15 አባላት ያሉት የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ምክር ቤት መቋቋሙ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ይፋ ሆኗል።
ምክር ቤቱ በታዋቂው ምሁር ዶክተር አለማየሁ ገብረማርያም ሊቀመንበርነት የሚመራ ይሆናል።
በምክር ቤቱ ውስጥ ከታዋቂ ዲያስፖራ አባላት መካከል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ 1 የአሜሪካ ዶላር በመለገስ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበር።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማቀናጀትና የልገሳውን ገንዘብ ለማሰባሰብ፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሂሳብ መከፈቱም ከዚህ ቀደም ተገልጿል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድን የሚያማክር ምክር ቤት ማቋቋማቸውን ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሰረት 15 አባላት ያሉት የዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ምክር ቤት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ይፋ ሆኗል።
ምክር ቤቱ በታዋቂው ምሁር ዶክተር አለማየሁ ገብረማርያም ሊቀመንበርነት ይመራል።
በምክር ቤቱ ውስጥ ከታዋቂ ዲያስፖራ አባላት መካከል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እና አቶ ኦባንግ ሜቶ ይገኙበታል።
ታማኝ በየነ የጥቅላይ ሚንስትሩን ሀሳብ በመደገፍ ዲያስፖራው በቀን እንድ ዶላር ብቻ ሳይሆን 10 ዶላር እንዲያዋጣ የበኩሌን አደርጋለሁ ማለቱ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment