(ፍኖተ ነፃነት) በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እንዲሁም ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣ በነርሱ አነሳሽነት፣ ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አደረጉ።
ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር እንደተነጋገሩ የገለጹት የአዉሮፓ ሕብረት ባለስልጣናት፣ የአንድነት ፓርቲ በጠራዉ የሚሊዮኖች ድምጽ ሁለተኛ ዙር ንቅናቄ እንዳሳሰባቸው በመገለጽ፣ አንድነት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ዙሪያ፣ ፓርቲው ፍቃደኛ ከሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው፣ ጠይቀዋል።
የአንድነት ፓርቲ ወክለው ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር የተነጋገሩት ሊቀመንበሩ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉና የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌው በበኩላቸው ያሉትን ሁኔታዎች ለማስረዳት ሞክረዋል።
አንድነት አሁን የሚያደርገው የሚሊዮነሞች ንቅናቄ ከዚህ በፊት ከተደረገው የቀጠለ እንደሆነ ያስረዱት የአንድነት አመራር ፣ ፓርቲዉ አዲስ አበባ ጨምሮ በ17 ከተሞች ፣ በፍትህ እና በላንድ ሪፎርም ዙሪያ ፣ ከሕዝብ ጋር ዉይይቶችን እንዲሁም ሰላማዊ ስለፎች እንደሚያደርግ ገልጸዋል። አንድነት ከዚህ በፊት ባደረጋቸዉ በርካታ ሰልፎች አንዳች አይነት በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት የአንድነት አመራር አባላት ፣ ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ እንደሚሆኑ በማስረዳት ፣ አንድነት አገር አቀፍ መዋቅሩን እያሰፋ እንደሆነም ለማሳየት ሞክረዋል።
የአዉሮፓ ሕብረት ተወካዮች፣ አንድነት ይዞት የተነሳዉ የመሬት ጥያቄ ተገቢና ወቃታዊ፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም የሚያመጣ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ በመጪው የ2010 ምርጫ ዙሪያ አንድነት ያለውን አቋም እንዲያስረዳቸው ጠይቀዋል። “ለምርጫ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገን ነው። በሁሉም ክልሎች ለፌዴራልም ሆነ ለክልል ተወዳዳሪዎች ከወዲሁ እያዘጋጀን ነው