Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, March 11, 2018

የአጋዚ ጦር በሞያሌ ቦረና ንጹኃንን ጨፈጨፈ

በህወሓት የሚመራው የአጋዚ ጦር በሞያሌ ቦረና ጭፍጨፋ መፈጸሙ ታወቀ”” ጦሩ በዛሬው ዕለት በፈጸመው አስከፊ ጭፍጨፋ 13 የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል”” እንደዚሁም በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መቁሰላቸውን የመረጃው ምንጮች ገልጸዋል”” ጭፍጨፋው የተፈጸመው ሞያሌ ውስጥ በምትገኘው ቦረና ዞን ውስጥ መሆኑም ተሰምቷል”” የህወሓት ጦር እንዲህ ዓይነት ጭፍጨፋ ሲፈጽም ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም፤ ዛሬ በሞያሌ ቦረና ዞን ውስጥ የተፈጸመው ግድያ የአገዛዙ ጭካኔ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ ለመምጣቱ አንድ ማሳያ እንደሆነ ተነግሯል”” ከሞቱት 13 ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ተደብድበው የቆሰሉ ሰዎች፣ እዛው ድንበር ላይ በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን፤ ሆስፒታሉም በሟቾች እና በቁስለኛ ዜጎች መሞላቱን መረጃዎች ይገልጻሉ”” በተጠናቀቀው በዚህ ሳምንት ከሰኞ የካቲት 26 እስከ ረቡዕ የካቲት 28 ቀን 2010 ድረስ ለሶስት ቀናት የቆየ የስራ ማቆም አድማ መካሄዱ ይታወሳል”” መላውን ኦሮሚያ ባዳረሰው በዚህ አድማ ከተሳተፉ ከተሞች መካከል ሞያሌ- ቦረና አንዱ ሲሆን፤ በከተማውም አድማው በስፋት ሲተገበር እንደነበር ይታወቃል”” በዛሬው ዕለት በንጹኃን ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከስራ ማቆም አድማው ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል”” ድርጊቱ ወይም ጭፍጨፋው የቂም በቀል መወጣጫ እንደሆነ የሚናገሩ ወገኖችም አሉ”” በተፈጸመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ13 ቢሆንም፤ በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ሰዎች በመኖራቸው የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል”” በኬንያ እና በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚገኘው ሞያሌ የኢትዮጵያ ኦሮሞዎች በብዛት እንደሚኖሩበት ይታወቃል”” በአጋዚ ጦር የተጨፈጨፉ ንጹኃን ዜጎች፤ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ድንበር ላይ በሚገኙ ሆስፒታሎች ተወስደው ህይወታቸውን ለማትረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል”” የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሳለ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች መኖራቸውን ምንጮች ጠቁመዋል”” ግማሾቹ ተጎጂዎች በሌሎች ከተሞች ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ሪፈር መደረጋቸውም ተሰምቷል”” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጸደቀ በተባለ ገና በአንድ ሳምንቱ በተለያዩ አካባቢዎች ንጹኃን ዜጎች እየተጨፈጨፉ እና እየተገደሉ ይገኛሉ”
BBN NEWS
Image may contain: night and fire

No comments:

Post a Comment

wanted officials