Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 12, 2017

የጋይንት የ26 አመት የቁልቁለት ጉዞ(ከጋይንት የተላከ)

የጋይንት የ26 አመት የቁልቁለት ጉዞ(ከጋይንት የተላከ)
ባንድ ወቅት ደበርታቦር ላይ በነበረ የሩጫ ውድድር ፡ጋይንት “አንበሳው ጋይንት” ተብሎ በሚጠራበት ዘመን ፡ አወዳዳሪዎች “የጋይንት ሯጮች ወደ መሮጫው ቦታ ኑ!” ብለው በማይክራፎን ሲናገሩ በወቅቱ የነበሩት የጋይንት አውራጃ አስተዳዳሪ “ጋይንት ያሯሩጣል እነጅ፡አይሮጥም” አሉ ይባላል፡፡ ጋይንት አንበሳ፤ ልበ-ሙሉ፤ደፋርና በጀግንነት የተሞላ፡ የአፄ ቴዎድሮስ ቀኝ እጅ የፊትአውራሪ ገብርየ ሀገር፡ ከገጠመ ወደኋላ የማይል፡ እንጅ ቦቅቧቃ ፈሪ አይደለም ለማለት ፈልገው ነው፡፡ ሩጫ እንደዛሬው ቢዝነስ ሳይሆን በአካል የጠነከረ በአእምሮው የዳበረ ፡ ሀገሩን የሚወድ በኢኮኖሚውና ፖለቲካው፡ ንቁ ተሳትፎ ያለው ወጣት ለማፍራት በሚፈለግበት ዘመን ነው፡ ይህ የሆነው፡፡ የአሁኑ መንግስት ግን ወጣቱ በጫትና መጠጥ የደነዘዘ፡ በግዴለሽነት የተሞላ፡ እራሱን የጣለ ፡ስለሀገሩም ሆነ ስለ ፖለቲካው ምንም ደንታ የሌለው፡ ምንም አይነት ጥያቄ የማይጠይቅ፡ ዝም ብሎ የሚገዛ፡ ለማድረግ 26 አመት ሙሉ ህወሀት ድብቅ ሴራ ስትጎነጉን ኖራለች፤ ምንም እንኳን የባሰ እሳት የሆነ ህወሀትን መቆሚያ መቀመጫ የነሳ ጠንካራ ትውልድ በህዝብጥረት ቢፈጠርም፡፡አሁን ላይ ሳስበው ፡ ከየት እንደምጀምር ይጨንቀኛል፡፡ 



ግፉና የኋሊት ጉዞው ዘግናኝ ነው፡፡ ጋይንት፡ በህወሀት ትእዛዝ በጉጅሌው ፡ብአዴን ተላላኪነት፡ በጥቂት የመሀይማን ሆዳም አባላት አስፈፃሚነት ፡ ደረጃውን የጠበቀ እስር ቤት ከ10፡አመት በፊት ተገንብቶለታል (ይሄ በኢቢሲ አልተነገርም፣አልተለፈፈም፡፡)፡፡ ጋይንትን ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ ከማንኛውም ማህበረሰብም ሆነ አካባቢ ፡ ለየት የሚያደርገው፡ ሰው ሰራሽ የማደህየት ወንጀል ተፈፅሞበታል፡፡ አሰቃቂ ፡ የጭቆና፡ የተመፅዋችነት ስነ-ልቦና እንዲያድርበት በህወሀት-ብአዴን ተፈርዶበት የጣረሞት ጉዞ ይጓዛል፡፡ አንድን ፈረንጅ ወይም ነጭ ዜጋ፡ ብር ልስጥህ ወይም በሆነ ነገር ልደግፍህ ብትሉት “ለምን? እኔ እራሴን የቻልኩ የማንንም ድጋፍ የማልፈልግ ሰው ነኝ”የሚል መልስ ይሰጣችኋል፡፡ ምክንያቱም ከልጅነቱ ጀምሮ እንዴት እራሱን የቻለ ሰው መሆን እንዳለበት ቤተሰቡም ሆነ መንግስት ስላስተማሩት፡፡ ወደ ጋይንት ስንመጣ “ጋይንት በልማት ጎዳና ነው” በማለት ኤፍ.ኤች.አይ፤ ሲ.ፒ.ኤ.አር፤ ወርልድ ቪዥን….በሚባሉ ድርጅቶች ህብረተሰቡን ያላንዳች ርህራሄ ጥገኛ፡ ተመፅወችና የእርዳታ ለማኝ እንዲሆን 26 አመት ዝቅጠት ውስጥ እንዲገባ ፈረዱበት፡፡ ጋይንት ማለት ህወሀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከዋልካ ጭቃ+በስኳር ተላቆ፤ጤፍ እንጀራ በእርጎ የበሉበት፤ ቅማል የወረሰውን ቁምጣቸውን ጥለው፡ ንፁህ ልብስ የለበሱበት፤ ሰውነታቸውን የታጠቡበት ሀገር ስለመሆኑ ማንንምመጠየቅ አያስፈልግም (አቦይ ስብሀት፤ ስዩም መስፍን፤ በረከት ስመኦን….ታዉቁታላችሁ፤ ታስታዉሱታላችሁ)፡፡ 

ነገር ግን ይሉኝታ በተፈጥሮው የማያውቀው ህወሀት፡ የጭካኔ በትሩን ጋይንት ላይ ሲያሳርፍ ብዙ ጊዜም አልወሰደበት፡፡ባንድ ወቅት፡ ገበሬወችን ለማደህየት በማሰብ ህወሀት ከማእከል ለሆዳሙና ምንመ አርቆ ማየት ለተሳነው የወቅቱ ብአዴን መላ ብላ የዘየደችው ነገር እንኳን የአንድ ሀገር ዜጎች የትኛውም አለም ላይ ተፈፅሞ አያውቅም፡፡ ገበሬዎችን “እርዳታ የምንሰጣችሁ በሚኖራችሁ የበሬ ብዛት ይወሰናል” በማለት፤ ገበሬዎች ፡ በሬዎቻቸውን እንዲሸጡ ፤ በቀጣይም ምንም ማረስ ስለማይችሉ፡ ሙሉ በሙሉ በድህነት ውስጥ ከወደቁ እንደፈለግን እናስተዳድራለን በሚል ቁንፅልና ጭካኔ የተሞላበት ሀሳብ ፤ በሬዎቻቸውን እጅግ በወረደ (በርካሽ) ዋጋ ለህወሀት ወታደር ቀለብና ለህወሀት ነጋዴዎች እንዲሸጡ ተደረጉ፡፡በ1989 ዓ.ም አካባቢ ተስፋዬ፡ የተባለ አረመኔ ከትግራይ ወደ ጋይንት በእንግሊዝኛ አስተማሪነት በማምጣት፡ ወጉን ባህሉን እነዲሁም የከተማውን መውጫ መግቢያ ሁሉ በደንብ እንዲያጠናና እንዲሰልል፡ ከተደረገ በኋላ የከተማው አስተዳደር በመሆን የጋይንትን ህዝብ የድህነት፡ የመከራና የጭቆና ጉዞ ያፋጥነው ጀመር፡፡ ተስፋዬ እንደመጣ በደንብ አማርኛ እንኳን፡ መናገር አይችልም ነበር፡፡ 

በነገራችን ላይ የጋይንት ሰው ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ “ከሌላ አካባቢ የመጣ ሰው ነው” ከታባለ የመንከባከብና በርህራሄ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ወዲያዉኑ ከማህበረሰቡ ጋር እንዲቀላቀልና አብሮ መኖር እንዲችል የማድረግ ልዩ ተሰጥኦ አለው፡፡ የጅኦግራፊ እስተማሪ የነበረው “አሰፋ” ኦሮሞ ነበር፡፡ ነገር ግን አሰፋ ኦሮሞ ስለሆነ እንደ ተስፋዬ ስልጣን አልተሰጠውም፡፡ጋይንትን እንደ ስዩም በላይ፤ ዘመነ፤ ሁሴን ኢብራሂም፤ ( አምባቸው ፡ የጎማጣ ሰፈሩ ወፍጮ በሙስና ያስተከለው)…..የመሳሰሉት ያካባቢው፡ አርቀው ማሰብ የማይችሉት ድውያን፤ አስፈፃሚነት 26 አመት የድህነት፤ የጨለማ የስቃይና የግፍ አመታትን ተጓዘ፡፡ ህወሀት ወያኔ ከፈፀማቸው ወንጀሎች ከብዙው በጥቂቱ የሚከተሉትን እንይ፡-1. ጋይንት እጅግ ሀብታም ሀገር ነው፡፡ ማንም ሰው በዚህ ቅፅበት ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ የደን ሽፋኑን ማየት ይችላል፡፡ ባለፉት 25 አመታት ከወረዳው ከ4.000.000.000 (አራት ቢሊዮን ብር) የሚገመት ደን በመጨፍጨፍ፡ በመላው ሀገሪቱ ለሚካሄደው የመብራት እና ስልክ ግንድ (ፖል) እንዲሁም ትግራይ ውስጥ ለተቋቋመው የወረቀት ፋብሪካ ግብአት ሲያቀርብ ኖሯል፡፡ 

ለዚህ ውለታውም 26 አመት ሙሉ እርደታ ተመፅውቷል፡፡2. አንዱን ቅንጣት የመንገደኞች ማረፊያ እና የህዝብ መዝናኛ የነበረውን “ነፋስመውጫ ሆቴል”ን እንዲከስርና ለካድሬ ሴራ መሸረቢያ፡ እንዲሆን በማድረግ ህወሀት ውለታዋን ስትመልስ፤ ቲኒሽ አለፍ ብሎ ማሰብ የማይችለው ሎሌው ብአዴን ከተለያዩ የጋይንት ገጠራማው ክፍል የሚያመጣቸው አስተዳዳሪዎች፡ ያንን ታላቅ ሀገር፡ ለዚህ ድህነትና ውርደት አበቃው፡፡3. ጉና ተራራ አካባቢ ወረቀት ፋብሪካ ፤ የችፑድ ፋብሪካ (ጥሬ እቃው ከላይ እንደገለፅኩት በአይን የሚታይ) ፤የመስታወት ፋብሪካ፤ የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካ (ቆዳተሰብስቦ ወዴት እንደሚጫን እናውቃለን) ፤ የአረቄ ፋብሪካ (ጥሬ እቃውን ለዳሽን ቢራ ይጠቀሙበታል) ለመትከል የሚያስችል እምቅ የተፈጥሮ ሀብት እንዳለው በማወቅ በደርግ ጊዜ እነኝህን ፋብሪካዎች ለመትከል ሲታሰብ ፤ እነዚህ ፋጉርቶችና ጥላቢሶች ከየት እንደመጡ ሳይገመት፡ እቅዱን ሁሉ ሰብስበው በመውሰድ፤ ትግራይ ላይ ሁሉንም ፋብሪካወች ተከሉ፡፡ ልብ-በሉ፡ ጥሬ እቃ ከጋይንትና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች፡ ፋብሪካው ትግራይ፤ ሰራተኛው ትግሬ ብቻ፤ ባለቤቱ ኤፈርትወይም የትግራይ ክልል፡፡ ትግራይ ፋብሪካ አይተከል አላልንም፡፡


 ነገር ግን ጋይንት ላይ ጥሬ እቃ እየወሰዱ ትግራይ ላይ መትከልና ልዩ ተጠቃሚ ማደረግ ግን ያስተዛዝባል፡፡ እኔ ስበላ አንተ ተመልከት ማለት ግን ፍፁም እራስ-ወዳድነትና ስግብግብነት ነው፡፡4. በደርግ ጊዜ የተተከለ፡ ለ6 ተከታታይ ሰአታት ለመላው የነፋስ መውጫ ከተማ ህዝብ ፡ የመብራት አገልግሎት ፡ የሚሰጠውን ጀኔረተር ወደ ትግራይ በማሻገር ጋይንትን መበዝበዝ አሀዱ ብለዉ የጀመሩት ከ25 አመት በፊት ነበር፡፡5. ጋይንት አውራጃ ነበር፡፡ ይህም ማለት በአሁኑ ወቅት ዞን እየተባለ በሚጠራው አወቃቀር ማለት ነው፡፡ ያ እንዳይሆን ወደ ወረዳነት ዝቅ እንዲል ተደረገ፡፡ ዞን ቢሆን ኖሮ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችንም ኢነቨስትመንቶችን መሳብ ይቻል ነበር፡፡ ምክንያቱም በቂ ጥሬ እቃ (የተፈጥሮ ሀብት የታደለ በመሆኑ) ፤ ነገር ግን በሚፈፀምበት ፖለቲካዊ ተፅእኖ፤ እዛው ተወልደው ያደጉት ባለሀብቶች ሳይቀሩ ወረዳውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል፡፡ የነበረው ከተማ አድጎ፡ ሰፍቶና በልፅጎ ፡ የዘመናዊነት መገለጫ ፡ ለአካባቢው የገጠር ማህበረሰብ አገልግሎት ማቅረብ ሲገባውበተቃራኒው የገጠርነት ባህሪ እንዲኖረው ፡ በማድረግ፡ እንዲሁም ምንመ አይነት ጥያቄ ማንም ማቅረብ ባማይችልበት ደረጃ በስነ-ልቦና በመጉዳት ለማሰብ የሚዘገንን ሴራ ተፈፅሞበታል፡፡6. ህዝቡ የትምህርት ፖሊሲው ከ7ኛ ከፍል ጀምሮ በእንግሊዝኛ ይሁንልን ብሎ ቢጠይቅም፤ ከጫካ የመጣ መሀይም የብአዴን ካድሬ፡ ህወሀት የሰጠችውን የቤት ስራ ለመስራት፡ የእራሱን ህዝብ መስዋትነት በማቅረብ ፡ ሆዱን ሲሞላ ኖረ፡፡ ለመሆኑ የትኛው የአማራ ክልል ህዝብ እና ሙህር መንግስትን ልጆቼ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው፡ ይማሩልኝ ፡ ብሎ ጠይቆ ነው በግድ በአፍ መፍቻ ቋንቋ ካልተማርክ ተብሎ የተፈረደበት? የትምህርት ፖሊሲውን ያለህዝብ ፍላጎትና ሳይንሳዊ ጥናት በግዴታ አስፈፅሙ ሲባል ብአዴን እንዴት ይሄንን ሴራ ተገንዝቦ መቀልበስ ያቅተዋል (ለነገሩበትግሬዎች አይደል እያንዳንዱ መስሪያ ቤት የሚተዳደረው፡፡)7. የጋይንት ህዝብ በጀግንነቱ በታሪክ የሚታወቅ ፤ የሚከበርና የሚፈራ፡ የፊታውራሪ ገብርየ ሀገር ነበር፡፡ 
Image may contain: 1 person

ይሄንን ኩሩ እና ሩህሩህ፡ ህዝብ በ1977 ዓ.ም በተከሰተው ድርቅ ከተለያዩ የትግራይ፡ አካባቢዎች የመጡ ወገኖቹን የሚበላውን አካፍሎ፡ በችግር ቀን አብሮ መኖርን ያሳየ ህዝብ ከህወሀት ዘንድ ውለታው የተመለሰለት እራሱ ድህነትን እንዲለማመድ በማድረግ፣ ስልጣኔን እንዲተው በማድረግ ፣ ከ30 አመትና ከዚያ በፊት የነበረውን ህዝብ ፡ እንደ ፍቃዴ ዳምጤ ያሉሆዳም ካድሬዎች ሆዱን (ቦርጩን) እንጂ ጭንቅላቱን ማስፋት የማይችለው ተራ መሀይም እንዲገዛው ፈረዱበት፡፡በነገራችን ላይ ጋይንት ከ 4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጥሬ ሀብት የዘረፉት ወያኔዎች፡ ለዚህ ውለታ የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች ያለተሟሉለት ፡ ባዶ ግድግዳና ጣሪያ፡ ያለው የገጠር ፡ ሆስፒታል ሰራንላችሁ በማለት በህብረተሰቡ ላይ ተሳለቁ፡ ከበሮ ደለቁበት፤ለሚዲያ ሽፋን አዋሉት፤ ህዝቡን የበለጠ አዘናጉበት፡፡ በመሆኑም ደረጃውን የጠበቀ እስርቤት (ማረሚያ ቤት ለማለት ያስቸግራል) ከመገንባትውጭ የጋይንት ህዝብ ምንም ተጠቃሚ የሆነበት ሁኔታ የለም፡፡ ስለዚህ1. ጋይንት የክልልም ሆነ የሀገር አቀፍ ምክር ቤቶች ተወካዮች ከዚህ በኋላ የሚፈይዱለት ነገር አለመኖሩን በማወቅ፡ ውክልናቸውን መሰረዝ፤2. ህወሀት የጋይንትን ህዝብ ለማጥፋት ብትፈልግም በፈጣሪ ታምር እስካሁን ሊቆይ ችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ከዛሬ ነገ የተሻለ ይሆናል በሚል መዘናጋት ሳያስፈልግ የወደፊቱን አርቆ በማሰብ አስፈላጊውን ትግል መጀመር፤ የተጀመረውን አጠናክሮ መቀጠል፡፡

3. ከእለት ሆዳችሁ እና እንደ ህፃን ልጅ፡ በቶዮታ መኪና ለመንሸራሸር የህዝባችሁን መከራና ግፍ የምታራዝሙ የብአዴን አባላትና የወረዳው አመራር ከታሪክተጠያቂነት ብትድኑ መልካም ነው፡፡ እንደ እነ ወንድወሰን ከልካይ በሄዳችሁበት ሁሉ ሰው የሚወዳችሁ በመሆን ታሪከ ሰርቶ ማለፍ እንጅ፡ ወያኔ የነገረህን ተረት ተረት በማስፈፀም የእህትና ወንድሞችንህ ፡ ሰቆቃ ዞር ብላችሁ ብትመለከቱና ባታራዝሙ ጥሩ ነው፡፡ ህወሀት እንደሆን ቢያንስ እንኳን ብሄሩዋን ጠቅማለች (ለዚያም ነው ህወሀት ትግራይ ላይ ሙሉ ድጋፍ ያለው)፡፡ ሂድና የአድዋን ወረዳ ተመልከት፡፡

ለብአዴን ሆይ!! አድዋ ወረዳ ነች፡፡ ነገር ግን ውድድሯ፡ ከክልሎች ከተሞች ከእነ ባህርዳር ጋር እንጂ ፡ ህወሀት በኢቢሲ፡ እንደሚነግርህ የተመጣጠነ የከተሞች እድገት፡ አለ ብለህ “በራስህ” ህዝብ ላይ፡ ጥቁር ታሪክ አትፃፍ፣ ፡፡ (…ሀሀሀሀሀ….ባህር ዳር ከመቀሌ፤ ጎንደር፣ደብረታቦር፣ ፍኖተሰላም፣ ደሴ፣ ደ/ብርሀን፣ ደብረማርቆስ፣ሰቆጣ፣ ወልዲያ ከአቻዎቻቸው ከሽሬ፡ አዲግራትና አክሱም ጋር ሲወዳደሩ…ሀሀሀሀሀሀሀሀሀሀ…ድንቄም የተመጣጠነ የከተሞች እድገት)4. በተለያየ ጊዜ በክልሉ የተፈፀሙትን የኢኮኖሚ፤ ጤና እና ማህበራዊ እድገቶች ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ወደ ኋላ የቀራችሁ መሆኑን አለም-አቀፍ እንዲሁም የህወሀት ጥናቶች አረጋግጠውላችኋል፡፡ ሆዱ እንጅ ጭንቅላቱ መስፋት የማይችለው የብአዴን አተላ አባላት፤ ቆም ብላችሁ ሌሎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ጀግኖችን በማየት ፡ እናንተም አስፈላጊውን መስዋትነት ለህዝባችሁ በመክፈል የጥሩ ታሪክ ባለፀጋ ብትሆኑ ይሻላችኋል፡፡ በነገራችን ላይ፡ እጅጉን የተጠናከረ የውስጥ ትግል እያደረጋችሁ ያላችሁ ጀግኖቻችን፡ ስማችሁን በወርቅ ቀለም የምንፅፍበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጋይንት ህዝብ አሁንም ቢሆን በጀግንነቱ እንደማይታማ በ2008 ዓ.ም የወያኔን መንግስት ምጥ ውስጥ በማስገባት ማስጨነቁ ከብዙው የቅርብ ጊዜው ትዝታ ነው፡፡ ወደፊትም ቢሆን በዚህ ጀግንነቱ ከሌሎች አማራ ወንደሞቹ ጋር በመስራት የወያኔን ግባተ-መሬት እንደሚፈፅም ጥርጥር የለውም፡፡ ህወሃትም ብትሆን ጋይንትን በእጅጉ እንደምትፈራው ይታወቃል፡፡ ለዚያም ነው ከየትኛውም አካባቢ ቀድመው የጋይንትን ህዝብ ለችግር የዳረጉት፡፡
facebook Yeabesha Tilahun Tsehay

 

No comments:

Post a Comment

wanted officials