Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, March 10, 2018

የአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው የባሰ መሆኑን የህወሓት ሊቀ- መንበር ተናገሩ

ለሁለተኛ ጊዜ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር፣ ባስ ያለ መሆኑንዶ/ ር ደብረጽዮን ገ. ሚካኤል ተናገሩ”” በቅርቡ የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት እና የህወሓት ሊቀ- መንበር ሆነው የተሾሙት ደብረጽዮን፤ ይህን ያሉት ትላንት አርብ የካቲት30 ቀን 2010 በሰጡት መግለጫ ሲሆን፤ በመግለጫቸውም ስለ አዋጁ እና ስለ ሀገሪቱ ‹‹ ››የጸጥታ ሁኔታ አውርተዋል”” የአሁኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከበፊቱ ጠበቅ ያለ ነው በማለት የአዋጁን አፋኝነት አምልጧቸው የተናገሩት የህወሓቱ ሊቀ- መንበር፤ አዋጁ የታወጀው ስርዓቱን ለማፍረስ የተደራጁ ኃይሎችን ለመምታት እንደሆነም ገልጸዋል”” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ እንደሰፈረው መመሪያ ከሆነ፣ የትኛውም የክልል ባለስልጣን ከኮማንድ ፖስቱ በቀር፣ በሀገሪቱ የጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠት አይችልም”” ሆኖም የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ ር ደብረጽዮን ግን፣ አዋጁን እና አፈጻጸሙን እንዲሁም ስለ ሀገሪቱ ወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ትላንት መግለጫ ሰጥተዋል”” የአዋጁን መጽደቅ ተከትሎ በአብዛኛው ወታደሮች የተሰማሩት በአማራ፣ ኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች መሆኑ ይታወቃል”” እስካሁን የአዋጁ ሰለባ ያልሆነውን የትግራይ ክልል የሚመሩት ደብረጽዮን ገ. ሚካኤል፣ ስለሌሎች ክልሎች የጸጥታ ሁኔታ መግለጫ ለመስጠት ደፍረዋል”” በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ከህዝብ ጋር አብራችኋል ተብለው በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት፤ የትግራዩ ሹም ደብረጽዮን ግን በኮማንድ ፖስቱ ጣልቃ በመግባት ስለ ሀገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ እና እየታሰሩ ስለሚገኙ ሰዎች መግለጫ ሲሰጡ ተስተውለዋል”” የሌሎች ክልሎች ባለስልጣናት ስለ ሌላው ክልል ይቅርና ስለራሳቸው ክልል እንኳን በጸጥታ ጉዳይ መግለጫ እንዳይሰጡ ተደርገው ባለበት በዚህ ሰዓት፣ ዶ/ ር ደብረጽዮን አፈንጋጭ መግለጫ መስጠታቸው አስገራሚ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ”” ይህ አንዱ የህወሓት የበላይነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ታዛቢዎቹ ያክላሉ”” በኢትዮጵያ ውስጥ ‹‹ህዝባዊ ትግል እየተካሄደ የሚገኘው የስርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚታወቅ ሲሆን፤ ደርግን ›› ገርስሰን መጣን የሚሉት የህወሓት ሹማምንት፣ ትግሉን ከሽብር እና ወንጀል ጋር መፈረጃቸው ያስገርማል ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች”” ባንክ እየዘረፉ ከደርግ ጋር ሲዋጉ የነበሩት ህወሓቶች፣ አሁን ላይ በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ ያለውን የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እንደ ወንጀል መቁጠራቸው ያበሻቅጣል ሲሉም አስተያየት ሰጪዎቹ ይገልጻሉ”
BBN NEWS

No comments:

Post a Comment

wanted officials