-45 አመቱ ጎልማሳ አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግላቸው ከቆየ በሁዋላ ትናንት አርፈዋል። የአቶ አለማየሁን እረፍት ተከትሎ የኦህዴድ አባላትና የክልሉ ነዋሪዎች ስለአሟሟታቸው ሚስጢር የተለያዩ መላምቶችን እያቀረቡ በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። አብዛኛው ህዝብ ግለሰቡ በተቃዋሚዎቻቸው ተመርዘው መሞታቸውን በማመን የአሟሟታቸው መንስኤ እንዲታወቅ ይፈልጋል።
የኦህዴድ አባላትም በጉዳዩ ላይ እየተወያዩ ሲሆን ችግሩ በአመራሩና በአባላቱ መካከል መከፋፈል እንዳይፈጥር አንዳንድ የድርጅቱ አባላት መግለጫ እንዲሰጥ ግፊት እያደረጉ ነው። የፕሬዚዳንቱ የግል ጠባቂ የሆነው ግለሰብ በተመሳሳይ በሽታ ላይ መገኘቱ ለጥርጣሬው በር እንደከፈተ ለማወቅ ተችሎአል። አቶ አለማየሁ የኦህዴድ ሊቀመንበርነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ሳይለቁ እንደለቀቁ ተደርጎ የተለቀቀው ዜናም መነጋገሪያ መሆኑን ከድርጅቱ አባላት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ኢሳት ዜና :
በጣም የሚያሳዝነው የህወሃት አሻንጉሊቶች የሚሞቱት ሁለት ግዜ መሆኑ ነው። በቁም እየሞቱ ስለሚኖሩ የመጨረሻው ሞታቸው ብዙም አስደንጋጭ አይሆንም። የአቶ አለማየሁ አቶምሳ አሟሟትን በተመለከተ የታዘብኩት መርዶውን የመንግስት ሚድያዎች ከታይላንድ በፍጥነት ማድረሳቸውን ነው። አቶ መለስ ሲሞቱ መርዶውን በግዜ ያረዳውን ኢሳትን ውሸታም እያሉ ህዝቡን ስድስት ሳምንታት ያለአግባብ አስጠበቁት። ህውሃቶች ለዚህም ያዳላሉ!!!
በፎቶው ላይ ከሚታዩት "መሪዎች" መሃል የቀሩት ሁለቱ በቁም የሞቱት ብቻ ስለሆኑ ሁሉም ሞተዋል ማለት ነው። ይህንን የነቀዘ ስርአት ሳይሸት ተረባርበን ቶሎ እንቅበረው።abebe gelaw
በፎቶው ላይ ከሚታዩት "መሪዎች" መሃል የቀሩት ሁለቱ በቁም የሞቱት ብቻ ስለሆኑ ሁሉም ሞተዋል ማለት ነው። ይህንን የነቀዘ ስርአት ሳይሸት ተረባርበን ቶሎ እንቅበረው።abebe gelaw
No comments:
Post a Comment