Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, March 24, 2018

በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሶ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት መሆኑን ገለጸ።


🔶 ከግብረሰዶማዊያን እና ከአህምሮ እመምተኞች ጋር ከአንድ አመት በላይ አንድ ላይ አንድታሰር ተደርጌአለሁ...
🔷 በደረሰብኝ ኢ-ሰባዊ ድርጊት ኩላሊቴ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም...
🔶ከወልቃይት መሬት እና ማንነት ጋር በተያያዘ አሁንም በማረሚያ ቤት ሀላፌዎች ድብደባ እየደረሰብኝ ነው...
ይህ ከላይ የምትመለከቱት ድምፅ ከግንቦት 7 ጋር በተገናኘ በሽብር ፈጠራ ወንጀል ተከሶ 7 አመት ተፈርዶበት አ/አ ማረሚያ ቤት ቃሊቲ የሚገኘው የአበበ ካሴ የስቃይ ድምፅ ነው።
ከ2006 ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ በቃሊቲ ማ /ቤት ከፍተኛ ስቃይና ድብደባ እንደደረሰበት ተናገረ። ከዝዋይ ማ/ቤት ወደ ቃሊቲ ከተዛወረ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ከፖለቲካ አመለካከቱ ጋ በተያያዘ ከፍተኛ የማረሚያ ቤቱ አመራሮች ማለትም ሱፐር ገብረ ህይወት÷ ኦፌሰር መካሻ÷ ኦፌሰር ጥላሁን ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውብኛል። ስነ ልቦና እና አካላዊ ጉዳት እንዲደርስብኝ ግበረ ሰዶማዊያን እና የአህምሮ ህመምተኞች ለብቻቸው ከሚተሰሩበት ማቆያ አሰረውኛል። ከወልቃይት መሬት እና ማንነት ጋር በተያያዘ እዚህ ሆነህ ወጣቶች እንዲደራጁ ÷ እንዲያምፁ÷ በመሬቱ ጉዳይ ምንም አይነት የሚዛንፍ አቋም ህዝቡ እንዳይኖረው መልህክት አስተላልፈሀል እያሉ ደብድበውኛል። በዚህም ድብደባ ኩላሊቴ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ሽንቴንም መቆጣጠር አልችልም ብሏል።(የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ አንደተመለከተው አበበ ከፍተኛ የሆነ የወገብ ህመም እና ድካም ሲታይበት ተመልክቷል) ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላ የማያውቀው ክስ ተከሶ 20 አመት ተፋርዶበት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍ/ቤት ቅጣቱ ተፈፃሚ እነዲሆን ትህዛዝ ለቃሊቲ ማ/ቤት መሰጠቱን አበበ ገልጿል። አበበ ማህከላዊ ወንጀል ምርመራ በደረሰበት ድብደባ እና ስቃይ የእግሩ እና የእጁ ጥፍሮቹ ሙሉ በሙሉ መነቀላቸው አና ብልቱ መኮላሸቱ ይታወቃል።
ፍትህ ለአበበ ካሴ.......
Bildergebnis für አበበ ካሴ

No comments:

Post a Comment

wanted officials