Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 16, 2017

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ፣ በኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎቶች ላይ አፈና እያካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ





በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ፣ በኢንተርኔት እና ስልክ አገልግሎቶች ላይ ደፈቃ ወይም አፈና እያካሄደ እንደሚገኝ ታወቀ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋው ስርዓቱ፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጥ፣ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ለማድበስበስ እየሞከረ እንደሚገኝ የገለጹት መረጃዎች፣ አፈናው ከክልሎች በተጨማሪም በአዲስ አበባ መስተዋሉን መረጃዎቹ አረጋግጠዋል በተለይ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት አስቸጋሪ ሆኖ እንደዋለ የጠቆሙት መረጃዎቹ፣ በቀጥታ መስመርም ሆነ በኢንተርኔት ከውጭ ሀገር የሚደወሉ ስልኮች ከፍተኛ የኔትዎርክ ችግር እንደገጠማቸው ከመረጃዎቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል::
ከሰኞ ዕለት ጀምሮ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆናቸው ለኢንተርኔት መቋረጥ ሰበብ ተደርገው ተወስደዋል አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሰልፎቹን ተከትሎ የሚፈጽማቸው ግድያዎች ተድበስብሰው እንዲቀሩ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ነቀምት፣ በደሌ እና ማንዲ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን ተከትሎ፣ በአካባቢዎቹ የኢንተርኔት አገልግሎት እዲቋረጥ ተደርጎ መዋሉን መረጃዎች ጠቁመዋል ስርዓቱ ተቃውሞ በተነሳበት ቁጥር እንዲህ ያለውን እርምጃ የሚወስደው፣ የሚፈጽመው ግድያ እና እስራት እንዳይጋለጥበት ስለሚፈልግ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ ላለፉት አራት ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የቆየው የኢንተርኔት አፈና፣ አድማሱን አስፍቶ ዛሬ በአዲስ አበባ መስተዋሉም ታውቋል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በተወሰኑ አካባቢዎች የኢንተርኔትም ሆነ መደበኛው የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል በተለይ ከሰባት እና ስምንት ሰዓት ጀምሮ፣ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የስልክም ሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት አስቸጋሪ እንደነበር፣ ችግሩ ያማረራቸው ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል ያለ ማቋረጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ በስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ፍርሃት የፈጠረበት ሲሆን፣ በተለያዩ አካባቢዎችም የታጠቁ የጸጥታ አካላት እንዲሰማሩ ተደርጓል::

BBN NEWS

No comments:

Post a Comment

wanted officials