Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, March 24, 2018

የደሕንነት መስርያ ቤቱ የንግስት ይርጋ ወንድም ላይ እየፈፀመ ያለው ግፍ (ሙሉቀን ተስፋው)

ሚኪያስ የንግስት ይርጋ ታናሽ ወንድም ነው። ንግስት ከመታሰሯ በፊት ታናሽ ወንድሟ ሚኪያስ ጎኗ አይጠፋም ይባላል።
ንግስት ይርጋ ከተከሰሰችበት የአማራ ሕዝባዊ ንቅናቄ በፊት ወደአርማጭሆ(ደብረሲና) ተመልሶ በግል ስራ ተሰማርቶ ነበር።
ንግስት መስከረም 5/2009 ዓም ታሰረች። ንግስት ከታሰረች ከወራት በኋላ ታናሽ ወንድሟ ሚኪያስ ስራው ላይ እያለ ታፍኖ ታሰረ። የተወሰደው ወደ ጎንደር ወይንም ወደ አዲስ አበባ ሳይሆን ወደ መቀሌ ነበር። ሁለት ወር ከ17 ቀን በመቀሌ ታፍኖ ከቆየ በኋላ አይኑን ተሸፍኖ ወደ አዲስ አበባ ተወሰደ። አዲስ አበባም ሕጋዊ የሚባል ተቋም አልተረከበውም። ለወራት ጦር ኃይሎች የሚገኘው የደሕንነት ተቋም ውስጥ ከታሰረ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ይዛወራል። ንግስት ተከስሳ ወደ ቃሊቲ ከተዛወረች በኋላ በጥር ወር 2009 ዓም ወደ ማዕከላዊ ተዛወረ። ማዕከላዊ በታሰረበት ወቅት “እህትክን እንድንፈታልህ ከእኛ ጋር አብረህ ስራ” እየተባለ ስቃይ ደርሶበታል። በወቅቱ ሚኪያስን ይመረምሩት የነበሩት ዋነኛዎቹ የማዕከላዊ ሰዎች እንደነበሩ ተገልፆአል።
ከማዕከላዊ የቀረበለትን መደራደሪያ አሻፈረኝ ቢልም፣ አብረውት ታስረው ከነበሩት “ወጥተህ የምትሰራውን አንተ ነው የምታውቀው” የሚል ምክር ያገኘው ሚኪያስ የማዕከላዊን ጥያቄ ተቀብሎ ይወጣል።
ሆኖም ከእስር አልተፈታም። ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር በመኪና አመጡት። ከእናቱ ውጭ ማንንም እንዳያገኝ ተገለፀለት። ሁለት ቀን ብቻ ከእናቱ ቤት እንደቆየ የት እንደገባ አልታወቀም።
እህቱ ከተፈታች ከቀናት በኋላ የሚኪያስ በሕይዎት መኖሩ ተሰማ። ሳንጃ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ። የታሰረበት ምክንያት ከአርበኞች ግንቦት 7 አባል ሆኖ ከኤርትራ ደርሶ ተመልሷል የሚል ነው። ሆኖም በወቅቱ የደብረሲና ቀበሌ አመራሮች ምህረት እንዳስገቡት ለማወቅ ተችሏል። ሚኪያስ ከታሰረ በኋላ ምህረት ያስገቡት የደብረሲና አመራሮችም ለእስር ተዳርገው ነበር። ከሶስት ቀናት በፊት የተፈቱ ሲሆን ሚኪያስ አሁንም በእስር ላይ ይገኛል።
ሚኪያስ የታሰረው ኮማንድ ፖስቱ ከመታወጁ በፊት ሲሆን ፍርድ ቤቱ ዋስ አቅርቦ እንዲፈታ ፈቅዶለት ነበር። መጀመርያ የሰው ዋስ፣ በኋላም የገንዘብ ዋስትና ተፈቅዶለት የነበር ቢሆንም ሁለቱንም በ”ኮማንድ ፖስቱ ስም ተከልክሎ በእስር ላይ ይገኛል።
ሚኪያስ ይህ ሁሉ ግፍ እየደረሰበት የሚገኘው ከስርዓቱ ጋር አልሰራም በማለቱ እንደሆነ እና በዚህ አቋሙ ምክንያትም ህይወቱም አደጋ ውስጥ ነች ተብሏል። ሚኪያስ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ችግር ደርሶበታል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials