Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 6, 2018

ዘርማ ተዘጋጅ! “መብታችንን ለመጣስ የታወጀብንን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በአንድነት እንኮላሸዋለን!”


ከዘርማ የተላለፈ መልዕክት
የወያኔ ህወሃት እንቢተኛዉ ቡድን ካደረበት ከፍተኛ ንቀት መንፈስ የተነሳ በሰላማዊ መንገድ የጠየቅነዉን መብታችንን መንፈጉ ሳያንሰዉ ወጣቱን የዘርማ ሐይል ማፈኑን ተያይዞት ይገኛል።
በመሆኑም ይህ ስርአት ፈጽሞ ጥያቄያችንን ሊመልስልን ፈቃደኛ ያለመሆኑን በእብሪት አረጋግጥልናል!
እኛም መብታችንን ማስከበር የምንችለዉ እራስችን መሆናችንን በሚገባ ያረጋገጥንበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
የጉራጌ ህዝብ ላለፉት 27 አመታት የደረሰበትን ግፍና በደል በጫንቃዉ ተሸክሞ ቀን ያስተምራቸዋል በሚል ኢትዮጵያዊነት ክብር በትእግስት ቢጠብቅም በአምባገነኖቹ መሪዎቻችን በኩል የመሻሻልም ሆነ የመፈወስ ለዉጥ አልታየም።
ወንድሞቻችን የዘርማ ጀግኖች ብሶት በወለደዉ ቁጭት እንቢኝ ለመብታችን ብለዉ የተሰዉለት እንዲሁም የታሰሩለት አላማ ምላሹ ጥይት መሆኑን ተረድተናል።
ምንም ሆነ ምን ከእንግዲህ የጉራጌን ህዝብ ሊመልሰዉ የሚችል አንዳችም ምክንያት የለዉም ዘርማዎች የሞቱለትን የታፈኑለትን የመብት ጥያቄ ከፍ አድርገን በመያዝ ለመጨረሻዉ ድል እንድንዘጋጅ ጥሪያችንን እናስተላለፋለን።
መብታችንን ለመጣስ የታወጀብንን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በአንድነት እንኮላሸዋለን !
ፍጹም ለዉጥ ካልመጣ ፍጹም ሰላም እንደማይኖረን አስረግጠዉ በይፋ ያወጁብንን ሀይሎች እስከመጨረሻዉ እንፋለማለን።
በኦሮምያ ክልል እና በአማራ ክልል የሚገኙ አቻዎቻችን ቄሮ እና ፋኖ ለስልታዊ ትግሉ ዝግጅታቸዉን እያገባደዱ የሚገኙ ሲሆን በእኛ በኩልም ይህዉ ተመሳሳይ ዝግጅት በብርቱ እንዲደረግ ሁላችንም የበኩላችን ጥረት እናድርግ።
አንድነት ሐይል ነዉ !
ድል ለዘርማ !
ድል ለኢይትጵያ ህዝብ !

No comments:

Post a Comment

wanted officials