Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 24, 2018

ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።


ሶማሊ ላንድ ሲያመልጡ የነበሩ ሁለት የ ኢትዮጵያ ባልስልጣናትን ይዛ አሰረች።
 ሀልቤግ የተሰኘው የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ የሶማሊላንድ የደህንነት ባለስልጣናት ሀርጌሳ ውሰጥ ነው ሁለት የአብዲ ኢሌይ የካቢኔ አባላትን ይዘው ያሰሩት።
የታሰሩት ባለስልጣናት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የነበሩት ኢብራሂም አድም ማሃድ እና የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አብዲልማጅድ አህመድ ጃማ ናቸው።
ባለስልጣናቱ የተያዙት፤የክልሉ ርእስ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌይ ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ከጅጅጋ ሲያመልጡ ነው። ሹመኞቹ ከጅግጅጋ ውድ ሶማሊ ላንድ መዲና ወደ ሀርጌሳ በማቅናት ላለፈው ሳምንት እዚያው መቆየታቸው ታወቆአል።
የሶማሊላንድ የኢሚግሬሽንና የደህንነት ዲፓርትመንት ሀላፊ ታይፕ ኦስማን ለሀልቤግ የዜና አገልግሎት ሲናገሩ ባለስልጣናቱ በኢልጋ አውሮፕላን ማረፊያ በህገ ወጥ መንገድ በመግባታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
የባለስልጣናቱ አላማ ወደ ሞቃዲሾ ለመሄድ እንደነበር የጠቀሱት ሚሰተር ኦስማን፤ ሆኖም ሁለቱም ምንም አይነት ህጋዊ የጉዞ ሰነድ እንደሌላቸው አመልክተዋል።No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment

wanted officials