Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, February 5, 2017

በጎንደር እስቴ ወያኔዎች የሚሰበሰቡበት ታረቀኝ መታሰቢያ ሆቴል በከፊል በእሳት ወደመ| | በሰሜን በምዕራብ በለሳ የወያኔ ጦር ተቀጥቶ ተመለሰ




ሙሉነህ ዮሃንስ
የተቃጠለው ቤት ወያኔወች የሚመገቡበት ታረቀኝ መታሰቢያ ሆቴል ሲሆን የሆቴሉ ስቶር እና የሆቴሉ1/3ኛው የወደመ መሆኑ ተረጋግጧል። በተኩስ ልውውጡ ወቅት ከወገን በኩል ምንም ጉዳት አልደረሰም። በመጨረሻም የመንገድ ስራ መኪኖች ስለነበሩ እና ህዝቡም እየተጠጋ እና እየጨመረ በመምጣቱ ንፁሀን እንዳይሞቱ ለማፈግፈግ ተገደዋል። እስቴ፣ አንዳቤት፣ ወለሽ፣ ምክሬ፣ ጥናፋ፣ ማጎት እና ስማዳ ከባድ ትግል እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል ሲሉ ከቦታው አስታውቀዋል። ገበያ ሁሉ ዝግ ነው።
በሌላ ዜና በሰሜን ጎንደር በምዕራብ በለሳ አርሶ አደሩን ትጥቅ ለማሰፈታት የወያኔ ጦር ከበባ ቢያደርግም ከአካባቢው በተጠራሩት አርሶ አደሮች የአፀፉ እርምጃ ተወሰዶባቸው ብዙ የጠላት ጦር ሙትና ቁሰለኛ ሲሆኑ የቀረው እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ተከዜ ተፋሰስ ላይ ያሉ የወያኔ ተቋማት ተጠቁ:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታላቁ ዋልድባ ገዳም ላይ ወያኔ በድፍረት የጀመረው የስኳር አገዳ ተቋም ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት በመወሰዱ ድርጅቱ ስራውን ማከናወን ከተሳነው ቆይቷል። ይህን ጥቃት የሚፈፅሙት ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ በጣም በፍጥነት የሚወረወሩ እጅግ የሚያስፈራ ግርማ ሞገስ ያላቸው የተደራጁ ሃይሎች ስለመሆናቸው በደስታ የተሞሉ የአካባቢው የአይን እማኞች በአድናቆት ይገልፃሉ።
በዛሬው እለት ደግሞ እጅግ እንግዳ የሆነ ጥቃት ተፈፅሟል። ከርቀት እየተምዘገዘገ የመጣ እረጅም የእሳት አለሎ ወደ ተከዜ ድልድይ አቅጣጫ ይወረወርና ከድልድዩ በቅርብ እርቀት ላይ ያለ ጋራ ላይ ፈንድቶ በአካባቢው ከፍተኛ መናጋት ፈጥሯል። በቦታው የነበሩት ይህ ተምዘግዛጊ ሚሳኤል/RPG ነገር ከየት እንደተተኮሰና ማን እንደተኮሰው ባይታወቅም ለተከዜ ድልድይ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም ብለዋል። ለትግራይ ልዩ አገልግሎት እንዲውል በከፍተኛ ወጭ የተገነባው የተከዜ የሃይል ማመንጫ ግድብም በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials