የሶማሌ ልዩ ኃይል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በፈጸሙት ጥቃት የተገደሉ ዜጎች ቁጥር 42 ደረሰ።ለተፈጸሙ ወንጀሎች የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ ናቸው ተባሉ !!
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 06 ቀን 2010 ዓ/ም )
የአብዲ ኢሌ ደጋፊ እንደሆኑ የሚታመኑ የሶማሌ ልዩ ኃይል ትናንትከቀትር በኋላ ነው ወባሳለፍነው ሳምንትደ ምስራቅ ሀረርጌ ዞን በመዝለቅ ድንገተኛ ጥቃት የፈጸሙት።
የኦጋዴ ብሄራዊ ነጻነት ግንቦር (ኦብነግ) ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ ደርሶ የተኩስ አቁም ባወጀበት በትናንትናው ዕለት የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊሶች በፈጸሙት በዚህ ጥቃት- የኦሮሚያ ፖሊሶችን ጨምሮ 42 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለው ወደ ህክምና ተቋማት መወሰዳቸው ተነግሯል።
ከሳምንት በፊት ከህግ በላይ ሆነው የቆዩትን የቀድሞውን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌይን በህግ ጥላ ስር ለማዋል እርምጃ ሲወሰድ ፣ የአቶ አብዲ ደጋፊ የሆኑ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ከ40 በላይ ሰዎች መግደላቸውና ከአስር በላይ አብያተ ክርስቲያናት ማቃጠላቸው ይታወቃል።
የአካባቢው ግጭትና ውጥረት በአንጻራዊ መልኩ እየተረጋጋ እንደመጣ እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የትናንቱ አስከፊ ጥቃት መፈጸሙ፣ መንግስት የአካባቢውን ሰላም በአስተማማኝ በኩል ለማረጋገጥ ሰፊና ተከታታይ ሥራዎችን መሥራት እንዳለበት የሚያመላክት ነው ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) በትናንትናው ዕለት በአቶ አብዲ ኢሌይ ምትክ አቶ አህመድ ሽዴንየፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጧል።
የመንግስት ቃል አቀባይ ሆነው እየሰሩ ያሉት አቶ አህመድ ሸዴ ለሚቀጥሉት ጊዜያት ሶህዴፓን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ ከመመረጣቸው ጋር ተያይዞ አሁን በያዙት የቃል አቀባይነት ሥራቸው ይቀጥሉ፣ አይቀጥሉ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
በሌላ በኩል ከትናንት ጀምሮ የተኩስ አቁም ማድረጉን እና በሰላማዊ ትግል ለመሳተፍ ዝግጁ መኾኑን ያሳወቀው የኦብነግ አመራሮች ፣ ዕለቱኑ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኦብነግ መሪዎች አዲስ አበባ ሲገቡ የመንግሥት ኮሚኒኬሽንስ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እና ሌሎች ባለሥልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተጨማሪም በጂጂጋ ከተማ አንጻራዊ ሰላም የሰፈነ ሲሆን ከዝርፊያ የተረፉት ሱቆች እየተከፈቱ ነው። የብሄራዊ የመረጃና ደኅንነት ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ሃሰን ኢብራሂም በክልሉ ለተፈጸመው ወንጀል የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ መሆናቸውን ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment