ኦሮሞውም ኦህዴድም የ ህወሃት መጫወቻ
መሳሪያ ከመሆን ይዳን
በአብራሃም ዘታዬ ከ ጀርመን
የኦሮሞን ህዝብ ለመጨቆን በ ህወሃት ኢህአዴግ የተፈጠረው ኦህዴድ ከህወሃት የባሰበት ጠባብ እንደሆነ ለመረዳት በጣም የቅርብ የሆነ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ። በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትነት እንደተመረጡ የታመሙት አለማየው አቶምሳ ሲሞቱ
በመላ ሃገሪቱ ለ ሶስት ቀን የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ዝቅ
ብሎ እንዲውለበለብና 3 ብሄራዊ የሀዘን ቀናት መታወጁ ይታወሳል
መላ ሃገሬው በሃዘን ተቀመጥ ተብሎ የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ዝቅ ብሎ ተንጠልጥሎ የሳቸው
አስከሬን ግን ሲቀበር የኦሮሚያ ባንዲራ ብቻ መልበሱ አነጋጋሪ ነበረ በዚህም
የኦህዴድ መሪዎች የሚለፉት የሚሞቱት ለ ኢትዮጵያ እንዳልሆነ አሳይተዋል።
የማንኛውም ክልል መሪ ተጠሪነቱ ለ ሃገሩ ጠቅላይ ሚንስትር እንደሆነና መስራት ያለበት ፕሬዝዳንት ለሆነበት ክልል ብቻ ሳይሆን ለ ሃገሩ ኢትዮጵያም እንደሆነ በህገ መንግስታቸው የጻፉት ነው ። ባይነግሩንም ማንኛውም ፓርቲ ከክልሉ በዘለለ ሃገር አቀፍ ራዕይ ነድፎ እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል። ነድፎ የሚለው ቃል ይሰመርባት ። በኢሕአዴግ ለሃገር መስራት ባይበረታታም በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ጠቅላይ ምኒስትሩ ፥ የየክልል ፕረዚዳንቶች ወዘተ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ፊት ለክልሉ ለሃገሩ ብሎም ለ አፍሪካ ተጠቃሽ የሚሆን ስራ በታማኝነት ለመስራት ቃለ መሃላ ለይስሙላ ይገባሉ።
በተግባር ግን ሃገር በማፍረስ በክልላቸው ግጭት በማስፈን የነሱ ያልመሰላቸውን ጎሳ በማፈናቀል የተንኮል ስራ ተጠምደዋል። ሃገር እያፈረሱም ቢሆን ሲሞቱ ግን የተጣላ ያስታረቁ የተበታተነ የሰበሰቡ ያህል ይካበድላቸዋል። ኢትዮጵያን ከወራሪ ጣልያን ሲከላከሉ የሞቱ ሰማዕታት በክብር ማረፊያ የአዲስ አበባው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ውስጥ ወያኔ የውጭ ባንዳ መሆኑ እየታወቀ በድፍረት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተሸፍኖ ይቀበራል። የእውነተኛ አርበኞች ቦታ የሃሰት ባንዳ ጎሰኞች ያረክሱት ጀምሯል። ለሃገራቸው ለሰንደቅ አላማቸው ክብር የተሰው አባት አርበኞች ባረፉበት ቦታ ባንዲራ ጨርቅ ነው ብሎ የነበረው ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ባንዲራውን ለብሶ ተቀበረበት። ደረታቸውን ለጥይት የሰጡ ሃቀኛ ወታደሮች በክብር ታጅበው በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተሸፈነው ቢቀበሩ ቅሬታ ላይኖር ይችላል ይሁንና የህወሃትን ትግል በማነቃቃት በዘፋኝነት ጀምሮ በ ነጋዴነት ያጠናቀቀው ኢያሱ በርሄ በ 2010 ሲሞትም በ ወታደራዊ ማርሽ ታጅቦ አስከሬኑ ከሰሜን ኢትዮጵያ መሃል አገር ድረስ መጥቶ በ ቅድስት ስላሴ ሲቀበር ሳጥኑ በ ወያኔው የኢትዮጵያ ባንዲራ ተሸፍኖ እንደነበር ያስታውሱ ይህን ዩቲዩብ ይመልከቱ http://www.youtube.com/watch?v=YrFU39VatEk
ህወሃት ቀብሩን ሃገራዊ መልክ የሚያላብሰው ኢትዮጵያን ስለሚወድ አይደለም። ሕወሃት ኢህአዴግ ኤርትራን ከኢትዮጵያ አቆራርጧል፥ የ ጎንደርን መሬት ለ ሱዳን ሰጥቷል፥ ከተረፈውም መሬት ዜጎችን ካሳ ሳይከፍል ማፈናቀሉ ሳያንስ ለ ውጪ ኢንቨስተሮች ለህንድ ለ ቻይና ለአረቦች እየሸለመ ይገኛል። እየዘራ ያለው ሃገርን በጎሳ የመከፋፈል አደጋው ሃገር የማተራመስ የማፈራረስ ዕቅዱና ድርጊቱ ከፋሺሰቱ ናዚ ሞሶሎኒ የባሰ ነው። ፋሺሰት ወራሪን በመመለስ ለተሰው ግፍ ለተሰራባቸው
ወገኖች አፅም ማረፊያ ቅዱስ ቦታ ለምን ግፈኛው ዘረኛው ናዚ ወያኔ ይቀበራል?? ፖለቲካ የለየንን መቃብር አንድ ሊያደርገን አይገባም። ሰሜን ሞቶ ካልጠፋ ቦታ መሃል አገር መጥቶ መቀበር አርበኛ ስለማያሰኝ ወያኔዎችን እዛው በሰፈራቹ እንበላቸው ገፍተው ከመጡም ቦታቸንን ማስከበር
ከአርበኛ ልጆች ይጠበቃል።
ስንት እሳተ ጎሞራ አርበኞች በከተሙበት ካቴድራል የ ሃገር ፍቅር የሌለው ጠቅላይ ሚንስተር ና የዱባይ ነጋዴ ለዚያውም በኢትዮጵያ ባንዲራ ተሸፍነው ሲቀበሩ ማየት እንደቀልድ አይታይም። በእርግጥ ወያኔ የቀየረው በ ክብ ውስጥ ኮከብ የሰፈረበት የ ፓጋኒዝም ምልክት የሆነው ባንዲራ አምልኮተ እግዚአብሄርን
ከማንም ቀድማ የምታውቀው የሃገራችን ባንዲራ እንዳልሆነ ቢታወቅም
በሰንደቅ አላማ ታጀቦ የመቀበር ክብር በወያኔዎች ሊቀል
አይገባውም።
በሰንደቅ አላማ ታጀቦ የመቀበርን ክብር ከወያኔዎች ቀጥሎ ያዋረዱት ኦህዴዶችም
ከተጠያቂነት አያመልጡም የሶስት ቀን ሃዘን ታወጆላቸው የሃገሪቱ
ባንዲራ ለ ሶስት ቀን ዝቅ ተደርጎ ተውለብልቦላቸው የኦሮሚያ ባንዲራን ብቻ የሞተውን በድን ማልበስ መላ ኢትዮጵያውያንን መናቅ
ነው ። አለማየው የሞተው ወይም ኦህዴዶች የሚሰሩት ለ ኦሮሚያ
ብቻ እንደሆነ በኦሮሞ የዋህነት በግልጽ አሳይተዋል። ነጋዴው እያሱም ጠቅላይ ምኒሰተሩም ህወሃት ግን ሲሞት የኢትዮጵያ ባንዲራ ለብሶ
ለሃገሪቱ እንደሰራ ይቀባጠርለታል።
*ኦህዴዶች በግልጽ ባሳያችሁን የኢትዮጵያን ህዝብ ጥላቻ የወያኔ እጅ
እንዳለበት ስለምናውቅ አልተገረምንባችሁም አቶ አለማየው ለሀክምና የጨረሱት 40 ሚሊዮን በላይ ወጪ ግን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ሰለሆነ እንድትመልሱ አስቡበት።
*ከኦሮሚያ ፐሬዘዳንትነታቸው በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቪዝንንና ራዲዮ ማኔጂንግ
ዳይሬክተር ሳሉ ነበረና የመጨረሻ ደስ ብሏቸው ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር የተገናኙት ኢትዮጵያዊ ብታረጓቸው የሙቱ ነፍስም ደስ ይላታል።
*አባዱላን ፈንግለው ሳይታሰቡ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ በወሰዱት የጸረ ሙሰና እርምጃ
ተናዳችሁ ባቀመሳችኋቸው መርዝ የኦሮሞኦህዴድን ተንኮል ተፀይፈው
ሳይመቻቸው በህመም ያሳለፉትን ፐሬዚዳነትነት የወደዱላችሁ ይመስል ይበልጥም ታመው ሳለ በቀየራችሁት አዲስ የ ኦሮሚያ ባንዲራ
ስትቀብሯቸው እያወናበዳችሁ እንደሆነ አልታወቃችሁም?
*ከአባዱላና መሰል ኦህዴዶች ጋር ደስተኛ ጊዜ እንዳላሳለፉ እያወቃቸሁ
አይናቸሁን በጨው አጥባቸሁ ፕሬዚዳነታችንን አጣን ስትሉ አታፍሩም
?
*ህወሃት አጭበርባሪ ነጋዴ እያሱን በኢትዮጵያ ባንዲራ ሲቀብር የኦሮሚያ ፕሬዚደንትን ሃገራዊ ክብር ማሳጣታችሁ ለቅሶ
የሚደርሷችሁን ክልሎችን ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያን ዝቅ ማድረግ ነው።
ኦህዴዶች
በተረፈም ጠፍጥፎ ከሰራችሁ ህወሃት ሰይጣናዊ ፖለቲካዊ ብልጠት ተማሩና ስትቀበሩ እንዲያምርባችሁ ኢትዮጵያዊነትን ልበሱ ብቻችሁን አታልቅሱ ዘረኝነትን በግልጽ ከማሳየት ተቆጠቡ ።
መላ መልኩ የ ኦነግ የሆነውን (የሚመስለውን) አዲሱን የኦህዴድ አርማ ባንዲራ መምረጣችሁ ካልቀረ የ ኦነግን ባንዲራ
መለያ በማንገባቸው ያሳሰራችሁአቸውን የኦሮሞ ተማሪ እስረኞችን
ባስቸኳይ አስፈቱ። ኦነግ ከድሮም የመለያ ባንዲራው የኢትዮጵያ ከሚባለው ሰንደቅ አላማ ቀለማት ብቻ
የተቀመመ መሆኑ ዘግይቶ ገብቷችሁ እንዳስተካከላችሁት ኦነግ ሲታገልለት ከነበሩት ሌሎችም ፍላጎቶች እየተገበራችሁለት እንዳለው
ሁሉ ማንኛውንም ኦሮሞ በአሸባሪነት ላለማሰር የአቋም ማስተካከያ አድርጉ። በዚህም ጊዜ የአዲሱ የኦሮሚያን መለያ ባንዲራ
የወሰድነው ከኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ነው ልትሉም ትችላላችሁ ስለሆነም ነው ሃገራዊ ሀዘን የታወጀለትን ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያዊ
ደንብ ባለማልበሳችሁ በሙቱ ነፍስ የተወቀሳችሁት።
ከሁሉም በላይ
የምትወቀሱት ልማቱ ኦሮሞን ያጠገበ ይሁን ፍትሃዊ የሃብት ከፍፍል በ ኦሮሚያ በማለታቸው ለእስርና ለስደት ወገናችሁን በመዳረጋችሁ ስለሆነ ጥያቄውን መልሱ። በኦሮሚያ ምድር
ኦሮሞዎች የማይመሩት ቢያንስ በብዛት የማይቀጠሩበት የህወሃት ኢፈርትና መሰል ድርጅት መኖር የለበትም።
ኦህዴድ
የህወሃት መጫወቻ ከመሆን ይዳን
No comments:
Post a Comment