ኢሳት ዜና :-
በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ በእናሸንፋለን ቀበሌ ከአበባ እርሻና ከውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የሚታሰሩ አርሶደሮች ቁጥር መጨመሩን አካባቢው ሰዎች ገልጸዋል።
በወረዳው ዋና ከተማ በመርአዊ ከተማ አሁንም የሚታሰሩ አርሶደአሮች መኖራቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ታዳጊ ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው እንዲታሰሩ መደረጉን ገልጸዋል።
የመኢአድ የመርአዊ ተወካይ አቶ ስማቸው ምንችል ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ወደ አካባቢው በመሄድ በብዛት የታሰሩትን ታዳጊዎች ሁኔታ እንዲከታተሉ ጠይቀዋል።
ከሳምንት በፊት ለአበባ ምርት ተብሎ የሚቆፈረውን የውሃ ጉድጓድ ፕሮጀክት የተቃወሙ አርሶ-ደሮች በጉድጓድ መቆፈሪያ ማሽኑ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ ከባህርዳር የመጡት የፌደራል ፖሊሶች በአርሶ አደሮች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስደዋል። አካባቢው አሁንም በፖሊስ የተከበበ ሲሆን በርካታ ወጣቶችም መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የወረዳውን ባለስልጣናት በስልክ ኔትወርክ ችግር ምክንያት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

No comments:
Post a Comment