Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 9, 2018

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ስዩም ተሾመ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተነገረ

ስዩም ተሾመ
ከሁለት ቀን በፊት ለእስር የተዳረጉት አቶ ስዩም ተሾመ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተነገረ”” በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ መምህር የሆኑት አቶ ስዩም ሐሙስ የካቲት 29 ቀን 2010 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊሶች ተይዘው መታሰራቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ በዕለቱ አቶ ስዩምን ለማሰር ወደ መኖሪያ ቤታቸው የሄዱት የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ በመምህሩ ላይ ከፍተኛ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ተገልጿል”” አገዛዙን በመተቸት እና ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን በማቅረብ የሚታወቁት አቶ ስዩም በአሁን ሰዓት በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙ ሲሆን፤ እሳቸውን ለመጠየቅ የሄዱ አንድ ግለሰብ አቶ ስዩም ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል”” የፖለቲካ እስረኛው ስዩም ተሾመ፣ ሊያስሯቸው ቤታቸው ድረስ በሄዱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለጠያቂያቸው የነገሯቸው ሲሆን፤ ድብደባው የተፈጸመባቸውም የላፕቶፓቸውን ፓስወርድ ተጠይቀው አልናገርም በማለታቸው እንደሆነ አቶ ስዩም ተናግረዋል”” የላፕቶፓቸውን ፓስወርድ እንዲናገሩ አቶ ስዩምን ያስገደዱት ወታደሮቹ፤ መምህሩን በኃይል ከደበደቡ በኋላ ፓስዎርዱን ሊቀበሏቸው እንደቻሉ ተነግሯል”” አቶ ስዩምም በተፈጸመባቸው ከፍተኛ ድብደባ የተነሳ ፓስዎርዳቸውን ለመስጠት መገደዳቸውን እስር ቤት ሊጠይቋቸው ለሄዱት ሰው ተናግረዋል”” ወታደሮቹ በዚህ ሳያበቁ ከአቶ ስዩም ቤት ሶስት ላፕቶፖችን ከወሰዱ በኋላ ቤት ውስጥ ያገኙትን ዕቃ አውድመው እንደወጡም አቶ ስዩም ተናግረዋል”” ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ አገዛዙን በመተቸት የሚታወቁት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ትላንት የካቲት 30 ቀን 2010 በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን የ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መፍቀዱ ታውቋል”” በዚህም መሰረት ለመጋቢት 14 ቀን 2010 ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ የተሰጣቸው አቶ ስዩም፤‹‹ ›› በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን አመጽ ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ ነበር የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ችሎቱን የታደሙ እማኞች ጽፈዋል”” የህወሓትን አገዛዝ አምርረው የሚቃወሙት አቶ ስዩም ተሾመ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሰዋል በሚል ሰበብ ባለፈው ዓመት ታስረው መፈታታታቸው ይታወሳል”” አሁን ለሁለተኛ ጊዜ የታሰሩትም በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፈው ሳምንት የጸደቀውን አዋጅ ጥሰዋል በሚል ሰበብ እንደሆነ ታውቋል”” ዓለም ዓቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲፒጄ፣ የአቶ ስዩምን መታሰር አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፣ መምህር እና ጦማሪ የሆኑት አቶ ስዩም ተሾመ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል”” አገዛዙ አቶ ስዩምን እስር ቤት መክተቱንም ሲፒጄ ተቃውሟል”
BBN NEWS

No comments:

Post a Comment

wanted officials