Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 1, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ • ጀዋር ሙሀመድና ታማኝ በየነም በቅርቡ ወደ አገራቸው ገብተው በድልድይ ግንባታ ውስጥ እንደሚሳተፉ አረጋግጠውልኛል፡፡


•የማንፈልገውና የእኛ ያልሆነ አንድም ዜጋ የለም
• ግንቡ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ፈርሷል፣ ፍርስራሹን የመጠራረግ ስራ በሚኒሶታ እውን ሆኗል፡፡
• አቡነ መርቆሪዮስ ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ ሲገቡ የመጀመሪያውን የግንባታ ጡብ አስቀምጠዋል፡፡
• በአሜሪካ የሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውንና ወገናቸውን ናፍቀዋል፡፡የተሳካለቸው በአዲስ አመት እንዲመጡ ጋብዣቸዋለሁ፡፡
• ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ገንዘባቸውን ሳይሆን ፍቅርና እንክብካቤ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች አንድነት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ደስታ ነው፡፡
• የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ እህት ቤተክርስቲያን ጋር በቅርቡ እንደምትደመር እንጠብቃለን፡፡
• ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት አገራቸው ገብተው ለማገልገል አረጋግጠውልናል፡፡
• ጀዋር ሙሀመድና ታማኝ በየነም በቅርቡ ወደ አገራቸው ገብተው በድልድይ ግንባታ ውስጥ እንደሚሳተፉ አረጋግጠውልኛል፡፡
• በዘርና በሀይማኖት ሳንከፋፈል ኢትዮጵያዊ ወገንተኝነትን በማሳየት ወደ እኛ የሚመጡ ወገኖቻችንን ልንቀበል ይገባል፡፡
• አንዱ ብሄር ሌላውን ብሄር፣ አንዱ ሀይማኖት ሌላውን ሀይማኖት ሳያጠቃ በአንድነት ወደፊት መገስገስ ይጠበቅብናል፡፡
• በአሜሪካ ለተደረገልን መስተንግዶ ለዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ክብር አቀርባለሁ፡፡
Image may contain: 1 personImage may contain: one or more people, people standing and suit

No comments:

Post a Comment

wanted officials