ኢትዮጵያዊቷ አንጋፋ ድምጻዊት ሐመልማል አባተ የመላው አፍሪካ የሙዚቃ አዋርድስ (AFRIMA) የ 2017 አሸናፊ መሆኗ ታወቀ:: (ዜናውን በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ)
በየዓመቱ በሚደረገውና ዘንድሮም በናይጄሪያው ትልቁ ኤኮ ሆቴል ማምሻውን በተደረገው ይህ የሙዚቃ አዋርድ መድረኩ የተመራው በሴንጋላዊው አንጋፋ ድምጻዊ ኤከን ነበር::
ሐመልማል አባተ የአፍሪካ ምርጥ ሴት ባህላዊ ድምጻዊት በሚለው ዘርፍ አሸናፊ ሆና ስታሽንፍ ከመካከለኛው አፍሪካ ምርጥ ወንድ ድምጻዊ ቻርለስ ሎኮ; ከመካከለኛው አፍሪካ ምርጥ ሴት ድምጻዊት ሞትነስ; ከምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ወንድ ድምጻዊ ኤዲ ከንዞ; ከምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት ድምጻዊት ናንዲ ሆነው አሸንፈዋል::
የዓመቱ ምርጥ አፍሪካ ድምጻዊም ዊዝ ኪድ ሆኗል::
ሐመልማል አባተ ይህን ታላቅ ውድድር ካሸነፈች በኋላ በፌስቡክ ገጿ ላይ “በአፍሪካና በመላው ዓለም ለምትገኙ አድናቂዎቼ
የመላው አፍሪካ የሙዚቃ አዋርድስ (AFRIMA) የ 2017 አሸናፊ በመሆኔ እንኳን ደስ አላችሁ! ስላደረጋችሁልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ
ሁላችሁንም እወዳችኃለሁ!::” ብላለች::
የመላው አፍሪካ የሙዚቃ አዋርድስ (AFRIMA) የ 2017 አሸናፊ በመሆኔ እንኳን ደስ አላችሁ! ስላደረጋችሁልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ
ሁላችሁንም እወዳችኃለሁ!::” ብላለች::
ሐመልማል ያደገችው አሰበ ተፈሪ ሲሆን ሙያዋን የጀመረችው በቤተ ክርስትያን ዘማሪ ሆና ነው። የመጀመሪያው አልበሟ የወጣው በ176 ዓ.ም. ነው።
ሐመልማል አባተ የሁለት ሴት ልጆች እናት ናት።
ከዓመታት በፊት በግንቦትወር በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል ቪላ ቤት በእሳት ቃጠሎ የወደመ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ወደ ቤቱ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ መዋዠቅ እንደሆነ ይጠቀሳል።
ከድምፃዊነትም አልፎ ሐመልማል የራሷን የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት አመል ፕሮዳክሽንስ በሚል ስም አቋቁማለች። ከሙዚቃ ሥራ በተጨማሪም ሐመልማል በንግድ ዘርፍ በግንባታ ስራ እንዲሁም አመል ካፌ ተሞክሮ እንዳላት የሕይወት ታሪኳ ያስረዳል::
እርሳኝ (፲፱፻፺ ዓ.ም.)
ስደት (2001 እ.ኤ.አ.)
ጊዜ ሚዛን (፲፱፻፺፰ ዓ.ም.)
ያደላል (2013 እ.ኤ.አ.)
የሚሉት የሙዚቃ አልበሞቿም ከ9 አልበምቿ መካከል መካከል ይጠቀሳሉ::
ስደት (2001 እ.ኤ.አ.)
ጊዜ ሚዛን (፲፱፻፺፰ ዓ.ም.)
ያደላል (2013 እ.ኤ.አ.)
የሚሉት የሙዚቃ አልበሞቿም ከ9 አልበምቿ መካከል መካከል ይጠቀሳሉ::
በአዲስ አድማስ ጋዜጣ በአንድ ወቅት “ሀመልማል ትዳር ትፈራለች እንዴ?” ለሚል ለቀረበላት ጥያቄ
ምን ያስፈራል? እግዚአብሔር ላለለት ሠው በጣም ይመከራል፡፡ ከመጣ ደግሞ ሠርግ መደገስ ይቻላል፡፡ ልጆቼም አንዳንዴ ያሾፉብኛል፤ “እኛ ሚዜ እንሆናለን፤ አንቺ ደግሺ፤ ግን ባል የለም” ይሉኛል፡፡ አሁንም ከመጣ እሰየው ነው፡፡ ያለችው ሃመልማል የጎሳዬ ተስፋዬና የሙሉቀን መለሰ ሙዚቃዎች አድናቂ መሆኗን ትናገራለች::
ምን ያስፈራል? እግዚአብሔር ላለለት ሠው በጣም ይመከራል፡፡ ከመጣ ደግሞ ሠርግ መደገስ ይቻላል፡፡ ልጆቼም አንዳንዴ ያሾፉብኛል፤ “እኛ ሚዜ እንሆናለን፤ አንቺ ደግሺ፤ ግን ባል የለም” ይሉኛል፡፡ አሁንም ከመጣ እሰየው ነው፡፡ ያለችው ሃመልማል የጎሳዬ ተስፋዬና የሙሉቀን መለሰ ሙዚቃዎች አድናቂ መሆኗን ትናገራለች::
በትርፍ ጊዜሽ ምን ትሰርያለሽ? በሚል ለቀረበላት ጥያቄም:
የቤት ስራ ያስደስተኛል፤ አበስላለሁ። አትክልቶችን እንከባከባለሁ፡፡ የሁለት ልጆች እናት ነኝ፡፡ ትልቋ ልጄ ማክዳ ትባላለች። ከአሜሪካ፣ ፖኖን ዩኒቨርስቲ ተመረቃለች፡፡ አሜሪካን አገር ጐበዝ ተማሪዎችን ለማበረታታት የምርቃት ሰርተፍኬታቸውን ፕሬዚዳንቱ ናቸው የሚሰጡት – በኋይት ሀውስ፡፡ የእኔም ልጅ ከክሊንተን፣ ከቡሽ እና ከኦባማ እጅ ወስዳለች። ይሔ ደስ ይላል፡፡ ” ብላለች::

No comments:
Post a Comment