Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, December 10, 2017

የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ

 የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች
...See More


የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ

በእለት ከእለት እንቅስቃሴያችን ቀላል ነገሮችን በቸልታ እናልፋቸዋለን፡፡ በመጨረሻ የእነዚህ ነገሮች ድምር ውጤት ከባድ የሆነ ችግር ላይ ይጥለናል፡፡ ለምሳሌ በቂ ውሃ አለመጠጣት፣ እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የተመጣጠኑ ምግቦችን አለመጠቀም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለከባድ ችግር ያጋልጡናል፡፡ ከነዚህ ችግሮች መካከል አንዱ የኩላሊት ጠጠር ነው፡፡


በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው አይቀርም፡፡ ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣ ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል፡፡ እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡

✔ የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች

የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!! ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡
ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የምታዎቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው:- እነርሱም

• 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ”
• 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ”
• 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”
• ግማሽ የሻይ ማንኪያ “ቀረፋ” ናቸው፡፡

✔አወሳሰድ

• “ለሁለት ሳምንታት” “ማታ” ከመተኛታችን በፊት መጠጣት፡፡
• እንደ ጠጠሩ መጠን በአስር ቀን ውስጥ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡ ለሌሎች ማጋራት ደግነት ነው!!

ጤናዎ ይብዛለዎት!!!




…….
የመረጃ ምንጫችን “ቶፕ ኸልዝ ኒውስ ዶት ኔት” እና “ወይ ማወቅ ደጉ: የጤና አምድ” ናቸው፡፡

ለሌሎች ማጋራት ደግነት ነው!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials