ከሰላማዊ ሰልፍ ወደ ተቀጣጣይ ሰልፍ
በመሻገር ወያኔን እናስወግድ
በአብራሃም ታዬ
የነጻነት ዕጦት፥ የዲሞክራሲ ዕጦት፥ የመልካም አስተዳደር ዕጦት፥ የፍትህ
ዕጦት፥ የዘረኛ መንግስት ጦስ ፥ከመኖሪያ ቀዬ የመፈናቀል ችግር
ወዘተ ብሶቶች ለአደባባይ ሰልፍ ከዳረጉን ቆዩ ። ኢትዮጵያን
እየገዛ ያለው ከፋፋዩ ፋሺስት ወያኔ ራሱ ሰበብ ሆኖን እንዲያውም ዝም ባልንበት ሰድቦን በመቃወም ላስወጣን ሰልፎች ምንም ምላሽ
አለመሰጠቱ አምባገነንነቱን ያሳያል። በቅርቡ የፀረ አማራ ስድቡን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ከሀያ ሺ በላይ ወገኖች በነቂስ ወጥተው ያደረጉት ታሪካዊ ሰልፍ ላይ “የኢህአዴግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል” ፥ “የህዝብን ክብር የደፈሩት አቶ አለምነህ መኮንን ለፍርድ ይቅረቡ” እና መሰል አገዛዙን ያስበረገጉ መፈክሮች ተሰምተዋል። አምባገነኑ አገዛዝ ግን ምንም ምላሽ አልሰጠም። ይበልጥም ከ አንድ ቀን ጩኸት አይዘሉም ብለው ተሳልቀውብናል። በተለያዩ የሃገሪቱ
ከተሞች የተደረጉ ሰልፎችንም ከምንም ባለመቁጠር የጉጅሌው መንግስት ጠቅላይ ሚነስትር ሳይቀር ከመርፌ ቀዳዳ ጠቦ ለሚሰጠን
መብታችን ተቃዋሚዎች ለሚያደርጉት ሰልፍ በ የእሁዱ ፖሊስ መመደብ ሰለቸን ብለውን ካስፈለገም ሊከለክሉን እንደሚችሉ ነግረውናል።
ስለዚህ የተገኘችው ሰልፍ ፈቃድን የሙጥኝ ብለን መልስ ካላገኘን ከስፍራው
አንንቀሳቀስም የሚል አዲስ ስልት መንደፍ ያስፈልገናል። የፖለቲካ ጥያቄን ለመጠየቅ ተሰብስበው ፍትሃዊ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ አደባባያቸውን
ባለመልቀቃቸው ለውጥ ያገኙ የሌላ ሃገር ህዝቦች ተሞክሮ በዚህ ጽሁፍ ባጭሩ ቀርቧል። ጭብጡ ህዝባዊ ሰልፎች ወደ ህዝባዊ አመፅ
ተቀይረው ነጻነትን ባጭር ጊዜ እንዴት እንዳገኙ መዳሰስና ማበረታታት ነው።
የቱኒዝያ ተሞክሮ
የመናገር ፥ የፖለቲካ ነጻነት ተነፍጎት ፥በስራ ዕጥነት ፥በኑሮ ውድነት ማቆ መንግስታቸው በሙስና ተጨማልቆ ይኖር የነበረው የቱኒዚያ ህዝብ የስርዓት ለውጥ ያመጡት ካንድ ወር ባነሰ ጊዜ (10 December 2011 - 14 January 2011) ያለማቋረጥ ባዳረጉት ህዝባዊ ሰልፍ ነው። ቱኒዝያውያን ለሰልፉ መነሻ የሆናቸው
ኑሮ ውድነትን በመቃወም ራሱን ያቃጠለውን የአንድ ቡአዚዚ የሚባል ወገናቸውን ጥያቄ በማሰተጋባት ሲሆን በወቅቱም በሃገራችንም
የኔሰው ገብሬ የተባለ የደቡብ ክልል መምህር የታሰሩ እንዲፈቱ በመጠየቅ ራሱን በኖቬምበር 2011 ሲያቃጥል ሌሎችም በተናጥል መንግስትን የተለያየ ጊዜ
የመቃወም እርምጃ ሲያደርጉ ለመነሳሳትም ሆነ ለሰላማዊ ሰልፍ እኛ ሃገር አልታደልንም ነበር።
የቱኒዝያንን ተሞክሮ አይተው የተነሱት ሊብያውያን 42 ዓመት ጫንቃቸው ላይ የነበረውን ሙአመር ጋዳፊን ለማውረድ የፈጀባቸው 6 ወር ብቻ ነው። በ17 February 2011 ተጀምሮ በ 23 August
2011 ጋዳፊ ተገደለ።
የዩክሬን ተሞክሮ
ወቅታዊ ከሆነው በአውሮፓ የዩክሬን ተቃውሞም የምንማረው ቀን ተሌት የሚታገሉለት ህዝባዊ አመጽ እያሸነፈ መምጣቱን ነው። በዋና ከተማው ኪየቭ በሚገኘው ኢንዲፐንደንስ ስኩየር ዩክሬናውያን በአንድነት መንግስት ካልተለወጠ አንንቀሳቀስም ብለው ለነጻነታቸው ዋጋ ከፍለዋል። የህዝብ ተመራጭነቱን ያስመሰከረው ፓርላማ ያንኮቪችን ለማስወገድ የተስማማው ህዝቡ ለ አንድ ሳምንት ያህል ሳይታክት በአደባባዩ ባሳየው መስዋዕትነት ነው።
ከ10 ዓመት በፊትም የቡርትካናማ አብዮት ተብሎ የሚታወቀውን ያካሄዱ ናቸው። የሚገርመው ምርጫ በድጋሚ እንዲካሄድ በተጠራው በዚህ ቡርትካናማ አብዮት ለሁለት ወራት ከ22 ኖቬምበር 2004 እስከ 23 ጃኑዋሪ 2005 በዛው አደባባይ ጠይቀው ዛሬ ያስወገዱት ያንኮቪች ያኔ የድጋሚ ምርጫውን ፍርድቤት አጽድቆለት ሲያስተዳድራቸው የነበረ ነው።
ህዝብ መሪውን በአደባባይ ይመርጣል ህዝብ መሪውን በአደባባይ ተቃውሞ ያባርራል።
በህዝባዊ ሰልፉ
ለ ኦስካር ሽልማት የታጨው “አደባባይ”
ግብጻውያን ሆስኒ ሙባረክን ፌብራሪ 2013 ያስወገዱት ለ 17 ተከታታይ ቀንና ሌሊት በካይሮ ታህሪር ስኩየር ባደረጉት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው። ሙባረክን አስወግዶ ስልጣን የያዘውንም ሙስሊም ብራዘር ሁድ ስብስብ ተረኞቹ ጁላይ 2013 ሲያስወግዷችውም የተቃውሞ ስልፍ ቦታቸው ታህሪር ስኩየር ቀን ተሌት ሳይለዩ ደጅ የጠኑት ከአንድ ሳምንት አይበልጥም። ይሄ ሁሉ ድራማዊ ሽግግር የመጣው ደሞ ሳይታክቱ በሰልፍ ቦታቸው በመገኘታቸው ነው። ዘ ስኩየር የሚል ዶክመንታሪ ፊልም ተሰርቶለት የታህሪር አደባባይ በቅርቡ ለ2014 ለኦስካር ሽልማት ታጭቶ የነበረውም በዚሁ ነው። www.cnn.com/2014/02/11/opinion/egypt-revolution-anniversary
ባለፈው ማርች 2 2014 አካዳሚ አዋርዱን በሌላ አፍሪካዊ ታሪክ ቢቀደምም ዘ ስኩየር ፊልሙ ዘ ፒፕልስ ቾይስ ዶኩመንታሪ አዋርድ በ ቶሮንቶ 2013 ኢንተርናናል ፊልም ፈስቲቫል እና የ2013 ዘ ኦዲየንስ አዋርድ በ ሰንዱንስ ከተማ አሸናፊ የሆነ ነው። http://www.youtube.com/watch?v=twB2zAOzsKE
እንግዲህ የኛ መስቀል አደባባይ ሳይሆን የደመራ በዓል ነው በ ዩኔስኮ የ አለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው። ለምን ሰለነጻነታችን ሰለሃገራችን አንድነት የምናቀነቅንበት ይኸው አደባባይ ሆኑ ሌሎች ብሶት መተንፈሻ ቦታዎቻችን ከነ ምናደርገው እንቅስቃሴ ለምን ለአለም አቀፍ ሽልማት አልታጨም? ዶክመንታሪ ፊልም ሆኖ የዶክመንታሪ ፊልም አዋርድ ማግኘቱ ይቅርና ሰልፋችንን መቅረጽስ ይፈቀድልናል ወይ? ከውጪ አድናቂዎቻችን ፊልም ሊሰሩልን የሚመጡት እኛ እንደግብጻውያን ጣህሪር አደባባዮቻችንን ቀን ተሌት በማጨናነቅ ነጻነታችንን ስናፋጥን ብቻ ነው። ከትንሹ በየአዳራሹ የምንደልቀው የነጻነት ዕጦት ድቤ እስከ ታላላቅ የአደባባይ ተቃውሞ ነጋሪቶቻችን ድረስ ምን ያህሉ የገዢዎቻችንን ጆሮ በሱት? ምን ያህሉ የአለም አቀፍ ተቋማት ሚዲያዎችን ቀልብ ሳበ?
የ አንድ ቀን ጩኸት ብቻ ሆኖ ማለፉ ቆጭቶን ስልት እንድንቀይር ግድ ይለናል።
በውጭ አገራት
የኢትዮጵያውያን ተቃውሞ
አንደኛ በተለያዩ የውጪ ሃገራት ያሉ ወገኖች ዲሞክራሲያዊነትና ተሰሚነት በሚያመዝንባቸው የምዕራቡ ዓለም መንግስታት ፊት ቀርበው
የሃገርቤቱን ብሶት በይበልጥ ህግን ጠብቀው ሊያስተጋቡ ይገባል። ሲቀጥል በአሁኑ ወቅት ግን ወያኔ ውጭ ሃገርም ድረስ በመምጣት ኢትዮጵያውያንን
በመሰለል በማፈን ላይም ስለሚገኝ የሃገርቤት ወገን ብሶትን ብቻ ሳይሆን የሰው ሃገር ድንበር ጥሶ ማጭበርበር የጀመረውን ወያኔ
ማጋለጥ የስደተኞች ግዴታ ሆኗል። ለምሳሌ በአሜሪካና በ እንግሊዝ ያሉ የፖለቲካ አቀንቃኞቻችንና ጋዜጠኞቻችን ኮምፒተር ወያኔ ከአውሮፓ በገዛው ፊን ፊሸርና ፊንሰፓይ ቫይረስ እንደተሰለሉ ሁሉ ነገ
በጀርመን በአውስትራሊያ ወዘተ ያሉ ወገኖች በወያኔ ነፃነታቸውን ያለመገፈፉ ያለመሰለሉ ዋስትና ምንድን ነው? በተለይም ፊንፊሸርን የሚሸጠው ጀርመን የሚገኝውን ጋማ የተባለ የሶፍትዌር
አምራች ለአምባገነን መንግስታት መሸጡን መቃወም እዚሁ ካሉ ኢትዮጵያውያን ይጠበቃል። ከሃገር ውስጥ አማርሮ እንዳሰደደን ሁሉ
በሰው ሀገር ከሚያሳድደን ወያኔ ደህንነታችንን ጠብቁልን በማለት የወያኔን መሰሪነት በጎን ለውጭ ሀገር መንግሰታት ማሳሰብ
ይቻላል። በሶሰተኛነትና በዋነኛነት የትግሉ ሜዳ መሆን ያለበት በሃገርቤት ስለሆነ የኢንተርኔትና ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የፌስ ቡክ
አብዮት የሚባለውን የአረብ ፀደይ አብዮት ለሀገራችን ህዝብ ማስገንዘብና መደገፍ አለብን ። በተጨማሪም በኢትዮጵያ የታገዱ የማይሰሙ አነቃቂ ሚዲያዎችን ሰብረው ሊያዩ ሊያውቁ የሚችሉበትን የተለያዩ መንገዶቸ
መጠቆም ያስፈልጋል።
ለማጠቃለል
የቱኒዚያ የግብጽ የ ዩክሬን ህዝብ መጀመሪያ ለሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ይጠይቁና ሲቀጥል ወደ ህዝባዊ አመጽ አምርተው ከሚሰሰሰቡበት አደባባይ ላፍታም ውልፍት ሳይሉ ስለታገሉ መሪዎቻቸውን ቀይረው የየጊዜውን ነፃነት ምን እንደሚመስል አወዳድረዋል።እኛ 40
ዓመት በላይ ያወዳደርነው አለመታደል ሆኖ ክፉና አምባገነን ገዠዎችን ነው
ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በሃገራችን ለመገንባት ከሰላማዊ ሰልፍ እና ከ ህዝባዊ አመጽ በተጨማሪም ህዝባዊ አድማ እና ህዝባዊ እምቢተኛነት ልንከተለው የሚገባን ቀላል የትግል ስልቶች ናቸው ።
ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት የሚያካሂዷቸው ሰልፎች ላይ ፍትሃዊ መልስ ካላገኙ ከ አደባባይ ባያነቃነቁ መንግስት ያልተለመደ ነገር ስለሚሆንበት ይደነግጣል፥አለም አቀፍ ትኩረትም እናገኛለን። ከተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች ይልቅ አንዱን ሰልፍ ተቀጣጣይ በማድረግ ወያኔ ኢህአዴግን ማስወገድ
ይቻላል።
ኢትዮጵያውያን በውጪ አገር ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው፥ መንግስት አንቀጥቅጥ ምክክር በየአዳራሹ ማሳማታቸውን እንኩዋን ሌላ አለም አቀፍ ትኩረት ሊያገኝ በዛው ሃገር ያሉ ኢትዮጵያዉያን ጥሪውን የማይሰሙበት ሁኔታ አለ።የተቀናጀ የተደራጀ ፖርታል ማስፈለጉ የሚሰመርበት ጉዳይ ሆኖ በሰው ሃገር
ምላሸ እስከምናገኝ ሳንታክት ማሳሰብ አስፈላጊ ነው።
No comments:
Post a Comment