Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, March 20, 2018

የጤና ጥበቃ ሚ/ር አርቲስት ፍቃዱ ተ/ ማርያም በነጻ ሙሉ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በሀገር ውስጥ ማድረግ እንዲችል ፈቃድ ሰጥቷል።



ደስ የሚል ዜና ስለፍቄ
~~~~~~~~~~~~
የጤና ጥበቃ ሚ/ር አርቲስት ፍቃዱ ተ/ ማርያም በነጻ ሙሉ የኩላሊት ንቅለ ተከላ በሀገር ውስጥ ማድረግ እንዲችል ፈቃድ ሰጥቷል።
አርቲስቱ ለ5 ዓመት ያክል የቲቢ በሽታ መከላከል የክብር አምባሳደር በመሆን አገልግሏል። በዚህም ሚ/ር መስሪያ ቤቱ አርቲስቱ የኩላሊት ንቅለ ተከላውን በነጻ እንዲያደርግ ፈቅዷል።
አርቲስት ፍቃዱ ሁለቱም ኩላሊቶቹ አገልግሎት በማቆማቸው ለንቅለ ተከላ ከሀገር ውጭ ለመሄድ በወዳጆቹና በአርቲስቱ አድናቂዎች የገቢ ማሰባሰብ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል።
Image may contain: 2 peopleከ40 ዓመታት በላይ በብሔራዊ ቴአትር መድረክ የነገሰው ይህ ፈርጥ ከሰራቸው አያሌ ተውኔቶች ውስጥ <ቴወድሮስ> ሁሌም ከምናባችን የማይጠፋ ህያው ስራ ነው፡፡
አርቲስቱ የጤና ጥበቃ ሚንስቴርም የ <ቲቭ> አምባሳደር በመሆን የቲቪ በሽታን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ሲደግፍ ቆይቶል፡፡ በዚህ ውለታውም የጤና ጥበቃ ሚንስቴር በሀገር ውስጥ ለሚደረገው ህክምና የሚወጣውን ወጭ ለመሸፈን ቃሉን ሰጧል፡፡
በ <go fund> በኩልም በ4 ቀን ብቻ ከ 53 ሺ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ፍቃዱ በህዝብ ልብ ውስጥ ያለውን ቦታና የ <ሀበሻን ውለታ መላሽነት መልካም ባህል በአንፃሩም ቢሆን የሚያሳይ ሁነት ነው፡፡
ፈጣሪ ምህረትን ይስጥህ!

No comments:

Post a Comment

wanted officials