የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማይቱ መሰረታዊ ችግሮች እየተባባሱ ከመምጣት ውጪ ለውጥ ማሳየት ባለመቻላቸው ለዚህ ተጠያቂ መሆን ያለበትን የከተማይቱን አስተዳደርና ገዢውን ፓርቲ የሚቃወም ‹‹የእሪታ ቀን››በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28/2006 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደርግ አስታውቋል፡፡የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል የፓርቲውን ደብዳቤ ተቀብሏል በዛሬው እለት የፓርቲው ተወካዩች ለአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቅ ክፍል ስለ ሰልፉ የሚገልጽ ደብዳቤ በማስገባት ተመልሰዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉ በተያዘለት ቀነ ገደብ የፓርቲው ጽ/ቤት ከሚገኝበት ቀበና በመነሳት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚጠናቀቅ የአዲስ አበባ አንድነት ህዝብ ግኑኝነት አቶ ያሬድ አማረ አስታውቀዋል፡፡
- See more at: http://www.fnotenetsanet.com/?p=6496#sthash.IZARPn7R.dpuf
No comments:
Post a Comment