Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 5, 2017

የ2018 የሩሲያ የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ



32 ሃገራት የሚሳተፉበት ሩሲያው የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል የይፋ ሆኗል።
የአምስት ጊዜ አሸናፊዋ ብራዚልን ጨምሮ ያለፈው ጊዜ አሸናፊዋ ጀርመን፣ ሩሲያ፣ አርጀንቲና፣ አውስትራሊያ፣ ቤልጂም፣ ኮሎምቢያ፣ ኮስታሪካ፣ ክሮሺያ፣ ዴንማርክ፣ ግብጽ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ አይስላንድ፣ ኢራን፣ ጃፓን፣ ሜክሲኮ፣ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ፓናማ፣ ፔሩ፣ ፖላንድ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሴኔጋል፣ ሰርቢያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ስፔን፣ ስዊዲን፣ ስዊዘርላንድ፣ ቱኒዝያ እና ኡራጋይ ናቸው በ2018ቱ ዓለም ዋንጫ ላይ የሚሳተፉት።
2018 FIFA World Cup.svg

ማራዶና በዝግጅቱ ቦታ ተገኝቷል
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የቀድሞው አርጀንቲና አጥቂ ዲያጎ ማራዶና ተገኝቶ ነበር። የብራዚሉ ፔሌም በቦታ ከተገኙ እንግዶች አንዱ ነው።
ሮናልዲንሆ፣ ክላረንስ ሲዶርፍ፣ ጄይ ጄይ ኦካቻ፣ ዲጎ ፎርላንና ሌሎች ተጫዋቾችም በስፍራው ተገኝተው ነበር።
ስለእያንዳንዱ ምድብ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይከተሉ
ምድብ አንድ ፡ ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ እና ኡራጓይ
ምድብ ሁለት፡ ፖርቹጋል፣ ስፔን፣ ሞሮኮ እና ኢራን
ምድብ ሶስት፡ ፈረንሳይ፣ አውስትራሊያ፣ ፔሩ እና ዴንማርክ
ምድብ አራት፡ አርጀንቲና፣ አይስላንድ፣ ክሮሺያ እና ናይጄሪያ
ምድብ አምስት፡ ብራዚል፣ ስዊዘርላንድ፣ ኮስታሪካ እና ሰርቢያ
ምድብ ስድስት፡ ጀርመን፣ ሜክሲኮ፣ ስዊዲን እና ደቡብ ኮሪያ
ምድብ ሰባት፡ ቤልጅየም፣ ፓናማ፣ ቱኒዝያ እና እንግሊዝ
ምድብ ስምንት፡ፖላንድ፣ ሴኔጋል፣ ኮሎምቢያ እና ጃፓን

No comments:

Post a Comment

wanted officials