Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 4, 2017

አዜብ ያለቀሰችው ለመለስ ነው ወይስ ለስብሓት?





ከናትናኤል አስመላሽ
አዜብ መለስ የሞተ ጊዜ ያሳየችው የለቅሶ አይነት እና የእምባ ብዛት የሚገርም ነበር፣ እውን አዜብ ያኔ ለመለስ ነበር ያለቀሰችው? መልሱ አይደለም ነው። አዜብ ካንጀትዋ ያስለቀሳት የመለስ መሞት ሳይሆን የስብሓትን በሂወት መኖር እና የመለስ አዜብ ቡዱን ስልጣን በስብሓት ቡድንን መነጠቅን ያሳስባት ስለ ነበር ብቻ ነው። በመለስ እና በሳሞራ ከሁሉም ስልጣኖች የተገለለው ስብሓት ነጋ ቂሙን እንደ ያዘ በመለስ ቡድን ላይ የቛጠረውን ጥላቻ የመለስን ሬሳ ከውጭ ሲመጣ ኤርፖርት ባለመገኘት በተግባር አሳይተዋል፣ ቂሙም ተወጥተዋል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
.እነ አዜብ በስብሓት መሸነፋቸው ካንጀታቸው ሲያለቅሱ ስብሓት የመለስ ቀኝ እጅ የነበረው የደህንነቱ ሃላፊ ወልደስላሴን አስሮታል። ከመለስ መሞት ደቂቃዎች ቦሃላ የወልደስላሴን እስር የሰማችው አዜብ፣ ከአውሮፕላን እስከ ቤተመንግስት ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ አይነት ለቅሶ አሳይታለች፣ ይህ ብቻ አይደለም፣ ከትግራይ የመጡት አንጋፋ ታጋዮች እና ካድሬዎች በሁለት ቤት ውስጥ ለቅሶ ሲደርሱ ነበር፣ አንድ ሰው በሞተ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ለቅሶ ሁለት ቤት ይደርሱ ነበር፣ ለዚህም ምስክራች ቄስ ገብረገርግስ ናቸው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አቶ ስብሓት ነጋ ስልጣኑን በእጃቸው ማድረጋቸው ሲታወቅ፣ የአዜብ እርምጃ አሜን ብሎ መገዛትን ብቻ ነበር፣ የስብሓት ነጋ ወዳጅ ጌታቸው አሰፋ የመቀሌው ህውሓት በወንድማቸው በኩል መከታተል ቀጥለው በመለስ ራኢ ስር ያሉትን ለማሽመድመድ ጊዜም አልፈጀባቸውም። የአቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ዳኒኤል አሰፋ የመቐለ ከንቲባ ናቸው።በሙስና ሊከሰሱ የተዘጋቹ የነ አዜብ ቡድን አንድ በአንድ ተለቅመው ወህኒ ወርደዋል፣ ከነዚህ መካከል እቺ አገር ወደየት እየሄደች ነው ብሎ ፍርድቤት ውስጥ የተናገረው የቀድሞ የግሙርክ ሃላፊ ገብረዋህድ አንዱ ነው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ባለፉት ወራቶች ህውሓት ግምገማ ተቀምጦ አሸናፊው ቡድን ተሸናፊውን ቡዱን ለመጣል ብዙ ካንገራገረ ቦሃላ አሁን ይፋ በማድረግ የመለስን ቡድን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። አዜብ ስትፈራው የነበረውን የስብሃት ነጋ ዱላ ደረሰባት፣ አባይ ወልዱ የአዲስ አበባው ህውሓት ከትግራይ ህዝብ ለመነጠል ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀረ፣ የስብሓት ቡዱን የአባይ ወልዱን ሚስት ከትግራይ ራቅ ባለ ቦታ በአምባሳደርነት በአስትራልያ አስቀመጠ፣ አሁን ከመለስ ሞት ይልቅ የስብሓትን የስልጣን መጨበጥ ካንጀት ያስለቀሳት አዜብ ከህውሓት ተባረረች፣ አባይም ሳይወድ በግዱ የመለስን ራኢ ሳያሳካ ከስልጣኑ ወረደ።በነ አዜብ እና አባይ ስር ያሉት የትግራይ የዞን አመራሮች እጣ ፈንታም ገና ያላለቀ ድራማ ነው። የመለስ ቡድን ከትግራይ ከስር ተነቅሎ በስብሓት ቡዱን መተካቱ አይቀሬ ነው።
.~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ስብሓት ስልጣን ወይሞት በማለት አሁንም ድረስ የህውሓትንም የፌደራል መንግስትንም ያሽከረክራል፣ ተረኛው ሳሞራስ፣ እጁን ይሰጣል ወይስ አገር እና ህዝብን ጨርሶ ራሱን ያጠፋል፣ የስብሃት ነጋ ቀጣዩ ትልቅ የቤት ስራ ሳሞራ ይሆናል፣ ከዛ በፊት በህውሓት ተጠፍጥፈው የተሰሩት የብአዴን እና የኦሆዴድ እጣም በስብሓት ነጋ ሳይሆን አይቀርም። የስብሓት ትልቁ ኢላማዎች አባዱላ ገዱ እና በረከት ሳይሆኑ አይቀሩም። ያኔ ስብሓት እንዳለው ኢህ አዴግ ራሱንበራሱን ያጠፋል ማለት ነው; ጊዜ ለኩሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials