Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 22, 2018

በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ


በምስራቅ ሃረርጌ ነዋሪዎች በወታደራዊ አገዛዙ መማረራቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ/ም) 

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በተለይ በኮምቦልቻ ከተማ ካለፈው እሁድ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ፍተሻ ፣ ነዋሪዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው መጓዝ እንደማይችሉና ህጉን ጥሰው ቢገኙ ሊመቱ እንደሚችሉ ተነግሯቸዋል። ሃዘን ቤት ተቀምጦ ማውራት፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በሁዋላ መዘዋወር እንዲሁም የተለያዩ የውጭ ጣቢያዎችን ማዬት እንደማይቻል እንደተነገራቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።
ካለፈው እሁድ ጀምሮ በተጀመረው ፍተሻ መታወቂያ የሌለው ሰው እየተገረፈ ወደ እስር ቤት ይገባል። የተለያዩ ሃይሎች ገብተዋል በማለት እያስፈራሩ እንደሚገኙ የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ በመኪኖች ላይ የተጠናከረ ፍተሻ እየተካሄደ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ የወታደሮቹ እንቅስቃሴ በእጅጉ እንዳስመረራቸውም ገልጸዋል።
ምስራቅ ሃረርጌ ከፍተኛ ተቃውሞ ከሚካሄድባቸው የኦሮምያ ክልል ዞኖች በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ነው። አካባቢው ከኢትዮ-ሶማሊ ክልል ድንበር ጋር የሚያያዝ በመሆኑ፣ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials