አርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ!
.
እጅግ በጣም ተወዳጁ የአገር ባለውለታ ታማኝ በየነ
ወደ እናት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ከረጅም ዓመት ቆይታ በኋላ ነሐሴ 26 ቀን 2010 ዓ.ም ይገባል ። ታማኝ በየነ "አንድ ሕዝብ ፣አንድ ኢትዮጵያ " በማለት ባለፉቱ 28 ዓመታት ብሔር ፣ ሐይማኖት ፣ቋንቋ እና ቦታ ሣይገድበው ስለ-ኢትዮጵያዊያን እና ስለ-ሚወዳት እናት ሃገሩ ኢትዮጵያ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል
ሙሉ ጊዜውን የሰጠ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው። ስለ-ታማኝ ይህ ከላይ የተገለጸው መልካም ተግባር ከውቅያኖስ በማንኪያ እንደመጨለፍ የሚቆጠር እንጂ የእርሱን በጎ ተግባር ሙሉ በሙሉ የሚገልጽ አይደለም ። ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ የአርቲስት፣ አክቲቪስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ወደ እናት ሃገሩ ሲገባ የሚደረገለት አቀባበል በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል
ለረጅም ዓመታት አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መቻቻልን እና መተሳሰብን ሲሰብክ የኖረ፣ አንድ ህዝብ አንዲት ኢትዮጵያ የሚል አቋም ያለዉ እና ብሔር ሃይማኖት ሳይለይ ለኢትዮጵያ ህዝብ የታገለ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ለመቀበል ፤ 1ኛ. ረ/ፕ ነብዩ ባዬ፣ 2ኛ. ሀብታሙብ አዱኛ ፣3ኛ. አርቲስት ዳዊት ይፍሩ ፣ 4ኛ. አቶ ይልማ ይፍሩ ፣ 5ኛ. አርቲስትና ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን ፣ 6ኛ. አቶ የሺዋስ አስፋ ፣ 7ኛ. ኮሜዲያን ደረጃ ሀይሌ ፣ 8ኛ. ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ ፣ 9ኛ. አቶ ይድነቃቸው ከበደ ፣ 10ኛ. አቶ ፋአድ ሰማን ፣ 11ኛ. አርቲስት አብርሃም ወልዴ ፣ 12ኛ. ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ የአቀባበሉ ዐብይ የኮሚቴ አባላት መካከል ሲሆኑ፤ ሌሎችም ንዑስ ኮሚቴ አባላት በታላቁ ሰው የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ስራዎችን የሚያከናውኑ የኮሚቴ አባላት ተዋቅረው ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። የአርቲስት ፣ የአክቲቪስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የታማኝ በየነን አቀባበል ለማስተባበር በዋነኛነት ይህ ከላይ የተገለጸው ኮሚቴ ነሐሴ 26 እና 27 በሚከናወነው መርሐ ግብር ላይ በዋነኛነት ስራውን ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው።
.
(ይድነቃቸው ከበደ)