ዛሬም፤ ሰላማዊዎቹ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድምጻችን ይሰማ እያሉ ነው።
ዛሪም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችን የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ተውለብላቢ እያውለበለቡ ድምጻችን ይሰማ እያሉ ሰላማዊ ተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን ሰምተናል (አይተናልም)
ጭንቅ….ቅ ያለኝ ነገር ምን እንደሆን ታውቃላችሁ… መንግስታችን እስከ መቼ ድረስ ነው ”የራስሽ ጉዳይ” የሚለውን ዘፈን በሞንታርቦ ከፍቶ እና ሞንታርቦን ያክል ነገር ጆሮው ላይ ደቅኖ እየሰማ ከየ አቅጣጫው የሚመጡ እሪታዎችን አላዳምጥ የሚለው…
እውነቴን ነው የምለው፤ እኛ ስንናገር ሌላ ይመስልብናል የኢህአዴግዬ የስጋ ዘመድ የሆናችሁ ወዳጆች ግን ኋላ እንዳይቆጫችሁ ከአሁኑ ምከሯት፤ ተይ ስሚ፣ ተይ አድምጪ፣ ተይ ተይ ተይ… በሏት። (ዝም ብላችሁ አትብሏት) ኋላ አጓጉል አወዳደቅ ትውድቅ እና እናንተም ትበሉት እርሷም ትሆነው ይቸግራታል።
abetokichaw