Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 7, 2017

Aopstle john Chi in Ethiopia አነጋጋሪው ሐዋርያው ጆን ቻይ አዲስ አበባ ገብቶ አነጋጋሪ ሆኖ ተመለሰ



(ዘ-ሐበሻ) በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከፌዴራል ፖሊሶች ግልምጫና አፈሳ እንዲሁም እየተባባሰ ከመጣው የኑሮ ውድነት በተጨማሪ መነጋግሪያ የሆነው የሐዋርያው ጆን ቻይ አዲስ አበባ መግባትና በከተማዋ ውስጥ ባዘጋጀው ትልቅ ኮንፈረንስ ላይም የተለያዩ ፈውሶችን ሰጠው ማለቱ ነው:: ካሜሮናዊው ጆን ቻይ አዲስ አበባ አየር ማረፊያ ሲገባ የኢትዮጵያን እና የካሜሮንን ባንዲራ በያዙ ወገኖች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለት ነበር:: ማምሻውንም በሞተር ሳይክሎችና በብዙ መኪኖች ታጅቦ በሊሞንዚን የአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎችን እንደጉድ ሲዞራቸው ነበር::
ጆን ቻይ ፈውስ ሰጠው ካለው በተጨማሪ አነጋጋሪ የሆነው ጉዳይ እርሱ ፈውስ ሰጠው ያለበት ቦታ ላይ በዝማሬ ሲያገለግሉ የነበሩት ወገኖች ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪዎች አለባበስና ዝማሬን የተከተለና የያዙትም ከበሮ, መቋሚያና ጽናጽል የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የተመሳሰለ መሆኑም ጭምር ነው:: በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በአዲስ አበባ የታደሙበትን አነጋጋሪ ኮንፈረንስ ከነ አቀባበሉ ለግንዛቤ ይረዳችሁ ዘንድ በተንቀሳቃሽ ምስል አስደግፈን ይዘንላችኋል:: አይታችሁ አስተያየታችሁን ስጡ::
  

No comments:

Post a Comment

wanted officials