Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 17, 2018

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ያለው የዘር መድልኦ ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ፡

Bildergebnis für ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ ያለው የዘር መድልኦ ይበልጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተነገረ፡፡
 በቅርቡ የኢሳት ቴሌቪዥን “በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ አመራሮች ዘንድ የሚሰራውን የተጠናከረ የሙስና አሰራር አጋልጠዋል” በማለት የተጠረጠሩ የሌላ ብሄር ተወላጅ የድርጅቱን ሰራተኞች ከኃላፊነት በማውረድ አሰራሩን ሚስጥራዊ ለማድረግ ይበልጥ እየሰራ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል፡፡
የኢሳት ቴሌቪዥን ዜና ከተሰማ በኋላ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የሚገኙት የፋብሪካው ከፍተኛ አመራሮች ፤ በተለይ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞችን በማንሳት እና ከአመራሩ ጥቅማ ጥቅም የሚያገኙ “ጥቅም አደር” ሰራተኞችን በመተካት የቆዬ የዝርፊያ ተግባራቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ሁኔታዎችን እያመቻቹ ነው ተብሏል፡፡
የህወሃት መራሹ የቅዱስ ጊዎርጊስ ቢራ ፋብሪካ ስራ አመራር ቡድን ‘ሊቃወሙንና መረጃ በማቀበል የዘረፋ አሰራራችንን ሊያጋልጡ ይችላሉ’ ብለው ያሰቧቸውን በአመራር ላይ የሚገኙትን ታታሪ ሠራተኞችን በማንሳታቸውም- ሰራተኛው ቅሬታ እያሰማ መሆኑን የውስጥ አዋቂዎች በተለይ ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
በፕሮሞተር ክፍል በዋና አስተባባሪነት ስራ ላይ ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩ በሠራተኛው የሚታወቁ ሶስት የስራ ኃላፊዎችን ከደረጃ ዝቅ ያደረገው የፋብሪካው የህውሃት ቡድን ፤ ሰራተኞችን ከነበሩበት ቦታ በማንሳቱ ሂደት ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የታዘዙት በምስራቅ አፍሪካ የቢጂአይና ካስቴል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱራፌል አለነ ናቸው፡፡
ከአሁን በፊት በፋብሪካው ሰራተኞች ላይ የወሰዱት የማሰርና የማንገላታት አሰራርን ለመከተል የወቅቱ ሁኔታው ያልፈቀደላቸው የፋብሪካው አመራሮች፤ በተቀናጀ መልኩ ምርመራና ክትትል በማድረግ ሚስጢር የሚሾልክበትን ቀዳዳ ለመዝጋት እየሰሩ ነው፡፡ ከአመራር ቦታቸው በግፍ እንደተፈናቀሉ የተነገረላቸው ሶስቱ ሠራተኞች- አቶ መቆያ አለምነው፣አቶ ቴዎድሮስ አላምረውና አቶ ፍቅረ ዮሃንስ እንደሆኑ የውስጥ መረጃ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
አቶ ሱራፌል እርምጃዎችን እንዲወስዱ የተሳሳተ መረጃ በመስጠትና ጥቆማ በማቅረብ በሰራተኞች ላይ ማፈናቀል እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት ሰራተኞች፣ በዚህ ስራ ላይ በፊታውራሪነት የሚሳተፉት አቶ ቴዎድሮስ፣አቶ ኢሳያስና አቶ ፍትሃንግሰት የተባሉት ቀደም ብለው በዝሪፊያው ተግባር የተሰማሩ አመራሮች መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡
የፋብሪካው አመራሮች ለመንግስት መክፈል የሚገባውን ገንዘብ ላለመክፈል ያልተገባ ወጭ በማውጣት እንደሚሰሩ የሚናገሩት የፋብሪካው ሰራተኞች ፤በግቢው ውስጥ ተለያዩ አላስፈላጊ ግንባታዎችን በማካሄድና በየሳምንቱ የማፍረስ – መገንባት ስራ በማከናወን የሃገሪቱ መንግስት ተገቢውን ግብር እንዳያገኝ በመስራት ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡
በረጅም ጊዜ የከተሞች ዕቅድ ፋብሪካዎችን ከማዕከላዊ የከተማ ክፍል ማውጣት ቢሆንም የፋብሪካው አመራሮች ግን አሁንም ታላላቅ ግንባታዎች በማካሄድ በሰበብ ከፍተኛ ምዝበራ እያካሄዱ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ፋብሪካው ከተለያዩ የህወሃት አስመጭዎች መኪኖችን በከፍተኛ ዋጋ በመግዛት የእርስ በርስ የጥቅም ትስስሩን እንዳጠናከረ የሚናገሩት ሰራተኞች ፤ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላጠናቀቁ መኪኖችንም የአመራሩ ወዳጅ ቤተሰቦች በወደቀ ዋጋ በመግዛት ህጋዊነትን ያልተከተለ የጨረታ ሂደት በማከናወን እርስ በርስ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር እንደሚከተሉ ተናረዋል፡፡
አብዛኛው የፋብሪካው ሠራተኛ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የኑሮ ሁኔታ ላይ ቢገኙም ፤ ወደ አመራሩ የቀረቡ ሆድ አደር ሰራተኞችና የህወሃት አባላት ብቻ ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት በፋብሪካው ለረጅም ዓመታት የሰሩ ሃቀኛ ሰራተኞች፤ “አጠቃላይ አሰራሩ ልብን የሚቆስል ነው” በማለት ይናገራሉ፡፡
የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የዶክተር አብይ አመራሮች፣ በፋብሪካው ውስጥ የሚካሄደውን ገደብ ያጣ ምዝበራ በመከታተል ሁሉም ዜጋ እንደስራው መጠን ማግኘት የሚችልበትን አሰራር እንዲዘረጉ እኚሁ ሰራተኞች በድጋሜ ጠይቀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials