Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 19, 2017

Saudi Arabia Releases Most Corruption Detainees After Settlements Reached

by JOHN HAYWARD
A statement from Saudi Arabia’s public prosecutor on Tuesday indicated that most of the suspects swept up in the recent anti-corruption crackdown will be released after reaching settlements with the government.
A sizable number of detainees, however, remain in detention, and some of those will be prosecuted for their offenses.
The statement said “320 people had been subpoenaed to provide information about alleged graft while 159 remain in detention and ‘a number’ of them have been referred for judicial action,” according to Reuters. At one point, the bank accounts of some 2,000 suspects had been frozen, but the number is down to 376.
“The allegations, which could not be verified, include kickbacks, inflating government contracts, extortion, and bribery,” the Reuters report adds.
The cash settlements reached by the accused are sizable indeed, beginning with a $1 billion repayment by the most senior royal swept up in the crackdown, Prince Miteb bin Abdullah. The total recovered from those suspected of graft could reach $100 billion. The Saudi government has said the recovered funds will be invested in “economic development projects.”
The deal worked out with the detainees, largely held at the luxurious Ritz Carlton Hotel in Riyadh, evidently involves dropping the charges against them and securing a royal pardon in exchange for handing over the allegedly stolen funds without too much of a fuss. Most of those who settle will be permitted to remain anonymous.
Crown Prince Mohammed bin Salman stated last month that only about one percent of the detainees have been able to prove themselves innocent of the charges, while only four percent have expressed a desire to fight their corruption accusations in court. Reuters notes one of the accused who seems prepared to contest the charges is a dual French and Saudi national who has inquired about securing consular protection.
Forbes notes the so-called “Supreme Anti-Corruption Committee” of Saudi Arabia has named four prominent billionaires among the detainees: “Prince Alwaleed bin Talal, Saudi-Ethiopian investor Mohammed Al Amoudi, media baron and conglomerate head Saleh Kamel and shopping mall tycoon Fawaz Alhokair.”
Prince Alwaleed, who is among the richest and most internationally famed men in Saudi Arabia, is worth about $16 billion all by himself. Or at least he was because his settlement offer is said to involve handing over most of his assets and a lifetime of house arrest. Alwaleed is rumored to have refused this unappealing offer and signaled a desire to contest his charges in court, a trial that would likely dominate Saudi news for months and create the kind of economic uncertainty the monarchy is desperate to avoid.
Saudi Minister of Commerce and Investment Majid bin Abdullah al-Qasabi told Reuters on Wednesday that he believes the primary wave of arrests is completed but added the government “will not keep its mouth shut when it sees a corrupt case” in times to come.
Qasabi added that Saudi Arabia’s economic reforms are on track, including a $300 billion privatization program, with significant milestones expected in 2018 and 2019. Foreign investment is to be a major element of the Kingdom’s shift away from an oil economy, as envisioned by the Crown Prince. Qasabi essentially conceded that instability from the anti-corruption crackdown is viewed as a necessary price to pay for convincing investors that Saudi Arabia will be a safe place for their money in the future.
“They’re worried about if this will be the end of it, or where it will stop,” he said. “But they all think this will be good for the country, because the country’s leadership stood visibly to fight corruption, and ultimately this will be a level playing field for everybody.”
Alaco director Ambrose Carey writes at Business Insider that the great anti-corruption drive was largely an attempt by the Saudi government to claw back huge amounts of money frittered away by self-indulgent royals during the heyday of the oil industry, funds that will now be desperately needed to lubricate the Kingdom’s transition to a post-oil economy and shore up defenses against the great regional threat of Iran.
“The fall in the price of oil – the kingdom’s main source of revenue – has led to a huge budget deficit, which stood at $79 billion in 2016. The government has had to use foreign reserves to help cover the revenue shortfall, with the former shrinking by about a third over the last three years. The recession has forced MBS to rein back public spending, alarming cosseted Saudis long accustomed to cradle-to-grave subsidies,” he notes.
But Carey argues this financial agenda is unlikely to succeed, in part because so much of the royal grift has been spent or sheltered overseas, putting skeptical financial advisers and business partners overseas in charge of the assets the Saudi government wants to recover.
“So, in all likelihood, MBS will struggle to generate the money he needs. Worse still for him, his actions could have deleterious consequences for the economy. While the acquisition of assets and cash is likely to play well with ordinary Saudis weary of corruption amongst the royals and the business elite, it may unnerve already jittery foreign investors whose engagement is critical to the Crown Prince’s economic plans,” he concludes, adding the kicker that, given the state of Saudi finances and the challenges facing the Kingdom, it might have been Crown Prince bin Salman’s best play anyway. Bold and visionary as he seems, rash and impulsive as he might be, the 32-year-old heir to the throne came along about 32 years after all the easy options and solid plans expired.

Sunday, December 17, 2017

ከወዲሁ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያሳየን ታላቁ የዓለም ዋንጫ – ሩሲያ world cup 2018







ከዓመታት የማጣሪያ ውድድሮች በኋላ በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የ2018 የዓለማችን ታላቁ የእግር ኳስ መድረክ ሊጀመር የወራት ዕድሜ ቀርቶታል። ከወዲሁም ያልተጠበቁ ክስተቶችን ማመልከት ጀምሯል። በፍልሚያው ሜዳ የተጠበቁት ሲቀሩ፤ ያልተጠበቁት የተሳትፎ ትኬት ቆርጠዋል። የመድረኩ ድምቀቶች ብርቱካናማዎቹ ሆላንዶች እና ጣሊያኖች በአይስላንድ እና በፓናማ ተተክተዋል።

በመድረኩ በአምስት አገራት የምትወከለው አህጉራችን አፍሪካም ብትሆን አብዛኞቹን ተወካዮቿን ቀይራለች። ከአራት ዓመት በፊት በነበረው መድረክ በጋና፤ ካሜሮን፤ ኮትዲቯር፤ ናይጄሪያና አልጄሪያ የተወከለችው አፍሪካ፤ ከአራት ዓመት በኋላ ናይጄሪያዎችን አስቀርታ አራቱን ቀይራለች። የተሳታፊዎቹን 32 አገራት አስቀድሞ ያስተዋወቀን የዓለም ዋንጫም ከቀናት በፊት ተሳታፊ ብሄራዊ ቡድኖቹን በምድብ ከፋፍሎ የመጀመሪያ ዙር ተፋላሚዎቻቸውን ይፋ አድርጓል።

በምድብ አንድ

በፊፋ የእግር ኳስ ደረጃ 65ኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙትና የዓለም ዋንጫው አስተናጋጆች ለሆኑት ሩሲያዎች ከምድባቸው በጊዜ መሰናበት ከምንም በላይ የማይዋጥ ነው። እናም አንድ ጨዋታ መሸነፍ የሚያስከፍለውን ዋጋ ጥንቅቀው ያውቁታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩበትን የፖለቲካ አቅምና አቋም በስፖርቱም መስክ ማሳየት ይፈልጋሉ። ለዚህ ዓላማቸው ተፈፃሚነትም ልምድ ያላቸውን አላን ድዛጎኤቭ፤ ፊዮዶር ስሞሎቭ የመሳሰሉ ኮከቦች ላይ ተስፋ ጥለዋል። ለውድድሩ ዝግጅት የሰጡትን ትኩረት በእግር ኳሱ ፍልሚያ መድገም ከቻሉም ታሪክ ይፅፋሉ።

ከጣሊያኑ 1990 የዓለም ዋንጫ ወዲህ ዓመታትን ቆዝመው ዳግም ወደ ታላቁ መድረክ የተመለሱት የአፍሪካ ተወካዮቹ ግብፆችም ቢሆኑ በሩሲያው መድረክ ያልተጠበቀ አስደማሚ ታሪክ መፃፍ ይፈልጋሉ። «ግብፃዊው ሜሲ» የሚል ቅፅል ከተሰጠው ውድ ልጃቸው መሃመድ ሳላህና ከአርሴናሉ ኮከብ መሃመድ አልኒኒ ብዙ ተዓምር ይጠብቃሉ።

በሉዊስ ሱዋሬዝ ልዩ ክስተቶች የምትታጀበው ኡራጓይ ከባርሴሎናው ኮከብ በተጓዳኝ በፓሪሴን ጄርሜኑ የጎል አውራ ኤዲሰን ካቫኒ ላይ ዕምነት ጥላለች። ከ1950 ወዲህ ዋንጫ ማንሳት ያልሆነላቸው ኡራጎዮች በሩሲያ ምድር የዋንጫ ረሃባቸውን ለማስታገስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም።

እግር ኳስ ሲነሳ እምብዛም ስሟ አብሮ የማይነሳውና በቀድሞው የአርጀንቲና አሰልጣኝ ኤድጋርዶ ባውዛ የምትመራው የመካከለኛው ምስራቅ አገር ሳዑዲ ዓረቢያ በሞስኮ ሰማይ ስር ያላትን አቅም ለማሳያት ዝግጅቷን አጠናቃለች። ከዚህ ምድብ ኡራጋይና ግብፅ በኮከብ ተጫዋቾቻቸው ብቃት ታግዝው ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ ተገምቷል። ክብር የሚሰጠው የመክፍቻ ጨዋታ በሳዑዲና ሩሲያ መካከል ይደረጋል።

ምድብ ሁለት

የ2016 የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ፖርቹጋል የአውሮፓ ኃያልነቷን በዓለም አቀፍ ደረጃ መድገም አቅዳለች። ይህን ኃላፊነትም ለዓለማችን ኮከብ የግብ ማሽን ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአደራ ሰጥታለች። ተጫዋቹ ከሰሞኑ እያሳየ በሚገኘው ደካማ አቋም ከቀጠለ ግን የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹ የሚፈለጉት ሳይሆን የማይፈልጉት መሆኑ አይቀሬ ነው።

ስፔኖች ከስምንት ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካ የፃፉትን ወርቃማ ታሪክ በሩሲያ ምድር ዳግም ማድመቅ ይፈልጋሉ። በወጣት ተጫዋቾቿ ተወክላ ወደ ሞስኮ የምታቀናው ስፔን፤ ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ካላቸው አገራት አንዷ ብትሆንም የቀድሞው አስፈሪነቷ ግን አሁን ያለ አይመስልም።

በ1978 በዓለም ዋንጫው መድረክ ጨዋታን በማሸነፍ ከአፍሪካ ቀዳሚ የመሆን ከብር ያገኙት የሰሜን አፍሪካዎቹ ድንቅ ልጆች ሞሮኮዎች፤ የዓለም ዋንጫው ልዩ ክስተት እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ሞሮኮዎች በመጨረሻው የምድብ የማጣሪያ ጨዋታ በጠንካራ ስብስብ የተዋቀረው የኮትዲቭዋር ቡድን አሸንፋው ሩሲያ የሚወስደውን ትኬት መቆረጣቸው ይታወሳል። የዚህ ምድብ ሌላኛዋ አገር ኢራን ናት። ወደ ዓለም ዋንጫ ስታልፍ የአሁኑ አምስተኛዋ የሆነው ኢራን ከዚህ ቀደሙ የተሻለ አዲስ ውጤት ታስመዝግባለች ተብሎ አይጠበቅም። የታላቁን መድረክ የመጀመሪያ ፈተና ማለፍ ስለመቻሏም ከራሳቸው በቀር ማንም አይተማመንም።

ከዚህ ምድብ ፖርቱጋልና ስፔን በቀላሉ ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን የሁለቱ አገራት ጨዋታም የመድረኩ ትልቅ ጨዋታ እንደሚሆን ታምኖበታል። በሁለቱ አገራት ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶም ከግማሽ በላይ ከሚሆኑ የሪያል ማድሪድ ቤት ጓደኞቹ ጋር ለተቃራኒ ዓላማ ይፋጠጣል። ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ሰርጂዎ ራሞስም ሮናልዶን ለማቆም አለኝ የሚለውን ብቃት አሟጦ ይጠቀማል።

ምድብ ሦስት

የ1998 የዓለም ዋንጫ አዘጋጅና የዋንጫው ባለቤት ፈረንሳይ ባለተሰጥኦ የወጣት ተጫዋቾችን የያዘ ስብስብ ይዛ ሞስኮ ትደርሳለች። በሰላማዊው የፍልሚያ መድረክ ለማንቸስተር ዩናይትዱ ፖል ፖግባ፣ ለቼልሲው የመሃል ሜዳ ሞተር ንጎሎ ካንቴ የመሃል ደጀን ኃላፊነቱን ስትሰጥ፤ የአትሌቲኮ ማድሪዱ አንቷን ግሪዝማን ደግሞ የግብ ኃላፊነቱን ይረከበዋል።

አሰልጣኝ ዲዲየር ዴሻም ብቁ ተፎካካሪና አሸናፊ ለመሆን የተጫዋቾችን የግል ብቃት ወደ ቡድን የማምጣት ከባድ ኃላፊነት ተጥሎበታል። የዘንድሮ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ዋንጫ ካላነሳም መቼም አያነሳም የሚል አስተያየት ከወዲሁ መሰጠት ጀምሯል።

እ ኤ.አ ከ2010 በኋላ በዓለም ዋንጫው ስትሳተፍ የመጀመሪያዋ የሆነችው ዴንማርክ ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ አምስተኛ ተሳትፎዋ ነው። ዴንማርኮች በብራዚል ከውድድሩ በወጡበት የ1998ቱ የዓለም ዋንጫ እስከ ሩብ ፍፃሜ መጓዝ መቻላቸው ይታወሳል፡፡ ዘንድሮ ከዚህ የተሻለ ታሪክ ለመሥራት ለቶተንሃሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰንን ከባድ ኃላፊነት አስረክባለች።

የዘንድሮው የአውስትራሊያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ ሲሆን በአጠቃላይ ግን አምስተኛዋ ነው። ጥሩ ተሳትፎ አድርጋበታለች የሚባለው በ2006 በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ ሲሆን፤ ከመጨረሻዎቹ 16 ቡድኖች ገብታ ከጣሊያን ጋር ባደረገችው ጨዋታ በመጨረሻዎቹ ደቂቃ በተሰጠባት ፍፁም ቅጣት ምት ተሸንፋ የወጣችበት ነው።

የደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ በሞስኮው ፍልሚያ የሎኮሞቲቭ ሞስኮውን ጨዋታ ቀያሪ ጀፈርስን ፋርፋንን ተስፋ አድርጋለች። በዚህ ምድብ የዓለማችንን ውድ ተጫዋች ይዛ መድረኩን የምትቀላቀለው ፈረንሳይ በኮከቦቿ ተዓምር ከምድቧ ማለፏ ጥርጥር አይኖረም። ዴንማርኮችም ለሁለተኛነት ሰፊ ግምት አግኝተዋል።

ምድብ አራት

በዚህ ምድብ የአህጉራችን ተወካይ ናይጄሪያ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን መሆን ከቻሉት በኮከቦች ስብስብ ከተዋቀሩት አርጀንቲናዎች ትፋጠጣለች። ከ1994 የአሜሪካ የዓለም ዋንጫ ወዲህ አንድ የዓለም ዋንጫ ብቻ ያመለጣቸው ንስሮቹ፣ በማጣሪያ ጨዋታዎች የነበራቸው ያለመሸነፍ ጉዞ በሩሲያው ታላቅ እግር ኳስ መድረክ ይደግሙታል ተብለው እንዲጠበቁ አድርጓቸዋል።

ቪክቶር ሞሰስ፣ የአርሴናሉ አሌክስ ኢዮቢ እና ሌሎችም ተጫዋቾች ያካተቱት ንስሮቹ፤ በተለይም በምድብ ማጣሪያዎች በየጨዋታው በአማካይ ሁለት ግብ እያስቆጠሩ መምጣታቸው የማጥቃት አጨዋወታቸው ማሳያ ተደርጓል።

አርጀንቲና አንሄል ዲማሪያ፣ ሰርጂዮ አጉዌሮ፣ ሊዮኔል ሜሲ፤ ኩን አጉዌሩ፤ ጎንዛሎ ሄጊዌን እንዲሁም የጁቬንቱሱን ጨዋታ ቀያሪ ፓውሎ ዲያባላን በመሳሰሉ ኮከቦች ብትወክልም ወደ መድረኩ ለመምጣት በእጅጉ ተቸግራ መታየቷ በሩሲያው መድረክ ብዙም ግምት እንዳይሰጣት አድርጓል። ይሁንና አስፈሪ ቡድን መያዟ እርግጥ ነውና የዋንጫ ግምት የሚሰጧትም በርካታ ሆነዋል።

ሉካ ሞድሪች፣ ኢቫን ራኪቲች፣ ማሪዮ ማንዙኪች፣ ኢቫን ፔርሲችና ኒኮላ ካሊኒችን የመሳሰሉ በድንቅ ክህሎት የታገዙ ብቁ ተጫዋቾች ባለቤት የሆነችው ክሮሺያ የመድረኩ ክስተት ትሆናለች ተብሎ ትጠበቃለች።

የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ለአይስላንዶች የመጀመሪያ ተሳትፏቸው ነው። በኮከቦች ከተዋቀረችው አርጀንቲና ጋር የመጀመሪያ ጨዋታዋን የምታደርገው ትንሸ አገር ምንም እንኳን በሩሲያው መድረክ ብዙ ርቀት ትጓዛለች ተብሎ ባይገመትም መድረኩን መቀላቀሏ ብቻውን እንደ ስኬት ይቆጠርላታል።

ምድብ አምስት

የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ከየትኛውም ብሄራዊ ቡድን በላይ ለብራዚሎች የላቀ ዋጋ አለው። የአምስት ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ብራዚል፤ የቀደመ የእግር ኳስ ኃያልነት ተምሳሌትነቷን እና ከአራት ዓመት በፊት ራሷ ባዘጋጀችው መድረክ የደረሰባትን ሃፍረት ለመቀልበስ ሌላ ተጨማሪ ዓመት መጠበቅ አትፈልግም።

ኔይማር ጁኒየር፤ ጋብሬል ጀሱስ እና ፊሊፔ ኮቲንሆ የመሳሰሉ ምትሃተኛ ተጫዋቾችን የያዙት ቢጫ ለባሾቹ፤ በዓለም ዋንጫው እያንዳንዱ የማጣሪያ ጨዋታ ያሳዩትን አቅምና አቋም በዋናው ውድድር የሚደግሙት ከሆነ የፍላጎታቸውን እንደማያጡ ጥርጥር የለውም።

የማጣሪያ ጨዋታዎችን በብቃት አሸንፈው ወደ ዓለም ዋንጫ መግባታቸውን ካረጋገጡ አገራት አንዷ ስዊዘርላንድ ናት። አገሪቱ የውድድሩ ልዩ ክስተት ከሚሆኑ ክለቦች መካከል ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ስትሆን፣ ዤርዳን ሻኪሪ፣ ብሬል ኤምቦሎ፣ ግራኒት ዣካ፣ የተለየ አቋም ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃሉ።

ከዚህ ምድብ ኮስታሪካና ሰርቢያ ዝቅተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል። ብራዚልና ሲውዘርላንድ የታላቁን መድረክ የመጀመሪያ ፈተና በማለፍ ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የሊቨርፑሉን ፊሊፕ ኩቲኒሆን ከአርሴናሉ ግራኒት ዣካ የሚያፋጥጠው የሁለቱ አገራት ጨዋታም ከወዲሁ ተጠባቂ ከሆኑት ትርታ ተመድቧል።

በምድብ ስድስት

ከአራት ዓመት በፊት በድንቅ ቡድናዊ ጥምረትና ሜሱት ኦዚልን በመሳሰሉ ድንቅ ተጫዋቾች ግላዊ ብቃት ዋንጫውን ማነሳት የቻሉት የወቅቱ የዓለማችን ቁጥር አንድ ብሄራዊ ቡድን የሆኑት ጀርመኖች፤ ያለፈውን ታሪክ ዘንድሮም መድገም ይፈልጋሉ። ቶማስ ሙለርና ቶኒ ክሩስን በመሳሰሉት ተጫዋቾች ጠንካራ ቡድን መመስረታቸውን ዋቢ በማድረግ ያለፈውን ድል እንደሚደግሙት የማይጠራጠሩት ከሚጠ ራጠሩት ይልቃሉ።

ሜክሲኮ ከዚህ ቀደም በነበሩት የዓለም ዋንጫዎች የነበራትን ምርጥ ተፎካካሪነት አሁንም እንድትጠበቅ ያደርጋታል። የውድድሩ ድምቀትና ክስተት እንደምትሆን የማትጠረጠር ሌላኛዋ አገር ስውዲን ናት። ለዘጠነኛ ተከታታይ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ጨዋታ መሳተፏን ያረጋገጠችው የእስያ ዞን ተወካይዋ ደቡብ ኮሪያ የቶተንሃሙን ኮከብ ሰን ሄዩንግ ሚን እና ሌሎችም ተጫዋቾች ይዛ ለተቃራኒ አገራት ፈታኝ እንደምትሆን ይጠበቃል። ጠንካራ ምድብ ከተባለው ከዚህ ምድብ ጀርመኖች በቀላሉ እንደሚያልፉ ጥርጥር የለውም። ከሲውዲንና ከሜክሲኮ ማን ያልፋል የሚለውን ግን መገመት አዳጋች ሆኗል።

ምድብ ሰባት

ይህ ምድብ ምርጥ ጨዋታ ይታይበታል ከሚባሉ ጨዋታዎች መካከል ተከታይ እንጂ ቀዳሚ የለውም። በጋሬዝ ሳውዝጌት የሚመሩት ሦስቱ አናብስት እንግሊዞች በማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ዓለም ዋንጫው ለመግባት ያሳዩት አቋም እጅግ ተደንቆላቸዋል። በቶተንሃሞቹ ጨዋታ ቀያሪዎች ሃሪ ኬንና ዴሌ አሊ ፊት አውራሪነት የሚመሩት አናብስቶቹ፣ ከ 1966 በኋላ የዓለም ዋንጫውን ዳግም ወደ ለንደን ይዘው መመለስ ከቻሉ ለቡድኑ አባላት በርከት ያለ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል።

ወደ ሩሲያ ከሚያቀናው የቤልጄም ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ በእንግሊዝ ምድብ የሚጫወቱ 19 ጨዋታዎች አሉ። ዓለም በማግባትና ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የመሰከረላቸው ኬቪን ደ ብሩይነ፣ ኤዲን ሃዛርድ እና ሮሜሉ ሉካኩ የመሳሰሉ ቁልፍ ተጫዋቾችን ይዛ ወደ ሞስኮ የምትገባው ቤልጄም፣ ለሦስቱ አናብስት ፈታኝ እንደምትሆን ጥርጥር የለውም።

ቱኒዚያ በዓለም ዋንጫ ስትሳተፍ የአሁኑ አምስተኛዋ ነው፤ የአሁኑ ብሄራዊ ቡድኗ ስብስብ በዋናነት ከአገር ውስጥ ክለቦች የተውጣጣ ነው። የአፍሪካዋ ተወካይ በጠንካራ ምድብ ውስጥ እንደ መገኘቷ በርካታ ወገኖች ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን እንዲጠራጠሩ ሆነዋል። ከዚህ ምድብ ዝቅተኛ ግምት ያገኘችው ፓናማ ሆናለች።

ምድብ ስምንት

በሩሲያ የዓለም ዋንጫ ልዩ ክስተት እንደሚሆኑ ከሚጠበቁ ብሄራዊ ቡድኖች መካከል ሴኔጋሎች ይካተታሉ። የምዕራብ አፍሪካዋ አገር በ2002 በእነ አል ሃጂ ዲዩፍ ፊት አውራሪነት እየታገዘች የሠራችው ገድል ሁሌም የሚታወስና ታሪክ ተሻጋሪ ነው። የሊቨርፑሉን ፈርጣማ ግብ አዳኝ ሳዲዮ ማኔ ድንቅ ብቃት በሩሲያ ከሚደምቁት አፍሪካዊ አገራት አንዷ የሆነችው ሴኔጋል፤ የዘንድሮ ስብስብም ጥንካራ እንደሆነ በበርካታ ወገኖች ተመስክሮለታል።

ሃሜስ ሮድሪጌዝ፣ ራዳሜል ፋልካኦ፣ ሁዋን ኳድራዶ፣ ዬሪ ሚና እና ዳቪንሰን ሳንቼዝን ይዛ ወደ ሞስኮ የምታቀናው የደቡብ አሜሪካዋ የኮከቦች መፍለቂያ ኮሎምፒያውም የሞስኮ ሌላ ድምቀት ናት። አውሮፓዊቷ ፖላንድም ብትሆን ቀላል ግምት የሚሰጣት አይደለችም። የባየር ሙኒኩ አስፈሪ አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ አገር በዓለም ዋንጫው ብዙ ርቀት መጓዝ እንደምትችል በርካታ ወገኖች ጥርጣሬ ውስጥ አልገቡም።

ሌላኛዋ የዚህ ምድብ ተካፋይ የሆነች አገር ጃፓን ናት። ምንም እንኳን በእግር ኳስ የሚሆነው ባይታወቅም፤ የኤሲያ ተወካይዋ በመድረኩ ታሳያለች የሚባለው ውጤት ዝቅተኛ ነው፡፡ የታላቁ መድረክ የመጀመሪያ ፈተና የማለፋቸው ነገር ያጠያይቃል። ቀላል ምድብ እንደሆነ በተለየው በዚህ ምድብ ኮሎምፒያ እና ሴኔጋል ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ ከወዲሁ መገመት ጀምሯል።



ታምራት ተስፋዬ

Ethiopia faces social media blackout after new ethnic unrest

Addis Ababa – Ethiopia faces a social media blackout as clashes intensify between ethnic groups in various parts of the country.
Facebook and Twitter were down on Tuesday after reports emerged of killings on Monday by security forces in the Oromia region.
Oromia regional spokesperson Addisu Arega said the violence in Chelenqo town killed six people and was being investigated. On Facebook he called the victims “innocent civilians.”
The Addis Standard news site reported 15 killed, including women and children. The Associated Press was not able to independently verify the reports.

Saturday, December 16, 2017

አስገራሚ!! ወላድ እናቶችን በነጻ ወደ ጤና ተቋም የሚወስደው ታክሲ ሹፌር በጎንደር



አስገራሚ!! ወላድ እናቶችን በነጻ ወደ ጤና ተቋም የሚወስደው ታክሲ ሹፌር በጎንደር

በሰሜን ጎንደር ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ





በሰሜን ጎንደር ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ መካሔዱ ታወቀ፡፡ ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት፣ በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ የህወሓትን አገዛዝ ሲቃወም ውሏል፡፡ በዚህ የስርዓት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ፣ በርከት ያለ ህዝብ ተገኝቶ ጸረ ህወሓት አመለካከቱን እንዳንጸባረቀ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ በዚሁ ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተስተጋቡ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሰልፉ ዓላማ ግን የህወሓት አገዛዝ እንዲያከትም የሚጠይቅ መሆኑን እማኞች ተናግረዋል፡፡

በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የንግድ መደብሮች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ሆነው መዋላቸውን የጠቆሙት የመረጃ ምንጮች፣ ሰልፉም እስከ አስር ሰዓት ገደማ ድረስ መካሄዱን መረጃዎቹ አክለው ጠቁመዋል፡፡ ህዝቡ የህወሓት አገዛዝ እንደመረረው የገለጸበትን ይኸው ሰልፍ ለመበተን የሞከሩ የጸጥታ አካላት ሳይሳካላቸው መቅረቱም ተሰምቷል፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ገለጻ ከሆነም፣ ህዝቡ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ድምጹን ሲያሰማ ነበር፡፡

ሰልፉን እንዲከታተሉ የታዘዙ የጸጥታ አካላት፣ ምንም እንኳን በሰልፉ ወቅት ሰልፈኛውን ባይተናኮሉም፣ ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ ግን በድብቅ የታሰሩ ወይም የተደበደቡ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ አገዛዙ አንዳንዴ፣ በአደባባይ የሚካሔዱ ሰልፎችን በዝምታ ከተመለከተ በኋላ፣ ህዝቡ ድምጹን አሰምቶ ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቆ፣ ብዙዎችን እስር ቤት እንደሚወረውር ከዚህ ቀደም ተስተውሏል፡፡ በዚህ ዓይነት መንገድ የተደበደቡ እና የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውም ይታወቃል፡፡ በአማራ ክልል ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎችን አካትቶ በሰፊው ተጠናክሮ ቀጥሏል፡

በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሔደ





በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ በዛሬው ዕለት የተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ በጨለንቆ ንጹኃን ዜጎች መገደላቸውን የሚያወግዝ ሆኖ ተስተውሏል በርካታ ህዝብ በተገኘበት በዚህ ተቃውሞ ላይ፣ ተማሪዎች በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችም መጽናናትን በመመኘት፣ ግድያውን የፈጸመውን የህወሓት አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውመዋል በነቀምቴ፣ ከተማሪዎች በተጨማሪም የአካባቢው ማኅበረሰብም አደባባይ በመውጣት፣ የጨለንቆን ግድያ እና ገዳዮችን በጽኑ አውግዟል ምንም ባላደረጉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው አስከፊ ግድያ እንዳሳዘናቸው የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በህወሓት አገዛዝ መተዳደር እንደማይፈልጉም ተናግረዋል በተመሳሳይ ሁኔታም በምዕራብ ወለጋ ማንዲ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ የተካሔደ ሲሆን፣ የሰልፉ ዓላማም በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዝ ነበር የአካባቢው ህዝብ በጨለንቆ ግድያ ላይ የተሳተፉ ወታደሮች እና ትዕዛዙን ያስተላለፉት አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በደሌ ከተማ ውስጥም የህወሓትን አገዛዝ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል የሰልፉ ተካፋይ የሆነው ማኅበረሰብ፣ እንደ ሌሎቹ ከተሞች ሁሉ በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ፣ የህወሓት አገዛዝ ስልጣን እንዲለቅቅ ጠይቋል መረጃዎች እንደጠቆሙት በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ጠንከር ያሉ እና አገዛዙ በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቅ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ በጨለንቆ ሜታ ወረዳ ውስጥ አንድ ሰው በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መገደሉ፣ የአካባቢው ህዝብ ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጣ አስገድዶት ነበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች የተፈጸመው ግድያ ያስቆጣው የጨለንቆ ህዝብ፣ በስፍራው በሚገኘው እና ህወሓት በሚያዘው መከላከያ ሰራዊት አማካይነት ተኩስ ተከፍቶበት አስራ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል::

BBN NEWS

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የተገደሉ ተማሪዎች አስከሬን ካልተመለሰ አንማርም አሉ


ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የተገደሉ ተማሪዎች አስከሬን ካልተመለሰ አንማርም አሉ




ጌታቸው ሽፈራው

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የተገደሉ ተማሪዎች አስከሬን ካልተመለሰ፣ ተማሪዎችም ወደየክልላቸው ካልተመለሱ አንማርም ብለዋል።

ተማሪዎች አንማርም በማለታቸው የተጨነቀው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ወደ ክፍል ገቡም አልገቡም መምህራን ወደ ክፍል እንዲገቡ እያደረገ ነው። መምህራን ያለ ክፍለ ጊዜያቸው ወደ ክፍል ገብተው ተማሪዎችን እንዲጠብቁ እየተገደዱ ነው ተብሏል።

ከአዲስ አበባ በስፖንሰር አሜሪካ (ቨርጂኒያ) የመጣው ጠንቋይ ጉዳይ እያደረሰ ነው


“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” ይላሉ። ከጉድም ጉድ የሚያሰኝ ወሬ ከወደ ቨርጂኒያ ተሰምቷል። በከባድ ሚዛን የሚመዘን ጠንቋይ ከአዲስ አበባ መጥቶ፣ በዲሲ፣ ቨርጂኒያ ሜሪላንድ እና ፌርፋክስ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በጥንቆላ እያገለገለ ይገኛል።
የጠንቋዩ ቢሮ በቨርጂኒያ፣ ሴሚናሪ ጎዳና ላይ የሚገኘው ሳውዘርን ታወርስ አፓርትመንት ውስጥ ነው። አገልግሎቱን የሚሰጠው፣ በማስታወቂያ አልተገለጸም እንጂ በሳምንት ስምንት ቀን ነው። በሳምንት ከ80 ሰዓት በላይ ማለት ነው። ግብር የማያውቀው ገቢውም በዚያ መጠን ይባዛል። አመሻሹ ላይ በዚህ ጠንቋይ ለመገልገል በተለያየ የሰው አይነት ይመጣል። እነዚህ መንፈሰ ደካሞች ምሽት ላይ ወደ ጠንቋዩ እየሄዱ ያጓራሉ። ይህ ሰው፣ ልክ እንደ ታምራት ገለታ፣ ”ባለ አውሊያ” እና ”ባለ ከራማ” ነኝ ብሎ በዚህ የጥንቆላ ሥራ ላይ ከተሰማራ ከዓመት በላይ ሆኖታል።
ዝርዝሩን እዚህ ጋር ተጭነው ይመልከቱትት

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ፣ በኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎቶች ላይ አፈና እያካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ





በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ፣ በኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎቶች ላይ ደፈቃ ወይም አፈና እያካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋው ስርዓቱ፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ፣ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማድበስበስ እየሞከረ እንደሚገኝ የገለጹት መረጃዎች፣ አፈናው ከክልሎች በተጨማሪም በአዲስ አበባ መስተዋሉን መረጃዎቹ አረጋግጠዋል በተለይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት አስቸጋሪ ሆኖ እንደዋለ የጠቆሙት መረጃዎቹ፣ በቀጥታ መስመርም ሆነ በኢንተርኔት ከውጭ ሀገር የሚደወሉ ስልኮች ከፍተኛ የኔትዎርክ ችግር እንደገጠማቸው ከመረጃዎቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል::
ከሰኞ ዕለት ጀምሮ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆናቸው ለኢንተርኔት መቋረጥ ሰበብ ተደርገው ተወስደዋል አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሰልፎቹን ተከትሎ የሚፈጽማቸው ግድያዎች ተድበስብሰው እንዲቀሩ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ነቀምት፣ በደሌ እና ማንዲ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን ተከትሎ፣ በአካባቢዎቹ የኢንተርኔት አገልግሎት እዲቋረጥ ተደርጎ መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል ስርዓቱ ተቃውሞ በተነሳበት ቁጥር እንዲህ ያለውን እርምጃ የሚወስደው፣ የሚፈጽመው ግድያ እና እስራት እንዳይጋለጥበት ስለሚፈልግ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ ላለፉት አራት ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የቆየው የኢንተርኔት አፈና፣ አድማሱን አስፍቶ ዛሬ በአዲስ አበባ መስተዋሉም ታውቋል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተወሰኑ አካባቢዎች የኢንተርኔትም ሆነ መደበኛው የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል በተለይ ከሰባት እና ስምንት ሰዓት ጀምሮ፣ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር፣ ችግሩ ያማረራቸው ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል ያለ ማቋረጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ በስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ፍርሃት የፈጠረበት ሲሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎችም የታጠቁ የጸጥታ አካላት እንዲሰማሩ ተደርጓል::

BBN NEWS

Ethiopia is using Israeli spy technology to target its dissidents abroad






Gagged—even abroad. (Reuters/Darrin Zammit Lupi)

Ethiopia’s government has been doubling down on its efforts to surveil its critics, bringing the long arm of the state into the foreground and its resolve to sabotage opposition figures and media outlets.

A new report published by the Citizen Lab at the University of Toronto’s Munk School of Global Affairs notes that dissident journalists and academics based in 20 countries received emails containing commercial spyware asking them to click on links to an Eritrean video website or download Adobe Flash updates or PDF plugins. If users clicked on the email, the spyware operators in Ethiopia would be able to monitor and extract virtually any information on the device including emails, audio, and video files.

The malware attacks, carried from 2016 to the present, was enabled through surveillance tools from Israeli cybersecurity company Cyberbit, a subsidiary of defense contractor Elbit Systems. The spyware system, known as PC Surveillance System (PSS), targeted opposition figures in Canada, US, and Germany, along with Eritrean companies and government agencies besides a researcher from Citizen Lab itself.

Through their analysis, the lab said it was able to monitor “apparent demonstrations of the spyware in several other countries where leaders have exhibited authoritarian tendencies, and/or where there are political corruption and accountability challenges, such as Nigeria, Philippines, Rwanda, Uzbekistan, and Zambia.”

Telecom and internet surveillance are not new in Ethiopia with the government manning large surveillance mechanisms for years, especially in the digital media context. This is especially augmented by the government’s monopoly over all mobile and Internet services through the state-owned Ethio Telecom. The current surveillance efforts are also increased by the climate of fear and worry that has pervaded the country following protests by the Oromo community in 2015 and 2016. During the protests, the government killed over 1,000 protesters and arrested tens of thousands of people in a wide purge criticized by human rights organizations. And despite having low internet and mobile connectivity, it also shut down the internet and banned posting updates about anti-government protests on Facebook.

During the protests, diaspora media outlets like OPride, Ethiopian Satellite Television, and Oromia Media Network (OMN) continued to shed light on the crisis and advocate for social justice. Ethiopian officials responded by banning the networks, and labeling them as “belonging to terrorist organizations.” Citizen Lab said the first attack they identified was aimed at OMN executive director Jawar Mohammed.

The new evidence also revives the discussion about the export of commercial spyware abroad, and how nation-states are using them to undermine entities they deem as political threats. Ethiopia, which has been accused of human rights violations, previously acquiredsurveillance systems from Germany-based Gamma International’s FinFisher and Italy-based Hacking Team’s Remote Control System. In a recent response to the allegations, Cyberbit said that as a vendor, its customers “are the sole operators of the products at their sole responsibility and they are obliged to do so according to all applicable laws and regulations.”

ግልፅ ደብዳቤ ለእግዚአብሄር | ከሔኖክ ዘውዴ

ይድረስ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ የአብረሃም አምላክ የቅድስት ድንግል ማሪያም ልጅ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አንዲሁም የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች በምታምኑት እና በምታመልኩት አምላክ እንዲታይልኝ የፃፍኩት ግልፅ ደብዳቤ ነው።
ይህንን ደብዳቤ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር ቢኖር ብዙ ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች ብዙ ጊዜ ግልፅ ደብዳቤ የሚፅፉት ለሃገር መሪ ወይም ጉዳዩ ይመለከተዋል ለሚሉት ክፍል ሲሆን እኔ ግን በአሁን ሰአት በሃገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ ቀዉስ ሃገራችንን ወደ ማንፈልገው የዘር መጠፋፋት እና እልቂት እያመራች ስለሆነች ይህን ጉዳይ በአሁን ጊዜ ሃገራችንን የሚያስተዳድረው መንግስት ብዬ ለመጥራት ትንሽ ስለሚከብደኝ ነፍሰ በላ አስተዳደር በኢትዮጵያኖች ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሱት ኢሰባዊነት ድርጊት ተቃዉሜ በእግዚሀብሄር ፊት ይህንን የክስ ደብዳቤ እንዲታይልን ነው።
በኢትዬጵያ ወይም በውጭ ሃገር ያላችሁ የፖለቲካ መሪዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የሃሳብ ልዩነት እና ግለኝነታችሁን ትታቹ ወደ አንድ ሃሳብ መታችሁ ሀገራችን ወደ ማትወጣው አዘቅጥ ዉስጥ ከመግባቷ በፊት የሚቻላችሁን እንድታደርጉ በእግዚሀብሄር ስም እጠይቃችዋለዉ።
በሊቢያ የሚደረገው የሰው ሽያጭ ልክ ደብረዘይት መንገድ ዳር እንደቆመ ከሰል የሰዉን ልጅ 200,300 ሲገመቱ ማየት ከዚህ በላይ ሊያም የሚችል ነገር አለ ብዬ ማሰብ ይከብደኛል።
በዩናይትድ ኔሽን እና በአፍሪካ ዩኒየን በተለያዩ መድረኮች ላይ ወይም በአለም ፍርድ ቤቶች ድምፃቸዉን የሚያሰማላቸው ወይም ፍትህ ያገኛሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።
ፍርድን ሳያጓድል የሚሰጥ አንድ እግዚሀብሄር ብቻ ነው።
t

 

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መግለጫ: በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ?





የሀገር መከላከያ ሰራዊት …የተፈፀመ የጅምላ ፍጅት

በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ?


የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውኝ ጊዜ ለህገመንገስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዘቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ የሀጎች ሁሉ የበላይ ሆኖ ባለበት ሁኔታ የስልጣን ባለቤት የአገሪቷ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች ሆኖ እያሉ በማንኛው የአገሪቱ ባለስልጣን ውሳኔ ወይንም በማንኛውም የመንግስት አካል ወሳኔ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጋጭ ተግባር በፈፀም በማይቻልበት ሁኔታ የአገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከተሰጠው የስልጣን ገደብ ጥሶ ህዝቡ ውስጥ በመግባት ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።



ለዚህ መልካም ማሳያ የሚሆን ጥቂት ሀላፍነት በጎደላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በሜታ ወረዳ በጨለንቆ ከተማ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ዘግናኝ የጅምላ ፍጂት ነው። ከዚህ ጅምላ ፍጂት በስተጀርባ ማነው ያለው የሚለው ጥያቄ ለህዝቡ መመለስ ግዴታ ነው። ከዚህ አፀያፊ ድርጊት በስተጀርባ ያለ ሃይል ሊጋለጥ ይገባል።

ለህግም መቅረብ ይኖርበታል። በአገራችን ህገ-መንግስት መሰረት የመጨረሻው የመከላከያ ሰራዊቱ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስተረሩ ነው። እንደዝህ አይነት ወንጀሎች ሲፈፀሙ ከእውቅናው ውጭ ከሆነ መርምሮ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ የሚገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህንን ከማድረግ ፋንታ ተመሳሳይ ወንጀሎች በሚፈፀሙበት ውቅት ዝምታን መምረጥ ለሚፈፀመው ወንጀል እውቅና መስጠቱን ያሳያል።

የመከላከያ ሰራዊቱ የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወደክልሉ እንዲገባ ጥሪ ባላደረገለት ሁኔታ የክልሉን ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤትነት መብት በመግፈፍ የፈፀመውና እየፈፀመ የሚገኘው ወንጀል የአገሪቱን ህገ-መንግስት በግልፅ የጣሰ ነው። ይህንን ስንል የመከላከያ ሰራዊቱ በሙሉ የዚህ ችግር ሰለባናቸው ማለታችን ሳይሆን የህዝቡ ወገንተኝነት ያላቸው የመከላከያ አባላት እንዳሉ ሁሉ ጥቂት የሰራዊቱ አባላት ግን ሆፐን ብለው ህዝቡ ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸው በግልፅ እየታየ ነው።

በመሆኑም የህዝቡን ደህንነትና ሰላም ከማስተጠበቅ ፋንታ የህዝቡን ሰላም እያደፈረሱና ጉዳት እያደረሱ ያሉ የሰራዊቱ አባላት ለህግ ሊቀርቡ ይገባል። የህግ የበላይነት እንዲከበር የሚመለከተው አካላት ሁሉ ካልተንቀሳቀሰ ነገም ተመሳሳይ ችግር መከሰቱ የማይቀር ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም በዚህ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶበት የመፍትሄ አቅጣጫ በማሰቀመጥ እየሰራ ይገኛል።

የመከላከያ ሰራዊቱ የቆመለትን አላማ በመዘንጋት ያለሙያው በህዝቡ ውስጥ በመግባት ማወክ የማንን አላማ ከግብ ለማድረስ እንደሆነ ተለይቶ መታወቅ አለበት። የፌዴራል መንግስትና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይህንን አሰቃቂ ወንጀል የፈፀሙትን የሰራዊቱ አባላትእና ከበስተጀርባ ሆነው ያቀዱትን ለህግ ለማቅረብ እየሰሩ ይገኛሉ። የሚደረስበት ውጤትም ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል።

የክልሉ የጸጥታ አካላትም የክልሉን ህዝብ ሰላም ለማስከበር ማንኛውንም አይነት መስዋዕትነት ለመክፈል ከማንኛውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን አለባቸው። ህዝቡ አላስፈላጊ መስዋዕትነት እንዳይከፍል በመረጋጋትና በጥንቃቄ ሊንቀሳቀስ ይገባል። ከሁሉም በላይ መደማመጥና በአንድነት መንቀሳቀስ እጅግ ወሳኝ ነው።

የኦሮሞ ህዝብ ላቀረበው የመብት ጥያቄ፣ መብቱን በሰላማዊ ትግል ለማስከበር ስለተንቀሳቀሰ በቄዬው ላይ በጅምላና በተናጠል የመገደል፣ ከሚኖርበት አከባቢ የመፈናቀልና ሽብር ሊፈፀምበት አይገባም። የኦሮሞ ህዝብ ትናንት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ደሙን የከፈለና አገሪቷ ሉዓላዊነቷን ጥብቃ ለዛሬ እንድትበቃ ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመሆን የተጠየቀውን ዋጋ ሁሉ የከፈለ ህዝብ ነው። የአገሪቷ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትናንት ያንን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈሉት ለዚሁ አገር አንድነት፣ ሰላምና ብልፅግና ነው።

ዛሬም ጥቂት የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ህዝቡ የጣለባቸውንሃላፊነት በመዘንጋት ሰላማዊውን ህዝብ በቄዬው ላይ መግደል አስነዋሪ ነው። በመሆኑም ይህንን ወንጀል የፈፀሙትን አካላት ለህግ ማቅረብ ያስፈልጋል። ይህንን ለማድረግ በአንድ ባንድራ ስር አብረን ለምንኖር የአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አንድነትና ድጋፍ ጊዜው አሁን ነው። በጨለንቆ በተፈፀመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው? ለሚለው ጥያዌ ህቡ በግልፅ መልስ ሊያገኝ ይገባል።

Oromia communication Bureau.

Tuesday, December 12, 2017

የጋይንት የ26 አመት የቁልቁለት ጉዞ(ከጋይንት የተላከ)

የጋይንት የ26 አመት የቁልቁለት ጉዞ(ከጋይንት የተላከ)
ባንድ ወቅት ደበርታቦር ላይ በነበረ የሩጫ ውድድር ፡ጋይንት “አንበሳው ጋይንት” ተብሎ በሚጠራበት ዘመን ፡ አወዳዳሪዎች “የጋይንት ሯጮች ወደ መሮጫው ቦታ ኑ!” ብለው በማይክራፎን ሲናገሩ በወቅቱ የነበሩት የጋይንት አውራጃ አስተዳዳሪ “ጋይንት ያሯሩጣል እነጅ፡አይሮጥም” አሉ ይባላል፡፡ ጋይንት አንበሳ፤ ልበ-ሙሉ፤ደፋርና በጀግንነት የተሞላ፡ የአፄ ቴዎድሮስ ቀኝ እጅ የፊትአውራሪ ገብርየ ሀገር፡ ከገጠመ ወደኋላ የማይል፡ እንጅ ቦቅቧቃ ፈሪ አይደለም ለማለት ፈልገው ነው፡፡ ሩጫ እንደዛሬው ቢዝነስ ሳይሆን በአካል የጠነከረ በአእምሮው የዳበረ ፡ ሀገሩን የሚወድ በኢኮኖሚውና ፖለቲካው፡ ንቁ ተሳትፎ ያለው ወጣት ለማፍራት በሚፈለግበት ዘመን ነው፡ ይህ የሆነው፡፡ የአሁኑ መንግስት ግን ወጣቱ በጫትና መጠጥ የደነዘዘ፡ በግዴለሽነት የተሞላ፡ እራሱን የጣለ ፡ስለሀገሩም ሆነ ስለ ፖለቲካው ምንም ደንታ የሌለው፡ ምንም አይነት ጥያቄ የማይጠይቅ፡ ዝም ብሎ የሚገዛ፡ ለማድረግ 26 አመት ሙሉ ህወሀት ድብቅ ሴራ ስትጎነጉን ኖራለች፤ ምንም እንኳን የባሰ እሳት የሆነ ህወሀትን መቆሚያ መቀመጫ የነሳ ጠንካራ ትውልድ በህዝብጥረት ቢፈጠርም፡፡አሁን ላይ ሳስበው ፡ ከየት እንደምጀምር ይጨንቀኛል፡፡ 



ግፉና የኋሊት ጉዞው ዘግናኝ ነው፡፡ ጋይንት፡ በህወሀት ትእዛዝ በጉጅሌው ፡ብአዴን ተላላኪነት፡ በጥቂት የመሀይማን ሆዳም አባላት አስፈፃሚነት ፡ ደረጃውን የጠበቀ እስር ቤት ከ10፡አመት በፊት ተገንብቶለታል (ይሄ በኢቢሲ አልተነገርም፣አልተለፈፈም፡፡)፡፡ ጋይንትን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ከማንኛውም ማህበረሰብም ሆነ አካባቢ ፡ ለየት የሚያደርገው፡ ሰው ሰራሽ የማደህየት ወንጀል ተፈፅሞበታል፡፡ አሰቃቂ ፡ የጭቆና፡ የተመፅዋችነት ስነ-ልቦና እንዲያድርበት በህወሀት-ብአዴን ተፈርዶበት የጣረሞት ጉዞ ይጓዛል፡፡ አንድን ፈረንጅ ወይም ነጭ ዜጋ፡ ብር ልስጥህ ወይም በሆነ ነገር ልደግፍህ ብትሉት “ለምን? እኔ እራሴን የቻልኩ የማንንም ድጋፍ የማልፈልግ ሰው ነኝ”የሚል መልስ ይሰጣችኋል፡፡ ምክንያቱም ከልጅነቱ ጀምሮ እንዴት እራሱን የቻለ ሰው መሆን እንዳለበት ቤተሰቡም ሆነ መንግስት ስላስተማሩት፡፡ ወደ ጋይንት ስንመጣ “ጋይንት በልማት ጎዳና ነው” በማለት ኤፍ.ኤች.አይ፤ ሲ.ፒ.ኤ.አር፤ ወርልድ ቪዥን….በሚባሉ ድርጅቶች ህብረተሰቡን ያላንዳች ርህራሄ ጥገኛ፡ ተመፅወችና የእርዳታ ለማኝ እንዲሆን 26 አመት ዝቅጠት ውስጥ እንዲገባ ፈረዱበት፡፡ ጋይንት ማለት ህወሀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከዋልካ ጭቃ+በስኳር ተላቆ፤ጤፍ እንጀራ በእርጎ የበሉበት፤ ቅማል የወረሰውን ቁምጣቸውን ጥለው፡ ንፁህ ልብስ የለበሱበት፤ ሰውነታቸውን የታጠቡበት ሀገር ስለመሆኑ ማንንምመጠየቅ አያስፈልግም (አቦይ ስብሀት፤ ስዩም መስፍን፤ በረከት ስመኦን….ታዉቁታላችሁ፤ ታስታዉሱታላችሁ)፡፡ 

ነገር ግን ይሉኝታ በተፈጥሮው የማያውቀው ህወሀት፡ የጭካኔ በትሩን ጋይንት ላይ ሲያሳርፍ ብዙ ጊዜም አልወሰደበት፡፡ባንድ ወቅት፡ ገበሬወችን ለማደህየት በማሰብ ህወሀት ከማእከል ለሆዳሙና ምንመ አርቆ ማየት ለተሳነው የወቅቱ ብአዴን መላ ብላ የዘየደችው ነገር እንኳን የአንድ ሀገር ዜጎች የትኛውም አለም ላይ ተፈፅሞ አያውቅም፡፡ ገበሬዎችን “እርዳታ የምንሰጣችሁ በሚኖራችሁ የበሬ ብዛት ይወሰናል” በማለት፤ ገበሬዎች ፡ በሬዎቻቸውን እንዲሸጡ ፤ በቀጣይም ምንም ማረስ ስለማይችሉ፡ ሙሉ በሙሉ በድህነት ውስጥ ከወደቁ እንደፈለግን እናስተዳድራለን በሚል ቁንፅልና ጭካኔ የተሞላበት ሀሳብ ፤ በሬዎቻቸውን እጅግ በወረደ (በርካሽ) ዋጋ ለህወሀት ወታደር ቀለብና ለህወሀት ነጋዴዎች እንዲሸጡ ተደረጉ፡፡በ1989 ዓ.ም አካባቢ ተስፋዬ፡ የተባለ አረመኔ ከትግራይ ወደ ጋይንት በእንግሊዝኛ አስተማሪነት በማምጣት፡ ወጉን ባህሉን እነዲሁም የከተማውን መውጫ መግቢያ ሁሉ በደንብ እንዲያጠናና እንዲሰልል፡ ከተደረገ በኋላ የከተማው አስተዳደር በመሆን የጋይንትን ህዝብ የድህነት፡ የመከራና የጭቆና ጉዞ ያፋጥነው ጀመር፡፡ ተስፋዬ እንደመጣ በደንብ አማርኛ እንኳን፡ መናገር አይችልም ነበር፡፡ 

በነገራችን ላይ የጋይንት ሰው ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ “ከሌላ አካባቢ የመጣ ሰው ነው” ከታባለ የመንከባከብና በርህራሄ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ወዲያዉኑ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀልና አብሮ መኖር እንዲችል የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ አለው፡፡ የጅኦግራፊ እስተማሪ የነበረው “አሰፋ” ኦሮሞ ነበር፡፡ ነገር ግን አሰፋ ኦሮሞ ስለሆነ እንደ ተስፋዬ ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ጋይንትን እንደ ስዩም በላይ፤ ዘመነ፤ ሁሴን ኢብራሂም፤ ( አምባቸው ፡ የጎማጣ ሰፈሩ ወፍጮ በሙስና ያስተከለው)…..የመሳሰሉት ያካባቢው፡ አርቀው ማሰብ የማይችሉት ድውያን፤ አስፈፃሚነት 26 አመት የድህነት፤ የጨለማ የስቃይና የግፍ አመታትን ተጓዘ፡፡ ህወሀት ወያኔ ከፈፀማቸው ወንጀሎች ከብዙው በጥቂቱ የሚከተሉትን እንይ፡-1. ጋይንት እጅግ ሀብታም ሀገር ነው፡፡ ማንም ሰው በዚህ ቅፅበት ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ የደን ሽፋኑን ማየት ይችላል፡፡ ባለፉት 25 አመታት ከወረዳው ከ4.000.000.000 (አራት ቢሊዮን ብር) የሚገመት ደን በመጨፍጨፍ፡ በመላው ሀገሪቱ ለሚካሄደው የመብራት እና ስልክ ግንድ (ፖል) እንዲሁም ትግራይ ውስጥ ለተቋቋመው የወረቀት ፋብሪካ ግብአት ሲያቀርብ ኖሯል፡፡ 

ለዚህ ውለታውም 26 አመት ሙሉ እርደታ ተመፅውቷል፡፡2. አንዱን ቅንጣት የመንገደኞች ማረፊያ እና የህዝብ መዝናኛ የነበረውን “ነፋስመውጫ ሆቴል”ን እንዲከስርና ለካድሬ ሴራ መሸረቢያ፡ እንዲሆን በማድረግ ህወሀት ውለታዋን ስትመልስ፤ ቲኒሽ አለፍ ብሎ ማሰብ የማይችለው ሎሌው ብአዴን ከተለያዩ የጋይንት ገጠራማው ክፍል የሚያመጣቸው አስተዳዳሪዎች፡ ያንን ታላቅ ሀገር፡ ለዚህ ድህነትና ውርደት አበቃው፡፡3. ጉና ተራራ አካባቢ ወረቀት ፋብሪካ ፤ የችፑድ ፋብሪካ (ጥሬ እቃው ከላይ እንደገለፅኩት በአይን የሚታይ) ፤የመስታወት ፋብሪካ፤ የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ (ቆዳተሰብስቦ ወዴት እንደሚጫን እናውቃለን) ፤ የአረቄ ፋብሪካ (ጥሬ እቃውን ለዳሽን ቢራ ይጠቀሙበታል) ለመትከል የሚያስችል እምቅ የተፈጥሮ ሀብት እንዳለው በማወቅ በደርግ ጊዜ እነኝህን ፋብሪካዎች ለመትከል ሲታሰብ ፤ እነዚህ ፋጉርቶችና ጥላቢሶች ከየት እንደመጡ ሳይገመት፡ እቅዱን ሁሉ ሰብስበው በመውሰድ፤ ትግራይ ላይ ሁሉንም ፋብሪካወች ተከሉ፡፡ ልብ-በሉ፡ ጥሬ እቃ ከጋይንትና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች፡ ፋብሪካው ትግራይ፤ ሰራተኛው ትግሬ ብቻ፤ ባለቤቱ ኤፈርትወይም የትግራይ ክልል፡፡ ትግራይ ፋብሪካ አይተከል አላልንም፡፡


 ነገር ግን ጋይንት ላይ ጥሬ እቃ እየወሰዱ ትግራይ ላይ መትከልና ልዩ ተጠቃሚ ማደረግ ግን ያስተዛዝባል፡፡ እኔ ስበላ አንተ ተመልከት ማለት ግን ፍፁም እራስ-ወዳድነትና ስግብግብነት ነው፡፡4. በደርግ ጊዜ የተተከለ፡ ለ6 ተከታታይ ሰአታት ለመላው የነፋስ መውጫ ከተማ ህዝብ ፡ የመብራት አገልግሎት ፡ የሚሰጠውን ጀኔረተር ወደ ትግራይ በማሻገር ጋይንትን መበዝበዝ አሀዱ ብለዉ የጀመሩት ከ25 አመት በፊት ነበር፡፡5. ጋይንት አውራጃ ነበር፡፡ ይህም ማለት በአሁኑ ወቅት ዞን እየተባለ በሚጠራው አወቃቀር ማለት ነው፡፡ ያ እንዳይሆን ወደ ወረዳነት ዝቅ እንዲል ተደረገ፡፡ ዞን ቢሆን ኖሮ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችንም ኢነቨስትመንቶችን መሳብ ይቻል ነበር፡፡ ምክንያቱም በቂ ጥሬ እቃ (የተፈጥሮ ሀብት የታደለ በመሆኑ) ፤ ነገር ግን በሚፈፀምበት ፖለቲካዊ ተፅእኖ፤ እዛው ተወልደው ያደጉት ባለሀብቶች ሳይቀሩ ወረዳውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ የነበረው ከተማ አድጎ፡ ሰፍቶና በልፅጎ ፡ የዘመናዊነት መገለጫ ፡ ለአካባቢው የገጠር ማህበረሰብ አገልግሎት ማቅረብ ሲገባውበተቃራኒው የገጠርነት ባህሪ እንዲኖረው ፡ በማድረግ፡ እንዲሁም ምንመ አይነት ጥያቄ ማንም ማቅረብ ባማይችልበት ደረጃ በስነ-ልቦና በመጉዳት ለማሰብ የሚዘገንን ሴራ ተፈፅሞበታል፡፡6. ህዝቡ የትምህርት ፖሊሲው ከ7ኛ ከፍል ጀምሮ በእንግሊዝኛ ይሁንልን ብሎ ቢጠይቅም፤ ከጫካ የመጣ መሀይም የብአዴን ካድሬ፡ ህወሀት የሰጠችውን የቤት ስራ ለመስራት፡ የእራሱን ህዝብ መስዋትነት በማቅረብ ፡ ሆዱን ሲሞላ ኖረ፡፡ ለመሆኑ የትኛው የአማራ ክልል ህዝብ እና ሙህር መንግስትን ልጆቼ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው፡ ይማሩልኝ ፡ ብሎ ጠይቆ ነው በግድ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ካልተማርክ ተብሎ የተፈረደበት? የትምህርት ፖሊሲውን ያለህዝብ ፍላጎትና ሳይንሳዊ ጥናት በግዴታ አስፈፅሙ ሲባል ብአዴን እንዴት ይሄንን ሴራ ተገንዝቦ መቀልበስ ያቅተዋል (ለነገሩበትግሬዎች አይደል እያንዳንዱ መስሪያ ቤት የሚተዳደረው፡፡)7. የጋይንት ህዝብ በጀግንነቱ በታሪክ የሚታወቅ ፤ የሚከበርና የሚፈራ፡ የፊታውራሪ ገብርየ ሀገር ነበር፡፡ 
Image may contain: 1 person

ይሄንን ኩሩ እና ሩህሩህ፡ ህዝብ በ1977 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ከተለያዩ የትግራይ፡ አካባቢዎች የመጡ ወገኖቹን የሚበላውን አካፍሎ፡ በችግር ቀን አብሮ መኖርን ያሳየ ህዝብ ከህወሀት ዘንድ ውለታው የተመለሰለት እራሱ ድህነትን እንዲለማመድ በማድረግ፣ ስልጣኔን እንዲተው በማድረግ ፣ ከ30 አመትና ከዚያ በፊት የነበረውን ህዝብ ፡ እንደ ፍቃዴ ዳምጤ ያሉሆዳም ካድሬዎች ሆዱን (ቦርጩን) እንጂ ጭንቅላቱን ማስፋት የማይችለው ተራ መሀይም እንዲገዛው ፈረዱበት፡፡በነገራችን ላይ ጋይንት ከ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጥሬ ሀብት የዘረፉት ወያኔዎች፡ ለዚህ ውለታ የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ያለተሟሉለት ፡ ባዶ ግድግዳና ጣሪያ፡ ያለው የገጠር ፡ ሆስፒታል ሰራንላችሁ በማለት በህብረተሰቡ ላይ ተሳለቁ፡ ከበሮ ደለቁበት፤ለሚዲያ ሽፋን አዋሉት፤ ህዝቡን የበለጠ አዘናጉበት፡፡ በመሆኑም ደረጃውን የጠበቀ እስርቤት (ማረሚያ ቤት ለማለት ያስቸግራል) ከመገንባትውጭ የጋይንት ህዝብ ምንም ተጠቃሚ የሆነበት ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ1. ጋይንት የክልልም ሆነ የሀገር አቀፍ ምክር ቤቶች ተወካዮች ከዚህ በኋላ የሚፈይዱለት ነገር አለመኖሩን በማወቅ፡ ውክልናቸውን መሰረዝ፤2. ህወሀት የጋይንትን ህዝብ ለማጥፋት ብትፈልግም በፈጣሪ ታምር እስካሁን ሊቆይ ችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ከዛሬ ነገ የተሻለ ይሆናል በሚል መዘናጋት ሳያስፈልግ የወደፊቱን አርቆ በማሰብ አስፈላጊውን ትግል መጀመር፤ የተጀመረውን አጠናክሮ መቀጠል፡፡

3. ከእለት ሆዳችሁ እና እንደ ህፃን ልጅ፡ በቶዮታ መኪና ለመንሸራሸር የህዝባችሁን መከራና ግፍ የምታራዝሙ የብአዴን አባላትና የወረዳው አመራር ከታሪክተጠያቂነት ብትድኑ መልካም ነው፡፡ እንደ እነ ወንድወሰን ከልካይ በሄዳችሁበት ሁሉ ሰው የሚወዳችሁ በመሆን ታሪከ ሰርቶ ማለፍ እንጅ፡ ወያኔ የነገረህን ተረት ተረት በማስፈፀም የእህትና ወንድሞችንህ ፡ ሰቆቃ ዞር ብላችሁ ብትመለከቱና ባታራዝሙ ጥሩ ነው፡፡ ህወሀት እንደሆን ቢያንስ እንኳን ብሄሩዋን ጠቅማለች (ለዚያም ነው ህወሀት ትግራይ ላይ ሙሉ ድጋፍ ያለው)፡፡ ሂድና የአድዋን ወረዳ ተመልከት፡፡

ለብአዴን ሆይ!! አድዋ ወረዳ ነች፡፡ ነገር ግን ውድድሯ፡ ከክልሎች ከተሞች ከእነ ባህርዳር ጋር እንጂ ፡ ህወሀት በኢቢሲ፡ እንደሚነግርህ የተመጣጠነ የከተሞች እድገት፡ አለ ብለህ “በራስህ” ህዝብ ላይ፡ ጥቁር ታሪክ አትፃፍ፣ ፡፡ (…ሀሀሀሀሀ….ባህር ዳር ከመቀሌ፤ ጎንደር፣ደብረታቦር፣ ፍኖተሰላም፣ ደሴ፣ ደ/ብርሀን፣ ደብረማርቆስ፣ሰቆጣ፣ ወልዲያ ከአቻዎቻቸው ከሽሬ፡ አዲግራትና አክሱም ጋር ሲወዳደሩ…ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ…ድንቄም የተመጣጠነ የከተሞች እድገት)4. በተለያየ ጊዜ በክልሉ የተፈፀሙትን የኢኮኖሚ፤ ጤና እና ማህበራዊ እድገቶች ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ወደ ኋላ የቀራችሁ መሆኑን አለም-አቀፍ እንዲሁም የህወሀት ጥናቶች አረጋግጠውላችኋል፡፡ ሆዱ እንጅ ጭንቅላቱ መስፋት የማይችለው የብአዴን አተላ አባላት፤ ቆም ብላችሁ ሌሎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ጀግኖችን በማየት ፡ እናንተም አስፈላጊውን መስዋትነት ለህዝባችሁ በመክፈል የጥሩ ታሪክ ባለፀጋ ብትሆኑ ይሻላችኋል፡፡ በነገራችን ላይ፡ እጅጉን የተጠናከረ የውስጥ ትግል እያደረጋችሁ ያላችሁ ጀግኖቻችን፡ ስማችሁን በወርቅ ቀለም የምንፅፍበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጋይንት ህዝብ አሁንም ቢሆን በጀግንነቱ እንደማይታማ በ2008 ዓ.ም የወያኔን መንግስት ምጥ ውስጥ በማስገባት ማስጨነቁ ከብዙው የቅርብ ጊዜው ትዝታ ነው፡፡ ወደፊትም ቢሆን በዚህ ጀግንነቱ ከሌሎች አማራ ወንደሞቹ ጋር በመስራት የወያኔን ግባተ-መሬት እንደሚፈፅም ጥርጥር የለውም፡፡ ህወሃትም ብትሆን ጋይንትን በእጅጉ እንደምትፈራው ይታወቃል፡፡ ለዚያም ነው ከየትኛውም አካባቢ ቀድመው የጋይንትን ህዝብ ለችግር የዳረጉት፡፡
facebook Yeabesha Tilahun Tsehay

 

የአሸባሪዎች ምንጭ በተባሉ 8 ሀገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ ሕግ በአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጸደቀ


)
የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ሕግ አጸደቀ።
ውሳኔው ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ሲታወቅ በሁለት ግዛቶች የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ለመቀልበስ ክርክር በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ሉ የተባሉ 
ባለፈው መስከረም ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበውን የጉዞ እገዳ ሕግ ሙሉ ለሙሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሲያጸድቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔውን ያሳለፈው ትላንት ሰኞ ነበር።
ሕጉ ከቻድ፣ኢራን፣ሊቢያ፣ሰሜን ኮሪያ፣ሶሪያ፣ቬንዙዌላ፣ሶማሊያ እንዲሁም ከየመን ወደ አሜሪካ ለመምጣት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው እገዳ ያስቀምጣል።
ከዚህ በፊት ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተንቀሳቀሱበት ወቅት በሀገሪቱ ሁለት ግዛቶች ባሉ የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ እንዳይሆን እገዳ ተጥሎበት እንደነበር ይታወሳል።
በአብዛኛው የእስልማና እምነት ተከታይ ሀገራት ላይ የጉዞ ማዕቀብ ለመጣል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲያደርጉ ለነበረው ጥረት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰኞ ውሳኔ ጊዜያዊ ደስታና የአሸናፊነት ስሜት ሊሰጣቸው ቢችልም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ታውቋል።–እስከዛው ግን ተግባራዊ መሆኑ ይቀጥላል።
የትራምፕ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የጉዞ እገዳ ለማድረግ ስልጣን አለው ብሎ ያምናል።
ሕጉ እንዲጸድቅ መከራከሪያቸውን ያቀረቡት የሕግ ጠበቃው ጄኔራል ኖኤል ፍራንሲስኮ በፍርድ ቤቱ ሲናገሩ የሀገሪቱ ህገ መንግስትም ሆነ የተወካዮች ምክር ቤት ሕጎች ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈልጉ ሰዎችን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማገድ ይችላል ሲሉ ተከራክረዋል።
ሕጉ ሙስሊሞችን ለማገድ የወጣ ነው ለሚለው ነቀፌታም ተሻሽሎ በቀረበው ሕግ ከተዘረዘሩት ሀገራት ውስጥ በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች የማይገኙበት እንዳሉ መጥቀሳቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።
ሕጉ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ወቅት ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንቱ የአንድን እንግሊዛዊ በእስልምና ላይ ያነጣጠሩ ሶስት ትዊቶችን መልሰው ትዊት ማድረጋቸው ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ በሃዋይና በሜሪላንድ ግዛቶች ሕጉን ለማስቆም ክርክር በመደረግ ላይ ሲሆን በዚህ ሳምንት በይግባኝ ፍርድቤቶች ሊታይ እንደሚችል ይጠበቃል።

Monday, December 11, 2017

ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ የቀረበ የድረሱልን ጥሪ! (በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ 38ቱ ተከሳሾች)

ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ የቀረበ የድረሱልን ጥሪ!
(getachew shiferaw)
(በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ 38ቱ ተከሳሾች)
~ኢሰመኮ ያቀረበውን ሪፖርት አያይዘን ለዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ጀኔባ ለመክሰስ የተገደድን ስለሆነ ስለ ሰዎች መብትና ነፃነት የሚያስብ፣ የሚቆረቆር ግለሰብም ሆነ ተቋም ፣ የማንኛውም ሀገር ዜጋ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙብን አካላትን በህግ እንድንፋረዳቸው እንድትረዱን፣ ለዓለም ህዝብ እንድታደርሱልን ጥሪ እናቀርባለን!
~ጥፍራችን በፒንሳ ተነቅሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አይደገምም ተብሎ ሀውልት የየሰራለት የቶርች ገረፋ ተፈፅሞብናል። ንብረታችንን ዘርፈውናል። ህክምና ተከልክለናል። ለነርቭ፣ ስነ ልቦና እና ለተለያዩ በሽታዎችና ቀውስ ተዳርገናል። ይህንን የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት በመናገራችን ለ3 ወራት ጨለማ ቤት ከተውን ቤተሰቦቻችን እንዳናገኝ ተከልክለን ሕገ መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል።
~አማራና ጉራጌ ግንቦት ሰባት፣ ኦሮሞን ኦነግ፣ ሙስሊሞችን አልሻባብ በማለት መብታችን ተረግጧል። በእኛ በተከሳሾች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙብን አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ምርመራ እንዲያካሂድ ግልባጭ የተላከለት ቢሆንም እስካሁን ድረስ ቀርቦ ያናገረን አካል የለም። ይህም በመሆኑ የሰዎችን መብት ለማስጠበቅ ኃላፊነት ላለበት ዓለም አቀፈ የሰብአዊ መብት ኮምሽን ለማመልከት ተገደናል።
እኛ 38ቱ ተከሳሾች ቀድሞ ተከሰን በነበርንበት ክስ የዋስትና መብተችንን ተከልክለን እንደማንኛውም እስረኛ ክሳችንን በቀጠሮ እየተከታተልን ሳለን ነሃሴ 28/ 2008 ዓ•ም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ውስጥ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት "ሊያመልጡ ሞክረዋል!" በሚል ሰበብ፣ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የመብት ጥያቄ የሚጠይቁ ወንድሞቻችን (ጓደኞቻችንን) እኛ ፊት በጥይት ገድለው እሳት ውስጥ ጨምረው አቃጥለዋቸዋል።
እንዲህ ያለ አረመኔያዊ ድርጊት ከፈፀሙ በኋላ ገና ለገና ይህንን እውነት ያጋልጡብናል ብለው በመስጋት እኛን ወደ ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት በመውሰድ ለ3ወራት ከቤተሰቦቻችን ጋር እንዳንገናኝ በማፈን፣ ለምርመራ በሚል ሰበብ በዋና ኢንስፔክተር አለማየሁ በሚመራው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ አይደገምም ተብሎ ሰማዕታት ሙዝዬም ውስጥ ሀውልት የተሰራለት የ"ቶርች" ገረፋ ተፈፅሞብናል።
በካቴና ታስረን፣ ተሰቅለን ተገርፈናል። ጥፍራችን በፒንሳ ተነቅሏል። በኤሌክትሪክ ሾክ ተደርገናል። በሚስማር ውስጥ እግራችንና ጀርባችን ተበሳስቷል። ጭንቅላታችንን በሰደፍ ፈንክተውናል። የተወሰንን ታራሚዎች ተለይተን ብልታችን ላይ ሁለት ሊትር ሀይላንድ ውሃ ተንጠልጥሎብናል። ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ ብዙ በደሎች ተፈፅመውብናል።
ይህ የደረሰብን ኢ_ሰብአዊ ድርጊት ታህሳስ 14/2009 ዓ•ም ለፍርድ ቤት በማሳየትና በማስረዳት ፎቶ መነሳት አለብን ብንልም ፍርድ ቤቱ ጥያቄያችን ሊቀበለን አልቻለም። ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ስንመለስ ደግሞ "ፍርድ ቤት ሄዳችሁ ብትለፈልፉ ምንም አታመጡም!" በማለት እስከ መጋቢት 12/2009 ዓ•ም ድረሰ ለ3 ወራት ጨለማ ቤት ውስጥ ከተው የቤተሰብ ግንኙነት ከልክለውን በፀሀይ ብርሃን እጦት መልካችን ቢጫ እስኪሆንና አይናችን ብርሃን ማየት እስኪያቅተው ድረስ ተቆልፎብን ተሰቃይተናል።
እንደዚህ አይነት ግፍ የተፈፀመብን በወቅቱ የነበሩ በጣት የሚቆጠሩ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችን ከተጠያቂነት ለማዳን በጣም ደካማ አስተሳሰብ ያላቸው የመንግስት ኃላፊዎች እኛን የፖለቲካ መልስ ለማድረግ የወሰኑት ውሳኔ ነው። ህሊናቸውን ሸጠው በእኛ በንፁሃን ላይ እንዲህ አይነት ስቃይ የፈፀሙብን፣ ያስፈፀሙብን እንዲሁም ሀሳት የተቀነባበረ ክሰ የከሰሱን።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ወደ ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስደን የተፈፀመብንን ኢ_ሰብአዊ ድርጊት የኮምሽኑ መርማሪዎች ከ10 ወራት ቆይታ በኋላም ቢሆን በአይናቸው ያዩትን እውነት በዝርዝር በሪፖርት ለፍርድ ቤት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም ሰብአዊ መብት ኮምሽን ሪፖርት ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 29/ 2010 ዓ•ም ቀጠሮ ይዟል።
#የኢትዮጵያሰብአዊመብትኮምሽን ስላቀረበው ሪፖርት ያለን አስተያየት:_
1) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን (ኢሰመኮ) የተፈፀመብንን ኢ_ሰብአዊ ድርጊት ሙሉ ለሙሉ አላካተተም።
2)የኢሰመኮ ኢ _ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙብን አካላት በሕግ እንዲጠየቁ በማለት ቁርጥ ያለ ሪፖርት ማቅረብ ሲገባው እና የኮምሽን መስርያ ቤቱ ጉዳዩን ተከታትሎ በዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያደረሱ አካላት በሕግ ማስቀጣት ሲገባው ምክረ ሀሳብ በማለት የተለሳለሰ የፍራቻ የሚመስል ሪፖርት በማቅረቡ ቅር ተሰኝተናል። መስርያ ቤቱ እውነቱን እያወቀ እንዲህ ያለ ሪፖርት በማቅረቡ ምን ያህል የደህንነት ቢሮ ተፅዕኖ እንዳለበት እና በራስ መተማመን የጎደለው መስርያ ቤት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
3) ኢሰመኮ በእኛ ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙ አካላትን እንዲመረምር ወይም እንዲያጣራ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽንና ለህክምና ቡድን አባላት በመፃፉ ቅር ተሰኝተናል። ምክንያቱም ኢ_ሰብአዊ ድርጊት ከፈፀሙብን አንዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ነው። ውሻ ነከሰን ብለን ለጅብ እንድንናገር መደረግ የለበትም።
4) ኢሰመኮ በዚህ መልክም (በጥቂቱም) ቢሆን የተፈፀመብንን ግፍ በሪፖርት በማቅረቡ ምስጋና እናቀርባለን። ምክንያቱም ምን ያህል ተገደን ለፖሊስ ቃል እንደሰጠንና ለዶክመንተሪ ፊልማቸው በቪዲዮ እንደተቀረፅን የሚያሳይ ነው። በፍርድ ቤቱም በ27(2) ቃላችን ውድቅ እንዲደረግ የሚጠቅመን የሰነድ ማድረጃ በመሆኑ ነው።
#የህዝብተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደራል ማረሚ ያ ቤቶች ላይ ያለን አስተያየት:_
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ነን፣ ለምርመራ ነው የመጣነው ብለው በግልና በጋራ አናግረው መርምረው ምንም አይነት መፍትሄ አልሰጡንም። ምንም አይነት ሪፖርትም አላቅረቡም። በዚህም በጣም ቅር ተሰኝተናል። እንዲህ ነው እንጅ የህዝብ ተወካይ መሆን;
1) የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር እውነቱን እያወቀ፣ እኛ እንድንከሰስ በማቀነባበር፣ በህግ ጥላ ስር እያለን ወደ ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስደን ያ ሁሉ ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲፈፀምብን ማድረጉ፣
~ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ያሉ እስረኞችን በማስፈራራትና በማባበል ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመውሰድ በእኛ ላይ እንዲመሰክሩብን በማድረጉ፣
~መርማሪዎች ነን ከሚሉ አካላት ጋር በመተባበር እኛን በመደብደብና በማስደብደብ ጨለማ ቤት አስገብቶ፣ ቤተሰብ ግንኙነት ከልክሎ በማሰቃየት በተፈፀመብን ኢሰብአዊ ድርጊት ቅር ተሰኝተናል
2) በዚህ ኢትዮጵያዊነት በጎደለው በዘራችንና በሀይማኖታችን ተመርጠን፣ በሀሰት ተከሰን ለአመታት እንዲህ ያለ ስቃይ እንድንሰቃይ መደረጋችን ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በልባችን ላይ ጥላችሁብናል። የሞቱት ጓደኞቻችን! ገዳይ እናንተ! በሀሰት ተከሰን የምንሰቃየው እኛ! ፈጣሪን አትፈሩም? ግፍ አይደለም? ነገ በልጆቻችሁ አይደርስም? ከትግራይ ተወላጆች ውጭ ሌላው ዘር ጠላት ነው? ያሳዝናል!
3) በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከትግሬ ውጭ ሌላ አመራር የለም። አንድም የተማረ ወይም የበሰለ አስተዳደር የለም። ተናዳጅ፣ ተቆጭ፣ መሃይሞች ብቻ ናቸው። አብዛኛዎቹ ታጋይ የነበሩና በዘረኝነት ያበዱ ከትግሬ ውጭ ሌላው ዘር ሰው የማይመስላቸው ያልሰለጡ ናቸው። ይህ ደግሞ ለጭካኔና አረሜኔያዊ ተግባር ለመፈፀም አግዟቸዋል። ለዚህ ነው ፍርድ ቤት ሄደን ስንናገር የምንደበደበው። ጨለማ ቤት የምንገባው ማገናዘብ በማይችሉ አመራሮች ስለምንመራ ነው።
ቂሊንጦ ማረፊያ የሆኑት ዋና ሱፐር ኢንተንደንት አሰፋ ኪዳነ ቃጠሎው ሲደርስ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ነበርኩ ብለው ተጠርጣሪዎች በቆይታቸው ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሰብአዊ መብት ኮምሽን መርማሪዎች የደረሰብንን ጉዳት እያወቀ! በምን አይነት ሰዎች እጅ ተይዘን እንዳለን ማሳያ ነው።
#በ19ኛወንጀልችሎት ዳኞች ላይ ያለን ቅሬታ
ከነሃሴ 1 እስከ 12/2009 ዓ•ም በተከታታይ ቀናት ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን እንዲያሰማ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም ሌሎች መዝገቦችን በተደራቢ በመስራት በጠዋቱ ፕሮግራም ላይ ዳኞች ከ4 ሰዓት በፊት ባለመግባት ጉዳያችን ተጓትቶብናል።
ይህ ሳያንስ ቀሪ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በሚል ነሃዴ 12/2009 ዓም፣ ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 3 /2010 ዓም ድረስ የግማሽ አመት ቀጠሮ ተቀጥሮብናል። በዚህም ቅር ተሰኝተናል። "የዘገየ ፍትህ እንደተከለከለ ይቆጠራል" የሚለውን መርህ የጣሰ ተግባር ነው።
2) በፍርድ ቤቱ ውስጥ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለእኛ ቤተሰቦችና የእኛን ጉዳይ መከታታል እና መታዘብ ለሚፈልጉ የትኛውም ወገኖች በችሎት ውስጥ በቂ የመቀመጫ ወንበር አለመኖር፣ የችሎት መጥበብ፣ በምስክር አሰጣጥ ወቅት ዳኞች ገለልተኛ አለመሆን ቅር አሰኝቶናል።
#ለኢትዮጵያሕዝብና #ለዓለምአቀፍ ማህበረሰብ የምናቀርበው የድረሱልን ጥሪ!
1) ይህ ክስ ባለቤት አለው። ክሱ ለባለቤቶቹ ይሰጥ! ክሱ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችና ፖሊሶች ነው።
2) ኢትዮጵያ ውስጥ እውነት መንግስትና ሕግ ካለ በእኛ ላይ የቀረበው ክስ ሊቋረጥ ይገባዋል። የምናውቀው ብዙ ሚስጥር አለን። ከፍተኛ የመንግስት አካላት መጥተው ሊነጋግሩን ይገባል።
3) የብሔራዊ ደህንነት ስብሰባ ላይ በቴሌቪዝን ያየነው ዋና ኢንስፔክተር አለማየሁ ኃይሉ የተባለው የማዕከላዊ መርማሪ ፖሊስ የሚመራው ቡድን ለፈፀመብንና ላስፈፀመብን ኢሰብአዊ ድርጊት በህግ ይጠየቅልን
4) ኢሰመኮ ያቀረበውን ሪፖርት አያይዘን ለዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ጀኔባ ለመክሰስ የተገደድን ስለሆነ ስለ ሰዎች መብትና ነፃነት የሚያስብ፣ የሚቆረቆር ግለሰብም ሆነ ተቋም ፣ የማንኛውም ሀገር ዜጋ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙብን አካላትን በህግ እንድንፋረዳቸው እንድትረዱን፣ ለዓለም ህዝብ እንድታደርሱልን ጥሪ እናቀርባለን!
5) ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 3/2010ዓ•ም ድረስ ዐቃቤ ሕግ የሚያሰማቸውን የሀሰት ምስክሮችና የሀሰት ሁኔታ እንድትታዘቡልን ጥሪ እናቀርባለን
6) በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያት ከእኛ ከ38ቱ ተከሳሾች ውጭ 121 ተጠርጣሪዎች በዚሁ ወንጀል ከ20 እስከ 25 ተከፋፍለው በሌላ መዝገብ መከሰሳቸው ይተወቃል። ከእነሱ ውስጥ አርማዬ ዋቄ በማረሚያ ቤት ፖሊሶች ተደብድቦ የተገደለ በመሆኑ ጉዳዩ በሕግ ተይዞ እየተመረመረ ይገኛል። ሌሎቻችን ሰውነታችን በድብደባ በልዞ፣ ዝለን፣ ከነገ ዛሬ ገደሉን እያለን ስጋት ላይ ስለሆንን ይህ ግፍ እንዲቆም እንጠይቃለን።
#ለዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ኮምሽን
እኛ 38ቱ ተከሳሾች ቀድሞ ተጠርጥረን በታሰርንበት ክስ የዋስትና መብታችን ተከልክለን ክሳችን በመከታተል ላይ እያለን ነሃሴ 28/2008 ዓ•ም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ ሊያመልጡ ሞክረዋል በሚል ምክንያት በእስር ቤት ውስጥ የመብት ጥያቄ ይጠይቁ የነበሩ በርካታ ወንድሞቻችን ተነጥለው በማረሚያ ቤተ ፖሊሶች በጥይት እኛ ፊት ተገድለውብናል። ይህ ሳያንሳቸው ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን እኛ ለምርመራ በሚል ሰበብ ወደ ሸዋ ሮቢት ማረሚያ ቤት ተወስደን በዘራችን ብቻ ተመርጠን የአማራ፣ የኦሮሞና የጉራጌ ተወላጆች ብቻ ከፍተኛ የሆነ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈፅሞብናል።
ጥፍራችን በፒንሳ ተነቅሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አይደገምም ተብሎ ሀውልት የየሰራለት የቶርች ገረፋ ተፈፅሞብናል። ንብረታችንን ዘርፈውናል። ህክምና ተከልክለናል። ለነርቭ፣ ስነ ልቦና እና ለተለያዩ በሽታዎችና ቀውስ ተዳርገናል። ይህንን የደረሰብንን በደል ለፍርድ ቤት በመናገራችን ለ3 ወራት ጨለማ ቤት ከተውን ቤተሰቦቻችን እንዳናገኝ ተከልክለን ሕገ መንግስታዊ መብታችን ተጥሷል።
አማራና ጉራጌ ግንቦት ሰባት፣ ኦሮሞን ኦነግ፣ ሙስሊሞችን አልሻባብ በማለት መብታችን ተረግጧል። ይህን ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ጥቅምት 20/2010 መርምሬ አረጋግጫለሁ ባለው ሪፖርት ላይ በመጠኑም ቢሆን ተፈፀመብንን ኢ ሰብአዊ ድርጊት አቅርቧል። በእኛ በተከሳሾች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙብን አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን ምርመራ እንዲያካሂድ ግልባጭ የተላከለት ቢሆንም እስካሁን ድረስ ቀርቦ ያናገረን አካል የለም። ይህም በመሆኑ የሰዎችን መብት ለማስጠበቅ ኃላፊነት ላለበት ዓለም አቀፈ የሰብአዊ መብት ኮምሽን ለማመልከት ተገደናል።
1)አሁንም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከፍተኛ የሆነ ድብደባ፣ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ስለሆነ፣ አሁንም ህይወታችን አደጋ ላይ ነው። በዚሁ በቃጠሎ ምክንያት በሌላ መዝገብ ከተከሰሱ ወንድሞቻችን ውስጥ አርማዬ ዋቄ የተባለ ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ፖሊስ ተደብድቦ ተገድሎ ቤተሰቦቹ በክስ ላይ ይገኛሉ
2) ከነሃሴ 1 እስከ 12/2009 ዓ•ም ድረስ ዐቃቤ ሕግ በሀሰት ያሰለጠናቸውን ምሰረክሮች ያሰማ ሲሆን ቀሪ ምስክሮችን ለማሰማት በሚል ከታህሳስ 23 እስከ ጥር 3/2010ዓ•ም በተከታታይ ቀናት ተቀጥረናል። እስካሁንም ፍርድ ቤት ቀርበው የመሰከሩ ምስክሮች በተፅዕኖ ስር ሆነው ዐቃቤ ሕግ ባሰለጠናቸው መሰረት የመሰከሩ ናቸው። ቀሪ ምስክሮችም እንደ ቀድሞ ምስክሮች የታሰሩና በተፅዕኖ ስር ሆነው የሚመሰክሩ ናቸው። አንዳንድ በዋስት እና በነፃ የተፈቱ ምስክሮችን በዐቃቤ ሕግና ፖሊስ "እኛ በምንላችሁ መሰረት ነው የምትመሰክሩት" እየተባሉ ፣"ይህን ካደረጋችሁ ከቀድሞ ክሳችሁ ነፃ ትባላላችሁ" እያሉ በመደለል እንዲሁም፣ የተለያየ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰባቸው እንደሆነ አረጋግጠናል። ይህንን በተፅዕኖና ምስክሮችን በማስገደድ የሚደረግ አመሰካከር እንድትታዘቡልን ጥሪ እናቀርባለን
3) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ባቀረበው ሪፖርት መሰረት በእኛ በተከሳሾች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙብን አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ግፊት እንድታደርጉልን እንጠይቃለን። ነገር ግን ኢሰብአዊ ድርጊት ከፈፀሙብን አንዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን በመሆኑ በሌላ ገለልተኛ ወገን ምርመራው እንዲካሄድ እንጠይቃለን
4) ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኙ ኤምባሲዎች ይህንን በሀገራችን እየተፈፀመብን ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት እንድትቃወሙልንና አሁንም ህይወታችን አደጋ ላይ በመሆኑ የድረሱልን ጥሪ እናቀርባለን።
5) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን ምርመራ አረጋግጫለሁ ብሎ ባቀረበው ሪፖርት ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ማድረግ ሲገባው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን የወንጀል ምርመራ ክፍልና የህክምና ባለሙያዎች አስፈላጊ ምርመራ በማድረግ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል አስተላልፈው የተደረሰበትን ድምዳሜ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮምሽን እንዲያቀርቡ ምክረ ሀሰብ ቀርቧል በማለት ያቀረበው ሪፖርት ላይ በጣም ቅር ተሰኝተናል።
ምክንያቱም በሕግ ሊጠየቁ የሚገባቸው አካላት በሕግ ሊጠየቁ ይገበል ማለት ሲገባው፣ ጉዳዩን ተከታትሎ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ሲገባው በጣም ተለሳልሶ የፍራቻ የሚመስል መደምደሚያ ሪፖርት በማቅረቡ ቅር ተሰኝተናል።
#ለአፍሪካ ህብረት
#ለአሜሪካ፣ ለብሪታኒያ፣ ስውይድን፣ ካናዳ፣ ኖርዎይ ኤምባሲዎች
#ለማህበራዊ ሚዲያ፣ ለኤፍ ራዲዮዎች፣ ኢቢሲና ሌሎች ሚዲያዎች ይድረስልን
#ወደእንግሊዝኛና አረብኝ ተተርጉሙ ለዓለም ህዝብ ይድረስልን

ሕሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸው ተሰማ


በኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሕሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ባለማግኘታቸው ችግር ላይ እየወደቁ መሆኑን ቢቢሲ ዘገበ።
መድሃኒት አስመጪዎች የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻላቸው በተለይ የልብና የስኳር ህሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ለማግኘት ተቸግረዋል።
ቢቢሲ በአዲስ አበባ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው ህሙማን የሚፈልጉትን መድሃኒት ማግኘት ባለመቻላቸው ችግር ላይ እየወደቁ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይም የስኳርና የልብ ህሙማን እለት እለት መድሃኒት የሚፈልጉ ቢሆንም በየመድሃኒት ቤቶቹ ዞረው ማግኘት አልቻሉም።
ለቢቢሲ አስተያየቱን የሰጠው ግሩም ፈለቀ የተባለ የስኳር ህመምተኛ ካለፉት 3 ወራት ወዲህ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የኢንሱሊን እጥረት እንዳጋጠመው ነው የገለጸው።
መድሃኒቱ ቢገኝ እንኳ በውድ ዋጋ የሚሸጥበት ሁኔታ ተፈጥሯልም ሲል ምሬቱን ይገልጻል።
በተለይም በግል መድሃኒት ቤቶች የስኳር ሕመም መድሃኒት ማግኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአንድ ግዙፍ የመድሃኒት አስመጪ ኩባንያ ምክትል ዳይሬክተር እንዳሉትም በአጠቃላይ በመድሃኒት ላይ ያለው እጥረት ዋነኛው ችግር የውጭ ምንዛሪ ነው።
ከዚህ በፊት ጊዜ የማይሰጡ እንደ ኢንሱሊን አይነት መድሃኒቶችን ለማስገባት ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ይፈቅድ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከልክሏል ብለዋል።
የመድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ተስፋ ሚካኤል አፈወርቅ በበኩላቸው እነዚህ መድሃኒቶች ለመንግስት ሆስፒታሎችና መድሃኒት ቤቶች በበቂ ሁኔታ እየቀረቡ ናቸው ብለዋል።
የግል አስመጪዎች በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት መድሃኒት ባለማስገባታቸው ጫናው በመንግስት ላይ ወድቋል ባይ ናቸው።
ኢሳት ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት አጋጥሞታል።
በአሁኑ ጊዜም 7 መቶ ሚሊየን ዶላር ብቻ የመጠባበቂያ ክምችት ሲኖረው ይህም ለ3 ሳምንት ብቻ የሚበቃ መሆኑ ነው የተገለጸው።
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያጋጠመው የሀገሪቱ አገዛዝ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እስከመሰረዝ መድረሱም ይነገራል።
ከዚሁም መካከል ከጅቡቲ አዲስአበባ ድረስ ይዘረጋል የተባለው የነዳጅ ማስተላልፊያ መስመር አንዱ ነው።
በጅቡቲ ወደብ የተጠራቀሙ ሸቀጦችም በነዳጅ እጥረት ምክንያት መንቀሳቀስ አለመቻላቸው ይነገራል።
ይህንኑ ችግር መሰረት በማድረግም የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ ይፋዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ የኢሳት ምንጮች መግለጻቸው ይታወሳል።
ሴትዮዋ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ መንግስት ኢትዮ-ቴሌኮምን የመሳሰሉ ትላልቅ የመንግስት ተቋማት ወደ ግል እንዲዞሩ ግፊት ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሏል።

African Union plans to repatriate 20,000 African migrants from salve tarde in Libya

EU to expel Ethiopians: leaked document says

A leaked document obtained by the Addis Standard says the European Union and the Ethiopian regime are close to signing an agreement to return Ethiopians in Europe who have not been granted refugee status.
The document says the Ethiopians will be returned voluntarily or otherwise.
Meanwhile, the African Union says it now plans to repatriate 20,000 African migrants in detention centres in government-controlled parts of Libya in the next six weeks – an increase on previous plans.
According to the BBC report, African governments are under pressure to act after TV reports showed sub-Saharan Africans being sold as slaves in the country.
The report said the AU said it was working to organise consular services for stranded migrants and landing rights for planes to fly them out of Libya.
Some countries have already begun flying their citizens back home.

Sunday, December 10, 2017

የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ

 የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች
...See More


የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ

በእለት ከእለት እንቅስቃሴያችን ቀላል ነገሮችን በቸልታ እናልፋቸዋለን፡፡ በመጨረሻ የእነዚህ ነገሮች ድምር ውጤት ከባድ የሆነ ችግር ላይ ይጥለናል፡፡ ለምሳሌ በቂ ውሃ አለመጠጣት፣ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የተመጣጠኑ ምግቦችን አለመጠቀም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለከባድ ችግር ያጋልጡናል፡፡ ከነዚህ ችግሮች መካከል አንዱ የኩላሊት ጠጠር ነው፡፡


በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው አይቀርም፡፡ ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣ ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል፡፡ እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡

✔ የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች

የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!! ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡
ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የምታዎቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው:- እነርሱም

• 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ”
• 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ”
• 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ “ቀረፋ” ናቸው፡፡

✔አወሳሰድ

• “ለሁለት ሳምንታት” “ማታ” ከመተኛታችን በፊት መጠጣት፡፡
• እንደ ጠጠሩ መጠን በአስር ቀን ውስጥ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡ ለሌሎች ማጋራት ደግነት ነው!!

ጤናዎ ይብዛለዎት!!!




…….
የመረጃ ምንጫችን “ቶፕ ኸልዝ ኒውስ ዶት ኔት” እና “ወይ ማወቅ ደጉ: የጤና አምድ” ናቸው፡፡

ለሌሎች ማጋራት ደግነት ነው!!

በኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲናነት ጉዳይ በተነሳው ብጥብጥ አንድ ሰው ተገደለ


የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ስለመሆኗ እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ አንድ ሰው ሲገደል 200 ያህል ቆሰሉ።
በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክ እንዲሁም በእስራኤልና ጋዛ ድንበር ላይ ከፍተኛ ግጭት ተከስቷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ኢየሩሳሌም የእስራኤል መዲና ነች አሜሪካም ኤምባሲዋን ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ታዞራለች ማለታቸው ግጭት እንደገና እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል።
በፍልስጤም በመሀሙድ አባስ የሚመራው የፋታህ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን በዚህ ወር መጨረሻ በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ እቅድ የያዙት የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ እንዳይመጡብን ብለዋል።
ባለስልጣኑ አክለውም በፋታህ ስም የትራምፕ ምክትል የሆኑት ሰው እንዳይመጡብን በፋታህ ስም እንጠይቃለን ብለዋል።
ማይክ ፔንስ አባስን ለማግኘትና በቤተልሄም ስብሰባ ለመቀመጥ ቀጠሮ ይዘው ነበር።
ይህ ስብሰባ ግን አይከናወንም ብለዋል የፍልስጤሙ ባለስልጣን ጅብሪል ራጁብ።
የእስራኤሉ የመከላከያ ሃይል በታንክና በጦር ጀቶች በመታገዝ የሃማስ ኢላማዎችን መደብደቡን ኢየሩሳሌም ፖስት ዘግቧል።
ከጋዛ ሰርጥ የተተኮሱ ሁለት ሚሳኤሎች ግን በእስራኤል ግዛት ሳይደርሱ መቅረታቸው ታውቋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋንና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሜር ፑቲን በስልክ ባደረጉት ውይይት የትራምፕ ውሳኔ በሰላምና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
እስራኤል ቀድሞውንም ኢየሩሳሌምን እንደ መዲናዋ ስትቆጥር ፍልስጤሞች በበኩላቸው በ1967ቱ ጦርነት በእስራኤል የተያዘችው ምስራቅ ኢየሩሳሌምን የወደፊቱ የፍልስጤም አስተዳደር መዲና ነች ብለው ያምናሉ።
እስራኤል በ1948 ከተመሰረተች ወዲህ ኢየሩሳሌም መዲናዋ እንደሆነች እውቅና ስትሰጥ አሜሪካ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የአሜሪካንን ኤምባሲ ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ለማዞር በትንሹ 2 አመት ሊፈጅ ኣንደሚችል መናገርቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ብጥብጡ ግን ከአሁኑ የሰው ሕይወት መቅጠፍ ጀምሯል።የእስራኤል ፖሊሶች በጋዛ ለተቃውሞ በወጡ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ አንድ የ30 አመት ወጣት ሲገደል በየአካባቢው በተደረገው ተቃውሞ ወደ 200 የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል።
በዮርዳኖስ፣ግብጽ፣ቱርክ፣ቱኒዚያ፣ኢራን፣ማሌዢያ፣ባንግላዴሽ፣ፓኪስታን፣አፍጋኒስታንናበሕንድ በምትተዳደረው ካሽሚር  ግዛት  የፕሬዝዳንት ትራምፕን ውሳኔ በመቃወም ከፍተኛ ሰልፍ ተካሂዷል።
በአንዳንድ ቦታዎች ሰልፈኞቹ የአሜሪካንን ባንዲራ አቃጥለዋል።

wanted officials