Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 2, 2018

ታዋቂው እውነተኛ አርበኛ የልደታ ቤተክርስቲያን የቀድሞ አስተዳዳሪ አለቃ የማነ ብርሃን ስዩም አረፉ

አለቃ የማነ ብርሃን ስዩም ያረፉት ባለፈው ረቡዕ የካቲት 28 ሲሆን ሃሙስ የስርዓተ ቀብራቸውም አርብ የካቲት 30 ቀን 2010 ዓ.ም እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በተገኘበት ቀደም ሲል ባገለገሉበት በየካ የደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
መልዓከ ስብሃት የማነ ብርሃን አቡነ ጳውሎስ ምንም አይነት መንፈሳዊ እውቀት የሌላቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን በልደታ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሃላፊነት በማስቀመጥ በእጅ አዙር ያደርጉ የነበረውን ምዝበራ ምዕመናኑንና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችን በማስተባበር ለማስቆም የታገሉ ብቻ ሳይሆኑ በዚህም የተነሳ ብዙ በደል የደረሰባቸው የእውነተኛ አርበኛ ነበሩ።

በዚህ የተበሳጩት አባ ጳውሎስ አለቃ የማነ ብርሃንን ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ወስነው ለልደታ ሌላ አስተዳዳሪ ይሾማሉ። ይህንን ያልተቀበለው የቤተክርስቲያኗ ምዕመናንም፣ አባ ጳውሎስ ውሳኔያቸውን ይቀይሩ ዘንድ ለማግባባት ከምዕመናኑ፣ ከሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችና ከሰበካ ጉባዔ ወኪሎቹን መርጦ ወደርሳቸው ይልካል። ሆኖም አባ ጳውሎስ የተላኩትን ሽማግሌዎች ከመዝለፍ አልፈው “የምታመጡትን አያለሁ! መንግስት ከጎኔ እንዳለ እንድታውቁ!” በሚል ዛቻ አሳፍረው ነበር የመለሷቸው። ከዚህ በኋላም የአባ ጳውሎስ ስም በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በስርዓተ ቅዳሴ ላይ ሁሉ እንዳይጠራ ተወስኖ ይህም ተግባራዊ ተደርጎ ነበር።
ቅዱስ-ሃብት በላቸው
በምዕመናን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት የነበራቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርሲያን ሊቅና የቀድሞ የነበሩት የአዲስ አበባዋ የማሕደረ-ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ መልዓከ ስብሃት የማነ ብርሃን ስዮም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዪ።

በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ህዳር 9 1995 ዓ.ም ቤተክርስቲያኗ ውስጥ በጥይት የተገደለው ወጣት ስንታየሁ ታደሰ ፎቶ ነው።
ምንም እንኳን በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 11 ላይ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ በግልጽ ቢደነገግም፣ የሕወሃት/ኢሕአዴግ አስተዳደር ግን በግልጽ እጁን በማስገባት በተደጋጋሚ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናንና አቅመ ደካማ ካህናትን ጭምር በጅምላ እያፈሰ ወደ ኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ በማጋዝ በስፖርት፣ በድብደባ፣ እንዲሁም መሬት ላይ በተነጠፈ ጥቁር ኮረኮንች ድንጋይ ላይ በጉልበታቸው እንዲድሁ በማድረግ በርካቶችን ለአካል ጉዳት ዳርጓል። በወቅቱ በከፍተኛ 22 ቀበሌ 03 ውስጥ ልዩ ስሙ ቢርሞ ሜዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነ አንድ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወጣት፣ የታክሲ ረዳትነት ስራውን ጨርሶ ወደ ቤቱ በመግባት ላይ ሳለ ደሴ ሆቴል አቅራቢያ ከጓደኞቹ ጋር ታፍሶ ወደ ኮልፌ ለስቃይ ቢጋዝም፣ ከዚያ በኋላ ግን የደረሰበት ሳይታወቅ ወደቤቱ ሳይመለስ እስከወዲያኛው ቀርቷል።
ሕዳር 9 ቀን 1995 ዓ.ም የፀጥታ ሃይሎች ቤተክርስቲያኗ ውስጥ በፀሎት ላይ በነበሩ ምዕመናን ላይ በከፈቱት ተኩስ ነዋሪነቱ በከፍተኛ 4 ቀበሌ 38 የሆነ ስንታየሁ ታደሰ የተባለ ወጣት ወዲያውኑ ሕይወቱ ሲያልፍ በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ከ1991 ዓ.ም መጀመሪያ አንስቶ እስከ ታሕሳስ 1995 ዓ.ም ድረስ በዘለቀው በዚሁ አለመግባባት፣ አለቃ የማነ ብርሃን ስዪምም በተደጋጋሚ ታስረው ለስቃይና እንግልት የተዳረጉ ሲሆን፣ በጠቅላይ ቤተክህነትም ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻም ተካሂዶባቸው ነበር። በመጨረሻም መንግስት መሃል አዲስ አበባ ላይ በጠራራ ፀሃይ በታንክ የታጀበ ከፍተኛ የታጠቀ ጦር ምዕመናን ላይ በማዝመት የቤተክርስቲያኗን አስተዳደር በሃይል ተቆጣጥሮአል። ከዚህ በኋላም አባጳውሎስ አሁን የአዲስ አበባ አገረ-ስብከት ስራ አስኪያጅ በሆነውንና በከፍተኛ ሙስና በሚታወቀው የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሚመራ የራሳቸውን ቡድን በቤተክርስቲያኗ ውስጥ በሃላፊነት አስቀምጠዋል።
እውቀትን ከትህትና ጋር የተላበሱ የፍቅር ሐዋሪያ፣ የእውነት አርበኛ፣ በእምነት የጸኑ በምግባሪ የቀኑ፣ በቃልና በግብር ሰባኪ፣ ለእግዚአብሔር መኖር እንዴት እነደሆነ በህይወታቸው ጭምር ያስተማሩ መምህር፣ የድሆች አባትና የሁሉ ወዳጅ እየተባሉ የሚወደሱት
አለቃ የማነብርሃን ስዩም፣ ቀደም ሲልም በተለያዩ አድባራት በአስተዳዳሪነት ያገለገሉ ሲሆን የደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋዔል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ ምዕመናኑን በማስተባበርና የወርልድ ቪዥንን ድጋፍ በመጠየቅ 400 አሳዳጊ የሌላቸው ሕፃናት ማሳደጊያ ያቋቋሙ ሲሆን ቀዳማዊ ኃይለስላሴን በማነጋገርም አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በአካባቢው አሰርተዋል።
በምዕመናኑና በካሕናቱ እጅግ ተወዳጅ የነበሩት እኚህ አባት፣ በ1985 ዓ.ም ላይ ከደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋዔል ቤተክርስቲያን ወደ አዲስ አበባው የካ ደብረ-ሳሕል ቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን እንዲዛወሩ ሲወሰን ምዕመናኑ ቅሬታውን ለማሰማት ከደብረዘይት በ12 አውቶቡሶች ሞልቶ ወደ ጠቅላይ ቤተክሕነት በመምጣት ለአባጳውሎስና ለአባ ገሪማ ጥያቄውን አቅርቦ ነበር።
በየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካዔል ሲያገለግሉም ምዕመናኑን በማስተባበር የቅዱስ ሚካኤል ጽላት ወደ ቤተክርስቲያኑ ከመግባቱ በፊት የነበረበት ታሪካዊ ዋሻ ታድሶ ለመዘክርነት እንዲውል አድርገዋል፤ በአካባቢው መብራት ስላልነበር መብራት እንዲገባ አድርገዋል፣ ለሕዝብ አገልግሎት የሚውል ወፍጮ አስተክለዋል፣ ቤተ ክርስቲያኑ ቋሚ ገቢ ያገኝ ዘንድ አራት ሱቆችን አሰርተዋል። መል ዓከ ስብሃት የማነ ብርሃን ስዮም ከማሕደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያምና የደብረ መድሃኒት መድሃዔአለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ስራቸው በሃይል ከተነሱ በኋላ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ላለፉት 15 ዓመታት ደብረዘይት/ቢሾፍቱ በሚገኘው ቤታቸው በፀሎት ተወስነው ነበር የሚኖሩት።

No comments:

Post a Comment

wanted officials