Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 12, 2017

የአሸባሪዎች ምንጭ በተባሉ 8 ሀገራት ላይ የተጣለው የጉዞ እገዳ ሕግ በአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጸደቀ


)
የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ሕግ አጸደቀ።
ውሳኔው ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ሲታወቅ በሁለት ግዛቶች የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውሳኔውን ለመቀልበስ ክርክር በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ሉ የተባሉ 
ባለፈው መስከረም ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበውን የጉዞ እገዳ ሕግ ሙሉ ለሙሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሲያጸድቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የቀረበውንና በ8 ሀገራት ላይ የተጣለውን የጉዞ እገዳ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔውን ያሳለፈው ትላንት ሰኞ ነበር።
ሕጉ ከቻድ፣ኢራን፣ሊቢያ፣ሰሜን ኮሪያ፣ሶሪያ፣ቬንዙዌላ፣ሶማሊያ እንዲሁም ከየመን ወደ አሜሪካ ለመምጣት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው እገዳ ያስቀምጣል።
ከዚህ በፊት ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተንቀሳቀሱበት ወቅት በሀገሪቱ ሁለት ግዛቶች ባሉ የሀገሪቱ ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ እንዳይሆን እገዳ ተጥሎበት እንደነበር ይታወሳል።
በአብዛኛው የእስልማና እምነት ተከታይ ሀገራት ላይ የጉዞ ማዕቀብ ለመጣል ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲያደርጉ ለነበረው ጥረት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰኞ ውሳኔ ጊዜያዊ ደስታና የአሸናፊነት ስሜት ሊሰጣቸው ቢችልም የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ግን ይግባኝ ሊጠየቅበት እንደሚችል ታውቋል።–እስከዛው ግን ተግባራዊ መሆኑ ይቀጥላል።
የትራምፕ አስተዳደር ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የጉዞ እገዳ ለማድረግ ስልጣን አለው ብሎ ያምናል።
ሕጉ እንዲጸድቅ መከራከሪያቸውን ያቀረቡት የሕግ ጠበቃው ጄኔራል ኖኤል ፍራንሲስኮ በፍርድ ቤቱ ሲናገሩ የሀገሪቱ ህገ መንግስትም ሆነ የተወካዮች ምክር ቤት ሕጎች ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈልጉ ሰዎችን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማገድ ይችላል ሲሉ ተከራክረዋል።
ሕጉ ሙስሊሞችን ለማገድ የወጣ ነው ለሚለው ነቀፌታም ተሻሽሎ በቀረበው ሕግ ከተዘረዘሩት ሀገራት ውስጥ በአብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች የማይገኙበት እንዳሉ መጥቀሳቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።
ሕጉ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ወቅት ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንቱ የአንድን እንግሊዛዊ በእስልምና ላይ ያነጣጠሩ ሶስት ትዊቶችን መልሰው ትዊት ማድረጋቸው ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
ከዚህ በፊት እንደሆነው ሁሉ በሃዋይና በሜሪላንድ ግዛቶች ሕጉን ለማስቆም ክርክር በመደረግ ላይ ሲሆን በዚህ ሳምንት በይግባኝ ፍርድቤቶች ሊታይ እንደሚችል ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials