Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, December 6, 2017

Earphone use, የጆሮ ማዳመጫን ምን ያህል መጠቀም አለብን?

በሀገራችን ከሞባይል አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚከሰቱ የጤና እክሎች፣ ጆሮ ማዳመጫን በተከታታይ መጠቀም ላለመስማት ችግር እንደሚያጋልጥ ሐኪሞች እየተናገሩ ነው፡፡ ዘጋቢያችን የጤና ባለሙያዎችን እንዳነጋገረው ከሆነ የጆሮ ማዳመጫን /ኤርፎን/ አዘውትረው የሚጠቀሙ ወጣቶች ከፍ ካለ ድምፅ በቀር ለመስማት መቸገራቸውን ነው፡፡
እንደ ወጣቶቹ ከሆነ ጆሮ ማዳመጫ የተጣራ ሙዚቃን ለመስማት እንደሚያግዝ የተናገሩ ሲሆን አንዳንዶቹም ሙድ ነው የሚሉ ናቸው፡፡ ይሁንና ጆሮ ማዳመጫንና ለሌሎች ከፍተኛ ድምፅ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖች፣ በዘላቂው ለአለመስማት ችግር ተጋላጭ እንደሆኑ ነው የሐኪሞቹ አስተያየት የሚናገረው፡፡
ጆሯችን ድምፅን ለማስተላለፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርግልን የሰውነታችን አካል ነው፡፡ ይህን ተግባር የሚፈፅመው ጆሮ በሶስት ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡ ውጫዊው፣ መካከለኛውና ውስጣዊው የጆሮ ክፍል በመባል ይታወቃል፡፡
በጣም ወሳኝ ከሆኑት መካከል በመካከለኛ ክፍል የሚገኙት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ መካከለኛው የጆሮ ታምቡር /ስስ ሥጋ የሚመስልና ለመስማት አገልግሎት የሚውል ነው/ በአየር የተሞሉ ክፍሎች፣ ሶስት ትናንሽ አጥንቶች ማለትም ‹‹malleus incus and stapes›› የተባሉ ለመስማት የቀጫጭን ፀጉሮች፣ ጆሮን ከአፍንጫ ጋር የሚያገናኝ ክፍት ቱቦ (Eustachian tube) አየርን የሚመጥንና ፈሳሽን ከጆሮ ውስጥ የሚያስወግድ፣ ሁለት ትናንሽ ጡንቻዎች፣ አንደኛው ከጆሮ ታምቡር ጋር የተያያዘ ሌላኛው ከውስጣቸው የጆሮ ክፍል ጋ የተያያዘ ጡንቻ ናቸው፡፡ ኃይለኛ ድምፅ በሚኖረበት ጊዜ ይህ ጡንቻ ይኮማተርና ብዙ ድምፅ ወደ ውስጣዊው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ በማድረግ ጆሮን ከአደጋ ይከላከላል፡፡
የመስማት ችግሮች ሁኔታ
ውስጣዊው የጆሮ ክፍል ሁለት ዓይነት ሥራ ይሰራል፡፡  የመስማት ስራን ለማከናወንና የሰውነት ሚዛንን ለመጠበቅ፡፡ ለመስማት አገልግሎት የሚውለው የዚህ ጆሮ ክፍል ልክ እንደ ቀንድ አውጣ ያለ ጥምዝ ቅርፅ ያለውና ‹‹ኮክሊያ›› በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ጠቃሚና በውስጡም በፈሳሽ የተሞላ ነው፡፡ ኮክሊያ በግድግዳው ላይ የተለዩ ሴሎችን ማለትም እንደ ፀጉር ያሉና ለመስማታችን ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸውን ክፍሎች ይዟል፡፡ እነዚህ ሴሎ በተደጋጋሚ ወይም በከፍተኛ የድምፅ ኃይል ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ አንዴ ከተጎዱ በኋላ እንደገና ለመብቀል አይቻላቸውም፡፡ በዚህም ችግሩ ዘላቂ ይሆናል፡፡
ተደጋጋሚ ያለቅጥ የተጨመረ ድምፅ እነዚህን ሴሎች ቀስ እያለ ይጎዳቸዋል ይገላቸዋልም፡፡ በስተመጨረሻም ድምፅን ለመስማት መቸገርና መደንቆርን ያስከትላል፡፡ አንዳንዴም ይህንን ተከትሎ በጆሮ ውስጥ የሚሰማ የመጮህ ነገር የማይቋረጥ ድምፅ ይኖራል፡፡
ስለዚህ ከባድ ድምፅ ወይም ተደጋጋሚ ከፍተኛ ድምፅ ለድንቁርና ያጋልጣል፡፡ በዚህ ምክንያት ከ85db በላይ የሆኑ የድምፅ ሞገዶች፣ ለከባድ የመኪና ድምፅ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ መጋለጥ፣ ለድሪል ድምፆች በቀን ከ8 ሰዓት በላይ መጋለጥ፣ ለድሪል ድምፆች በቀን ከ2 ሰዓት በላይ መጋለጥ፣ ከፍተኛ ድምፅ ላለው የኮንሰርት ሙዚቃ፣ ለመኪና ጥሩንባ ድምፅ በቀን ከ15 ደቂቃ በላይ መጋለጥ፣ ለመሳሪያ/ሽጉጥ ድምፅ ለአጭር ጊዜም ቢሆን መጋለጥ ከላይ ለተጠቀሰውና ለጆሮ አለመስማት ችግር ይጋለጣሉ፡፡
ማንኛውም ሰው ምንም እንኳን ለከፍተኛ የድምፅ ሞገድ የተለያዩ አባባል ወይም ስሜት ቢኖረውም ለጆሮ አለመስማት ችግር በሂደት የመጋለጥ ዕድሉ አለው፡፡ ከፍተኛ የድምፅ ሞገድነትና ለዚህ ሞገድ የመጋለጥ/በጊዜ አንፃር ለችግሩ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የመስማት ችግር የሚገጥማቸው ሞገዱ ከፍተኛ ሲሆን ነው፡፡ እንዲሁም በተገላቢጦሽ፣ ይህ ከፍተኛ የድምፅ ሞገድ በአጭር ጊዜ ቆይታ የመስማት ችግር ሲያመጣ፣ ወይም ለአጭር ጊዜ/ከጊዜ በኋላ የሚተው፣ አለበለዚያ ደግሞ በቋሚ የመስማት ችግር አስከትሎ ሊያልፍ ይችላል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በሰውየው ጆሮ የሚጮህ ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ወይም በንግግር ተደማምጦ የመግባባት ችግር ይኖራል፡፡ ታዲያ ማንኛውም ሰው ይህንን ክስተት ተረድቶ ምክንያቱን ማስወገድ ችግሩ እንዳይባባስ ይጠቅማል፡፡
ከፍተኛ የድምፅ ሞገድ ከሚያመጣው የጆሮ አለመስማት ችግር ለመከላከል፡-
– የዚህን ከፍተኛ የድምፅ ሞገድ ምንጭ መረዳት ላይ እንደተጠቀሰው፡- ከዛም ቀጥሎ ለዚህ የድምፅ ሞገድ ብዙ ጊዜ ላለመጋለጥ መሞከር፡- ወይም ሙዚቃን ዝቅ ባለ ድምፅ ብቻ ለማዳመጥ መሞከር፡፡
– የዚህን የድምፅ ሞድ መቀነስ ከተቻለ በማስወገድ መጠንቀቅ፡፡ ከተቻለ ለዚህ ድምፅ በጭራሽ አለመጋለጥ፡፡ ካልተቻለ ግን ሰዓት ወስኖ መሞከርን የመሳሰሉት ዘዴዎች የጆሮ ሴሎችን ጉት በመቀነስ ችግሩ እንዳይባባስ ያደርጋል፡፡ ታዲያ በተደጋጋሚ ለከፍተኛ የድምፅ ሞገድ መጋለጥ፣ ለዚህ የጆሮ የመስማት አቅም ማነስ መጋለጥ እንደሚከተል ልናውቅ ይገባል፡፡ የበለጠ ማጣት ያለብን ነገር ግን ከአንገት በላይ ሐኪም በተከታታይ መታየትን እንዳለብንና ምክንያቱን በደንብ ማወቅ መቻላችን ለሚመጣው ክትትልም ጠቃሚ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡
ድምፅ የጆሮ ማዳመጫዎች ባሻገር ዳግም ሌሎች ከፍተኛ የድምፅ ሞገድ ላላቸው ነገሮችም አለመጋለጥ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ በተደጋጋሚ ከፍተኛ ወይም ከባድ መኪና ድምፅ፣ ለመኪና ጥሩንባ፣ ለድሪል ድምፅ፣ በዲጄነት ለረዥም ሰዓት መስራት፣ በጆሮ ማዳመጫ (Earphone) ለረዥም ጊዜ መጠቀም እንደውም በቅርቡ የወጣ አንድ ዘገባ፣ በተከታታይ ለ5 ዓመት በተከታታይ የጆሮ ማዳመጫ የሚጠቀሙ፣ ጆሮዋቸው ከመስማት ውጪ በመሆን ለጉዳት እንደሚጋለጥ ተነግሯል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials