶ ለማ መገርሳ፡አቶ አባዱላ ገመዳን ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው ጠይቀው ቴፍርድ ቤቱ ውድቅ ሲያደርግባቸው ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ነው ተብላል፡
እነ አቶ በቀለ እና ባልደረቦቻቸው በችሎቱ የትግል ዘፈን በማዜም ተቃውሞዋቸውን በድፍረት ገልጸዋ፡
በችሎት የነበሩና በአግ7 አባልነት የተከሰሱ እስረኞች ደግፈው በማጨብጨባቸው በችሎት መድፈር የ 3 ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል፡
በችሎት የነበሩ የእስረኞቹ ቤተሰቦች፡ደጋፊዎችና ባለጉዳዮች ሁሉ በእስረኞቹ ሁኔታ ልባቸው ተነክቶ ማልቀሳቸው ተገልጻል፡
የህወሃት ባለስልጣናት ዳንኪራ ከመቀሌ እያሳዩን ነው፡ የእኟን ወገኖች ሲያላቅሱ እያየን ነው፡
ይህ ስርዓት በሰዎች ስቃይ የሚደሰት ናዚና አሪዮስ ነው፡
ትግላችንን በማጠናከር በይበልጥ ማቀጣጠልና ማስጨነቅ አለብን፡
ህወሃት አይፈታም፡ ካልተጨነቀ የነጠቀንን መልሶ አይሰጥም፡ ወገኖቻችን እነ አቶ በቀለ ገርባ ግደሉን በማለት በግልጽ ተጋፍጠዋል፡ ማስተጋባት አለብን:

No comments:

Post a Comment

wanted officials