ስለ አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ፅኑወች አርበኛ ታጋዩች የመጀመሪያ ዙር ወደ ሀገር ቤት አገባብ እና አቀባበል ሁኔታ በቅንጭቡ ፦
፩ኛ. ከኤርትራ የተለያዩ ካምፕች ከ300 በላይ ታጋይ አርበኞች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ።
፪ኛ. በአማራ ክልል በ3 የማሰልጠኛ ጣቢያወች የሰለጠኑ ፣ እንዲሁም ንቅናቄው በጎበዝ አለቆች አደራጂቶ አስፈላጊውን የትጥቅ፣ የስንቅ አቅርቦት እያሟላ በተለያዩ አካባቢወች የህወሓትን ቡድን መፈናፈኛ አሳጥተው የነበሩ ከ5ሺ በላይ አርበኛ ታጋዩች ከነሙሉ ትጥቃቸው ይቀላቀላሉ።
፫ኛ. ሁለት ከተሞች ጎንደር እና ባህርዳር የአቀባበል መረሀ ግብሮች ተዘጋጂተዋል በጊዜያዊነት ከክልሉ የለውጥ ሃይል ጋር በመወያየት በተዘጋጀ ስፍራ ይሰፍራሉ። ዘላቂው ካምፕ ሙሉ በሙሉ እስኪዘጋጂ ድረስ።
፬ኛ. ሲገቡ በፀረ ለውጥ ሀይሉ የደህንነት ስጋት እንዳይፈጠር ከሀገር መከላከያ እና ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።
፭ኛ. የአግ7 አርበኛ ታጋዩች ትጥቃቸውን አይፈቱም፤ ከነሙሉ ትጥቃቸው ይገባሉ። ከገቡም በኃላ የእራሳቸው ህጋዊ ሰርተፍኬት ይሰጣቸዋል።ከካምፕ ውጭ ወደ ቤተሰብ ቢያቀኑ እንኳ ትጥቃቸውን ይዘው መሄድ ይችላሉ።
፮ኛ. በነፃነት ትግሉ በእስር ፣ በአካል መጉደል ፣ በቤተሰብ መበተን ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ለተጋለጡ አርበኛ ታጋዩች የንቅናቄው አባላት ለአመታት የሚቆይ በሚፈልጉት የሙያ መስክ ብቁ የሚያደርግ እና የሚያቋቁም ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ ወደ ስራ ተግብቷል።
፯ኛ. በመላ ሀገሪቱ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ አባሎቹ ወደ ካምፕ የሚገቡ ከ6 በላይ ካምፕች ቦታ መረጣና ወታደራዊ ጥናት እየተካሄደባቸው ይገኛል።4ቱ ወይም 5ቱ በአማራ ክልል ይሆናሉ።
በፅኑ ኢትዮጵያዊነት ከህብረ ብሄራዊው የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይል ጋር ወደ ፊት !!
ኢትዮጵያን እና ህዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ ይቀድስም!!
ኢትዮጵያን እና ህዝቧን እግዚአብሔር ይባርክ ይቀድስም!!
No comments:
Post a Comment