Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 13, 2014

የኢትዮጵያ ጦር በአልሸባብ ላይ የተጠናከረ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የንቅናቄው መሪ በኢትዮጵያ ላይ ጅሃድ አወጁ


ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
የአልሸባብ መሪ አህመድ ጎዳኔ በቅጽል ስማቸው ሙክታር አቡ አል ዙቢያር ” ለአሜሪካ መንግስት ጥቅም የሚዋጉት የሞቃዲሾ መንግስትና የኢትዮጵያ ጦር በጦርነቱ ድል ይሆናሉ “ብለዋል።
“ሶማሊዎች ሃይማኖታችሁ ተደፍሯል፣ መሬታችሁ ተከፋፍሏል፣ ንብረታችሁ ተዘርፏል፣ ድላችን በጅሃድ ላይ የተመሰረተ ነው ” ሲሉ ሚ/ር ጎዳኔ ተናግረዋል።
ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ  ወደብ ለማገኘት ስትል ሶማሊያን መውረሩዋን የሚናገሩት የአልሸባቡ መሪ ፣ “ኢትዮጵያ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ትሸነፋለች፣ ሙስሊሞችም ተጠናክረው ይወጣሉ። ብለዋል።
ኢትዮጵያና ኬንያ የሶማሊያ ግዛቶችን ለመከፋፈል ማቀዳቸውንም መሪው አክለዋል። አምና በአልሸባብ ውስጥ  የተፈጠረውን የውስጥ ሽኩቻ ተከትሎ በርካታ የድርጀቱ መሪዎች ስልጣናቸውን ለቀዋል ወይም ተገድለዋል።
አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በህዝቡ ላይ የሚፈጽመው የሽብር ጥቃት ብዙ ሶማሊዎችን ሳያሳዝን አልቀረም። አህመድ ጎዳኔ ያስተላለፉት አዲሱ ጥሪ ከዚህ በፊት ጣህር አዌይስ እንዳስተላለፉት የብዙ ሶማሊዎችን ስሜት ይገዛል ተብሎ አይጠበቅም።
የኢትዮጵያ ጦር እየሰነዘረ ባለው ጥቃት ጠንካራ የሚባሉ የአልሸባብ ይዞታዎች እየተለቀቁ ነው። የአትዮጵያ ጦር በመላዋ ሶማሊያ ከሚገኘውን አልሸባብ ጋር የመዋጋት ፍላጎት ይኑረው አይኑረው አልታወቀም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials