የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ወታደሮቹ በኢትዮጵያ መሬት ላይ የሚገኘውን ጎንግ ወንዝን አልፈው ኮርመር፣ ኮረደም ገላዋንን ከያዙ በሁዋላ ደሎንም ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ከሰአት በሁዋላ በደረሰን መረጃ ደግሞ ወታደሮቹ ከ30 እስከ 40 ኪሜ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው ገብተዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያና የሱዳን የመከላከያ ባለስልጣናት የተነጋገሩ ቢሆንም፣ የሱዳን የመከላከያ አባላት “ከገዳሪፍ መንግስት ታዘን የመጣን በመሆኑ አካባቢውን ለቀን አንወጣም” የሚል መልስ ሰጥተዋል። ስብሰባውም ያለውጤት ተበትኗል።
ወታደሮቹ ከባድ መሳሪያዎችን ታጥቀው መግባታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የሱዳን ወታደሮች በደንብ ተደራጅተው መግባታቸውንና እስካሁን ከኢትዮጵያ በኩል ምንም የአጸፋ መልስ አለመሰጠቱን የገለጹት ምንጮች፣ ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት 24 ክፍለ ጦር ከባድ መሣሪያዎችን በመያዝ ወደ ቦታው ተጉዞ ፊት ለፊት ተፋጦ እንደሚገን ምንጮች ገልጸዋል። የአካባቢው አርሶአደሮችም የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በመያዝ ወደ አካባቢው ተጉዘዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል።
ምሽት ላይ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተው ደግሞ የሱዳን ጦር ደለሎን ተቆጣጥሯል።

No comments:
Post a Comment