Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 16, 2017

በኦሮሚያ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሔደ





በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ በዛሬው ዕለት የተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ በጨለንቆ ንጹኃን ዜጎች መገደላቸውን የሚያወግዝ ሆኖ ተስተውሏል በርካታ ህዝብ በተገኘበት በዚህ ተቃውሞ ላይ፣ ተማሪዎች በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ አውግዘዋል በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችም መጽናናትን በመመኘት፣ ግድያውን የፈጸመውን የህወሓት አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውመዋል በነቀምቴ፣ ከተማሪዎች በተጨማሪም የአካባቢው ማኅበረሰብም አደባባይ በመውጣት፣ የጨለንቆን ግድያ እና ገዳዮችን በጽኑ አውግዟል ምንም ባላደረጉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው አስከፊ ግድያ እንዳሳዘናቸው የገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በህወሓት አገዛዝ መተዳደር እንደማይፈልጉም ተናግረዋል በተመሳሳይ ሁኔታም በምዕራብ ወለጋ ማንዲ ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ የተካሔደ ሲሆን፣ የሰልፉ ዓላማም በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ ማውገዝ ነበር የአካባቢው ህዝብ በጨለንቆ ግድያ ላይ የተሳተፉ ወታደሮች እና ትዕዛዙን ያስተላለፉት አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠይቀዋል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በደሌ ከተማ ውስጥም የህወሓትን አገዛዝ የሚያወግዝ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል የሰልፉ ተካፋይ የሆነው ማኅበረሰብ፣ እንደ ሌሎቹ ከተሞች ሁሉ በጨለንቆ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ፣ የህወሓት አገዛዝ ስልጣን እንዲለቅቅ ጠይቋል መረጃዎች እንደጠቆሙት በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ጠንከር ያሉ እና አገዛዙ በአስቸኳይ ስልጣን እንዲለቅ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ይገኛሉ በጨለንቆ ሜታ ወረዳ ውስጥ አንድ ሰው በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል መገደሉ፣ የአካባቢው ህዝብ ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጣ አስገድዶት ነበር በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች የተፈጸመው ግድያ ያስቆጣው የጨለንቆ ህዝብ፣ በስፍራው በሚገኘው እና ህወሓት በሚያዘው መከላከያ ሰራዊት አማካይነት ተኩስ ተከፍቶበት አስራ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል::

BBN NEWS

No comments:

Post a Comment

wanted officials