Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 19, 2014

ነጋዴዎች በግብር ስርአቱ መማረራቸውን ተናገሩ ESAT

ነጋዴዎች በግብር ስርአቱ መማረራቸውን ተናገሩ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

 ነጋዴዎች ምሬታቸውን የገለጹት ሰሞኑን በግብር አከፋፈል ዙሪያ ላይ በባህር ዳር ከተማ የኢፌዴሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ በአማራ ከልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት አማካኝነት የተካሄደ ጥናት የቀረበ ሲሆን፣ በጥናቱምው በግብር ሰብሳቢውና በግብር ከፋዩ መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተመልክቷል፡፡
የግብር ስርአቱ አገልግሎት አሰጣጥ የፍትሀዊነት ችግሮች ያሉበት በመሆኑ በነጋዴውና በመንግስት መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር አድርጓል። የመንግስት አካላት የሚወስዱት እርምጃ ፈተና እንደሆነባቸው የተናገሩት ነጋዴዎች በ25 ብር ቅጣት ለአመት የታሰሩ ነጋዴዎች አሉ ብለዋል።
ባጠቃላይ በግብር ምክንያት በመላ ሃገሪቱ ባሉ ትልልቅ ከተሞች 7 ሺ 943 ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ አንድ በቆዳ ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሀብት አግባብ ባልሆነ መንገድ 2 ሚሊዮን ብር የግብር ወለድ እንዲከፍሉ መገደዳቸውን ገልጸዋል ።
የፍትህ ተቋማት መንግስት ይዞ የሄደውን ብቻ የሚወስኑ፣ የነጋዴውን ጉዳይ ዘወር ብለው የማያዩ በመሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔ ለማግኘት መቸገራቸውንም ነጋዴዎች ገልጸዋል ።
በግብር አስገቢ መ/ቤቱ ብቻ ሳይሆን በግብር ከፋዩ በኩልም የሚታዩ ችግሮችን የዳሰሰው ጥናቱ ግብርን ለመክፈልና በዝምድናና በትውውቅ ለመስራት መሞከር እንዲሁም ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ለማጋለጥ አለመፈለግ ይታይባቸዋል ብሏል፡፡
ሂሳብ አዋቂዎች በመድረክ ላይ እንደተናገሩት ደግሞ በግብር ስርዓቱ ላይ የወጡ አዋጆችና ደንቦች በተሟላ መልኩ አለመገኘታቸው ችግር እየፈጠረ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials