Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, December 5, 2017

የአዲስ አበባ አስተዳደር የእውቁን ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን የሙዚቃ ኮንሰርት አገደ

 በቅርቡ ጅራ የተሰኘ ነጠላ ዜማውን የለቀቀውና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ምርጥ ድምጻውያን መካከል በቀዳሚዎቹ መካከል ስሙ የሚጠራው ሃጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ ሊያደርገው የነበረው የሙዚቃ ኮንሰርት ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ መታገዱ ተሰማ::
በአዲስ አበባ ባለፉት 2 ወራት ውስጥ ሁለት ትላልቅ ኮንሰርቶች የተደረጉ ሲሆን ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ ሁሉ የሃጫሉ ሁንዴሳም ኮንሰርት መታገዱ እያነጋገረ ነው::
ከሃገር ቤት የሚተላለፈው ኢትዮፒካሊንክ የራድዮ ፕሮግራም በዝርዝር የዘገበውን ይመልከቱት::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን የሙዚቃ ኮንሰርት ማገዱን ባለፈው ቅዳሜ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ደግሞ የተዘረዘበት ደብዳቤ ደርሶናል:: ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቴዲ አፍሮ እና አጫሉ ሁንዴሳን ይህ መንግስት ለማየት እንደማይፈልግ ያረጋገጠበት ሁኔታ ነው ያለው:: አርቲስቶቹን ሕዝብ ይወዳቸዋል – መንግስት ግን ይፈራቸዋል::   (ዝርዝሩ እዚህ ይገኛል)

No comments:

Post a Comment

wanted officials