Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, August 20, 2018

ኢሳት ዜና : ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ


ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስልጣን ከተነሱ አሜሪካ የኢኮኖሚ አደጋ ያጋጥማታል አሉ
 ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እርሳቸውን ከስልጣን ለማንሳት ሙከራ የሚደረግ ከሆነ የአገሪቱ ኢኮኖሚ አደጋ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። ፕሬዚዳንቱ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ለሁለት ሴቶች ገንዘብ መክፈላቸውንም የቀድሞው ጠበቃቸውና ጉዳይ አስፈጻሚያቸው ሚካኤል ኮኸን ካጋለጡ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ በጠበቃቸው አማካኝነት የከፈሉት ገንዘብ ከሁለቱ ሴቶች ጋር ከፈጸሙት ወሲብ ጋር የሚገናኝ ሲሆን፣ ይህ ይፋ እንዳይሆንባቸውም የአፍ ማዘጊያ ገንዘብ እንዲከፈል ማዘዛቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።
ከፍተኛ የህግ ፈተና የገጠማቸው ፕሬዚዳንቱ ፣ ከስልጣን እንዲወርዱ ግፊት እየመጣባቸው ሲሆን፣ እርሳቸው ግን ከስልጣን የሚወርዱ ከሆነ በአገሪቱ ላይ ከፍተና የኢኮኖሚ ቀውስ እንዲመከሰት በማስጠንቀቅ ስልጣናቸውን ለማቆየት እየታገሉ ነው።
ዋነኛ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው የሆኑት የዲሞክራቲክ ፓርቲክ ፓርቲ ፖለቲከኞች ከመጪው ህዳር ወር አጋማሽ ምርጫ ወዲህ ፣ ፕሬዚዳንቱን የመክሰስ ፍላጎት እንደሌላቸው እየተዘገበ ነው። ፕሬዚዳንት ትራምም ብቸኛ ተስፋቸው የፓርልማና የህግ መወሰኛ ምክር ቤቶችን ተቆጣጥረው የያዙት የረብሊካኖች ሲሆኑ፣ እነዚህን ሁለት የስልጣን ቦታዎች በዲሞክራቶች ላለመነጠቅ ከፍተኛ ቀስቀሳ እያደረጉ ነው።
ከምርጫው ማግስት ዲሞክራቶች በሁለቱም የምክር ቤት ወንበሮች አብላጫ ድምጽ የሚያገኙ ከሆነ፣ ትራምፕን ከስልጣን ለማንሳት ከፍተኛ እድል ይኖራል። ከፍተኛ የሪፐብሊካን ድጋፍ ያላቸው ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ማውረድ ቀላል እንደማይሆን ብዙዎች ይስማማሉ።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በምርጫው ወቅት ከሩስያ ጋር በማበር ተፎካካሪያቸው ሄላሪ ክሊንተን እንዲሸነፉ አድርገዋል በሚል የተጀመረው ምርመራ እስካሁን አልተጠናቀቀም። በዚህ የምርመራ ውጤት ፕሬዚዳንቱ ጥፋተኛ ከሆኑ፣ የራሳቸው ፓርቲ አባላት ሳይቀሩ ድጋፋቸውን ሊነሱዋቸው የሚችሉበት አጋጣሚ ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ይገመታል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials