Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 16, 2017

ግልፅ ደብዳቤ ለእግዚአብሄር | ከሔኖክ ዘውዴ

ይድረስ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ የአብረሃም አምላክ የቅድስት ድንግል ማሪያም ልጅ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አንዲሁም የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች በምታምኑት እና በምታመልኩት አምላክ እንዲታይልኝ የፃፍኩት ግልፅ ደብዳቤ ነው።
ይህንን ደብዳቤ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ነገር ቢኖር ብዙ ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች ብዙ ጊዜ ግልፅ ደብዳቤ የሚፅፉት ለሃገር መሪ ወይም ጉዳዩ ይመለከተዋል ለሚሉት ክፍል ሲሆን እኔ ግን በአሁን ሰአት በሃገራችን ላይ ያለው የፖለቲካ ቀዉስ ሃገራችንን ወደ ማንፈልገው የዘር መጠፋፋት እና እልቂት እያመራች ስለሆነች ይህን ጉዳይ በአሁን ጊዜ ሃገራችንን የሚያስተዳድረው መንግስት ብዬ ለመጥራት ትንሽ ስለሚከብደኝ ነፍሰ በላ አስተዳደር በኢትዮጵያኖች ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሱት ኢሰባዊነት ድርጊት ተቃዉሜ በእግዚሀብሄር ፊት ይህንን የክስ ደብዳቤ እንዲታይልን ነው።
በኢትዬጵያ ወይም በውጭ ሃገር ያላችሁ የፖለቲካ መሪዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የሃሳብ ልዩነት እና ግለኝነታችሁን ትታቹ ወደ አንድ ሃሳብ መታችሁ ሀገራችን ወደ ማትወጣው አዘቅጥ ዉስጥ ከመግባቷ በፊት የሚቻላችሁን እንድታደርጉ በእግዚሀብሄር ስም እጠይቃችዋለዉ።
በሊቢያ የሚደረገው የሰው ሽያጭ ልክ ደብረዘይት መንገድ ዳር እንደቆመ ከሰል የሰዉን ልጅ 200,300 ሲገመቱ ማየት ከዚህ በላይ ሊያም የሚችል ነገር አለ ብዬ ማሰብ ይከብደኛል።
በዩናይትድ ኔሽን እና በአፍሪካ ዩኒየን በተለያዩ መድረኮች ላይ ወይም በአለም ፍርድ ቤቶች ድምፃቸዉን የሚያሰማላቸው ወይም ፍትህ ያገኛሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።
ፍርድን ሳያጓድል የሚሰጥ አንድ እግዚሀብሄር ብቻ ነው።
t

 

No comments:

Post a Comment

wanted officials