** ስለ አክሱም ዝም አንልም!!(ክፍል 2)**
*** አክሱም ከቫቲካንና ከመካ ጋር እንጂ ከዱባይ ጋር አትነጻጸርም***
*** Axum and Islam***
መ/ር ታሪኩ አበራ
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን። ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓቢይ ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ በተደጋጋሚ ከሙስሊም ወገኖቻችን እየተነሳ ያለው ጥያቄ በአክሱም ከተማ ውስጥ መስኪድ እንድንሰራ ይፈቀድልን የሚል ነው።ይህ በሀገር ውስጥ የተነሳው የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አሜሪካን ሕዝብን አንድ ለማድረግ «የመለያየት ግንብ ይፍረስ የፍቅር ድልድይ ይገንባ» የሚል መርህ ቃል አንግበው በተጓበት ጊዜም በዋሽንግተን ዲሲ በተደረገው ሕዝባዊ የፍቅርና የአንድነት ጉባዔ ላይም ከሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄው ቀርቦ ስለነበር ጠቅላይ ሚንስትሩ ለጠያቂው መልስ በሰጡበት ሰዓት «በዱባይ ቸርች አለ፣ በኢየሩሳሌምም መስኪድ አለ ስለዚህም በአክሱም መስኪድ የማይኖርበት ምንም ምክንያት የለም።" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ምናልባት ነገሩን ቀለል አድርጎ በዓለማዊ የፍርድ ሚዛን ለሚመለከተው ሰው እውነትም የመብት ጥያቄ ነውና እያነሱ ያሉት እንዲሰሩ ሊፈቀድላቸው ይገባል የሚል ምላሽ ሊያሰጥ ይችላል።ነገርግን ጉዳዩን በጥልቀት ለተመለከተውና መንፈሳዊ ደኃራውንና የታሪክ መሠረቱን ላጤነው ሰው በሰከነ አዕምሮ እንዲታይና አማራጭ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ በግልጽ ይረዳዋል ።
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ወገኖቼ እንደምታውቁት ሀገራችን ለረጅም ዓመታት ከገባችባት የእርስበርስ መለያየትና በዘር ከሚፈጸም ዘግናኝ ግጭት ተላቃ ሕዝቦቿ በይቅርታ፣በፍቅርና በመተሳሰብ መንፈስ አብረው እንዲደመሩ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሌሊትና ቀን ያለ እረፍት እየደከሙ መሆናቸውን ኅሊናችሁ ያውቃል። የጠቅላይ ሚንስትሩንም ድካም ሁላችን የተረዳነውና ከልባችን የተቀበልነው በመሆኑ ሀገራችን ከወደቀችበት አሳፋሪ የኋላ ቀርነትና የድህነት ታሪክ ወጥታ ዓለም ከደረሰበት የሥልጣኔ ማማ ላይ እንድትወጣ ሁሉም በፍቅር እየተረባረበ ይገኛል። ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ሁሉ ወደ ኋላ እየጣልን አንድ በሚያደርገን ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሙሉ ጊዜና ኃይላችንን እያፈሰስን ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ፣መልካም አስተዳደር፣ፍትህና ነጻነት እንዲመጣ ሁላችንም በየአቅጣጫው በሙሉ ኃይል ልንረባረብም ይገባል።
ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! እናንተም እንደምትረዱት፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በድህነታችን ምክንያት በየሀገሩ እየተሰደድን የዓለም መሳለቂያ ሆነናል። ብዙ እህቶቻችን የአረብ መጫወቻ ሆነው ሙሉ አካላቸውን ይዘው ወጥተው አካላ ጎደሎ ሆነው ለከባድ በሽታ ተጋልጠው እየተመለሱ ነው።አንዳንዶችም በአሰሪዎቻቸው ከፎቅ እየተወረወሩና በየጓደው ታንቀው እየተገደሉ አስከሬናቸው በየጊዜው እየተላከልን ነው። ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንም ድህነትና የመልካም አስተዳደር እጦት ከሀገር እያሳዳዳቸው የበረሃ አውሬ መጫወቻ ሆነዋል።አብዛኞቹንም የባህር አውሬ እየበላቸው ተስፋቸው ጨልሞ ወጥተው እንደቀሩ ሁላችን እናውቃለን።በለስ ቀንቷቸው አውሮፓና አሜሪካ የሚገቡትም ቢሆኑ ዘመናዊ ባሪያ ሆነው ክብርና ኢትዮጵያዊ ስብዕናቸውን አዋርደው የዕለት ኑሮን ለማሸነፍ በብዙ ድካምና ውጣውረድ ሕይወትን እየታገሉ ይገኛሉ።
ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! አሁን የሁላችን ትኩረትና ኃይል መሆን ያለበት ከዚህ አስከፊና አዋራጅ የድህነት ታሪክ ተላቀን ሀገራችን በኢኮነሚ የምትበለጽግበትን፣ ሕዝባችን የድህነትን ድሪቶ አሽቀንጥሮ ጥሎ እንደሌላው ዓለም ብልጽግናን የሚጎናጸፍበትን፣ ኢትዮጵያ በሳይንሳና ቴክኖሎጂ፣በቢዝነስ፣በልዩ ምጣኔ ሐብት ከራሷ አልፋ ለሌላው መትረፍ የምትችልበትን ታሪክ ለመሥራት ነው እጅ ለእጅ ተያይዘን መረባረብ ያለብን።
ለግጭት የሚዳርግ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ሁሉ የዕድገት ፀር ነው። ከመፈቃቀር ይልቅ መቃቃርን ያመጣል፣ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን ያስፋል፣በጋራ ከመስራት ይልቅ በጋራ መጥፋትን ያፋጥናል፤ሃይማኖታዊ ጉዳይ ሰደድ እሳት ነው፤ ውስጥ ለውስጥ እየተቀጣጠለ ሀገር ያጠፋል፣የፍቅርን ድልድይ ያፈራርሳል፣በወንድማማችነት ሥነ ልቡና ላይ የጠላትነትን ጥዝጣዜ ይጨምራል ።ስለዚህም እባካችሁ ሙስሊም ወገኖቼ በመብት ጥያቄ ስም የፍቅር ጉዟችንን የሚጎትትና እድገታችንን እንደ ካሮት ቁልቁል የሚሰድ ነገር ከመፈጸም እንከልከል።
አክሱም ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደገለጸው ከዱባይ ጋር የምትነጻጸር ከተማ አይደለችም።ዱባይ እንደከተማ ከቆመች ገና 70 ዓመት ያልሞላት ምድረ በዳ የነበርች ከነዳጅ ግኝት በኋላ የቢዝነስ ከተማ ሆና የገነንች አረባዊ የዓለማችን ክፍል ነች እንጂ የሃይማኖት መዲና አይደለችም። አክሱም የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ ያላት የሃይማኖት መዲና ነች። ጥንት መስዋዕተ ኦሪት እየተሰዋ እግዚአብሔር ይመለክባት የነበረች፣ በኋላም ክርስትና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰበከባት፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ጥምቀትን ከእስራኤል ይዞ መጥቶ በኢትዮጵያ ያስፋፋባት፣ታላቁ የወንጌል መምህር የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ፍሬምናጦስ ወይም አባ ሰላም ከሳቴ ብርሃን የክርስትናን ሥርዓት ያጸናባትና ያስፋፋባት፣ነገሥታቱ አብርሃ እና አጽብሃ ክርስትናን ብሔራዊ ሃይማኖት አድርገው ያወጁባትና ሕግ የደነገጉባት፣ተሳቱ ቅዱሳን/ዘጠኙ ቅዱሳን አበው/ ከተለያዩ ሀገራት መጥተው ወንጌልን ያስፋፉባት የሰበኩባት ፣ ታላቁ አባት ቅዱስ ያሬድ ዜማን ከአርያም ተቀብሎ ያዜመባት፣ ያስተማረባት፣ በክህነት ያገለገለባት፤ ሌሎችም በርካታ ቅዱሳን አበው ታላቅ ገድል የፈጸሙባት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ቅድስት ሀገር ነች።
ከአክሱም ጋር በሃይማኖት መዲናነት የሚነጻጸሩት የሮማዋ ቫቲካን፣የእስራኤሏ ኢየሩሳሌምና የአረቧ መካ ነች።
በቫቲካን የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስ አጽም ስላረፈ በዛ ቦታ ላይ ታላቅ ካቴድራል ታንጾ ከተማዋ የካቶሊካውያን ታላቅ የሃይማኖት መዲና ሆና በሺ የሚቆጠሩ ዘመናትን አሳልፋ እስካሁን ድረስ በክብር አለች።ማንኛውም ቫቲካናዊ እስልምናን የመቀበል ተፈጥሯዊ መብት አለው ቫቲካን ውስጥ ግን መስኪድ ይሰራልኝ ማለት አይችልም።መካ የነብዩ ሙሐመድ የትውልድ ቦታና ሙስሊሞች ቅዱሱ ድንጋይ የሚሉት ካባ ያለበት የሃይማኖት መዲና ነች። ማንኛውም የመካ ከተማ ነዋሪ ክርስትናን የመቀበል ተፈጥሯዊ መብት አለው፤ መካ ውስጥ ግን ቤተክርስቲያን ይሰራልኝ ማለት አይችልም ። የአክሱም ከተማ ከላይ የጠቀስኩት የክርስትና ፈርጥ ታሪክ የተፈጸመባት፣ጽላተ ሙሴ በክብር የተቀመጠባት የኦርቶዶክሳውያን ታላቅ የሃይማኖት መዲና ነች።ማንኛውም አክሱማዊ እስልምናን የመቀበል ተፈጥሯዊ መብት አለው አክሱም ውስጥ ግን መስኪድ ይሰራልኝ ማለት አይችልም። ኢይሩሳሌም ክርስቶስ ድንቅ መለኮታዊ ሥራውን የሰራባት፣ የተሰቀለባት፣በቅዱስ ደሙ የኃጢአትን ሥርየት የሰጠባት፣ ትንሳኤና ዕርገቱን የገለጠባት ቅድስት ከተማ ነች፤ ነገርግን በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት የማያምኑት ፍልስጤሞች መስኪድ ሰርተው እኛም የማምለክ መብተን አለን በማለታቸው ምድሪቱ በየቀኑ የሰው ደም እየፈሰሰባት ለዘመናት አኬልዳማ ሆና ቀርታለች።
በኢየሩሳሌም መስኪድ መሰራቱ በወቅቱ የሙስሊሞችን የመብት ጥያቄን ለመመልስ በሚል የመፍትኄ ሐሳብ ሆኖ በመቅረቡ የተፈጸመ ውሳኔ ቢሆንም ለልጅ ልጆቻቸው ግን የደም እዳ ነው ያተረፈባቸው።ዛሬ በአክሱም የክርስትና መዲና ላይ መስኪድ ቢተከል በቀጣይ ትውልድ ላይ የማይቆም የደም እዳ ነው ተክለን የምናልፈው።አክሱም ላይ የሚነሳ እሳት ደግሞ ቤንሻንጉል ላይ አይቆምም ።አክሱም የመላው ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ቅርስና ሐብት ነች።
የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ለእናንተ ልዩ ፍቅርና አክብሮት አለን፣ለዘመናት ተዋደንና ተቻችለን ክፉና ደግ ዘመን አሳልፍን እስከዛሬ ኖረናል ወደፊትም አብረን እንኖራለን።በተለያዩ ከተሞች ቤተክርስቲያንና መስኪድ ጎን ለጎን እየተሰሩ በፍቅር ብዙ ዘመን ተሻግረናል።አክሱም ላይ መስኪድ አትስሩ የምንላችሁ እናንተን ጠልተናችሁ ሳይሆን አክሱም ለእኛ ልዩ የሃይማኖት መዲናችን ልክ እንደ መካ ስለሆነች ነው፣መካ ላይ ቤተክርስቲያን መስራት የማይቻለው እናንተ እኛን ስለጠላችሁን ሳይሆን ሃይማኖታዊ መዲናችሁ ስለሆነች ነው።ደግሞም ታሪክ አትርሱ ኢትዮጵያዊው ንጉሥ አርማህ አረቦቹ አል-ነጃሺ እያሉ የሚጠሩት ደጉ ንጉሣችን፤ የመጀመሪያዎቹን የነቢዩ ሙሐመድ ተከታዮች ሴት ልጁን ራቂያንና ባልዋ ሁስማንን ጨምሮ በመጀመሪያው ሂጅራ በ606 ዓ.ም በስደት ሲመጡ በክብር ሲቀበላቸው እምነታቸውን አክብሮ የማምለኪያ ስፍራ እንዲኖራቸው ከአክሱም ከተማ ውጪ በአሁን ሰዓት ምሥራቃዊ ዞን በሚባለው ነጋሽ በተባለው ሥፍራ ማምለኪያ መስኪዳቸውን እንዲሰሩ ስለፈቀደላቸው ዛሬም ድረስ መስኪድና መካነ መቃብር በዚያ አለ።ታዲያ ዛሬ ላይ ደርሶ ከአንድ ሺ አራት መቶ አምስት ዓመታት በኋላ ታሪክ ማበላሸት ምን ይባላል? እኛ አክብረን ፍቅር እንዳሳየናችሁ እናንተም ፍቅርና አክብሮትን አሳዩን።በእኛ በኢትዮጵያውያን የሚያምረው የቀድሞ ፍቅርና መከባበራችን ነው እንጂ ዘመን ያመጣው ጽንፈኝነት አይደለም።
አንዳንዶች ውሃ የማያነስ ሐሳብ ይዘው ጉንጭ አልፋ ክርክር ሲከራከሩ እንሰማቸዋለን።አክሱም ውስጥ ቡና ቤቶች ሲከፈቱ ዝምብላችሁ መስኪድ ይተከል ስንል ለምን ትቃወማላችሁ? በማለት ቤተክርስቲያንን ለመንቀፍ ሲሞክሩ እንሰማለን ።ሲጀመር በከተማው ውስጥ የንግድ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች የእምነት ተቋማት አይደሉም።ሲቀጥል እነዚህ ድርጅቶች በቤተክርስቲያን ትህዛዝ የተከፈቱ አይደሉም።ሰዎች ኑሮን ለማሸነፍ ተገደው ከሚገቡባቸው አላስፈላጊ ሕይወቶች እንዲወጡ ደግሞ ቤተክርስቲያን በምክርና በትምህርት በየጊዜው የሚጠበቅባትን መልህክት እያስተላለፈች ነው።ይልቅ ትኩረታችንን ሀገራችንን ወደ ማልማትና ወደ ማበልጸግ ብናስብና አክሱም ላይ የብዙ እህቶቻችንን ሕይወት ሊለውጥ የሚችል የልማት ተቋም ብንተክል በሰውም በፈጣሪም ፊት ዋጋችን ታላቅ ነው።
የተከበራችሁ ሙስሊም ወገኖቼ ! በፍቅር እለምናችዋለሁ እንደ ጥንቱ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሁኑ፣የወሃቢያ ድብቅ ሴራ ማስፈጸሚያ አትሁኑ፣ወሃቢያን ከ ሀ-ፐ ማንነቱን ጠንቅቀን እናውቃለን፣በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ድብቅ ዓላማና ስትራቴጂ የትድረስ እንደሆነም በመረጃ ጠንቅቀን እናውቃለን።«ድምጻችን ይሰማ» እያላችሁ የታሰሩ እንዲፈቱ ስትደክሙም ከጎናችሁ የቆምነው ኢትዮጵያዊ ፍቅር አስገድዶን እንጂ ድብቅ ሸፍጥ ከጀርባቸው ያለባቸው ሰዎች መኖራቸው ሳይገባን ቀርቶን እንዳይመስላችሁ።ይልቁን ግን እባካችሁ በፍቅር ተሳስረን፣በይቅርታ ተደምረን ኢትዮጵያችንን በክብር፣በብልጽግና እናንሳት
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቸዋን ይባርክ ።
እባካችሁ ይህንን መልህክት ለሰው ሁሉ ሼር አድርጉት ።
Axum and Islam
The Kingdom of Aksum has a longstanding relationship with Islam. According to ibn Hisham,[8] when Muhammad faced oppression from the Quraysh clan, he sent a small group that included his daughter Ruqayya and her husband Uthman to Axum. Sahama, the Aksumite king,[9] gave them refuge and protection. He refused the requests of the Quraish clan to send these refugees back to Arabia. These refugees did not return until the sixth Hijri year (628), and even then many remained in Ethiopia, eventually settling at Negash in what is now the Misraqawi Zone.
There are different traditions concerning the effect these early Muslims had on the ruler of Axum. On the other hand, Arabic historians and Ethiopian tradition state that some of the Muslim refugees who lived in Ethiopia during this time converted to Orthodox Christianity. There is also a second Ethiopian tradition that, on the death of Ashama ibn Abjar, Muhammed is reported to have prayed for the king's soul, and told his followers, "Leave the Abyssinians in peace, as long as they do not take the offensive.
SHARE SHARE SHARE
No comments:
Post a Comment