Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 8, 2017

በሰሜን ጎንደር ወገራና ምዕራብ በለሳ አካባቢዎች ስለነበረው የጦር ዘመቻ

በሰሜን ጎንደር ወገራና ምዕራብ በለሳ አካባቢዎች ስለነበረው የጦር ዘመቻ



ሙሉቀን ተስፋው
ከጥር 27 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር ወገራና ምዕራብ በለሳ አካባቢዎች የወያኔ ጦር እንደተለመደው በገበሬዎች ቤትና ንብረት ላይ ዘምቷል፡፡ አጀማመሩ እንዲህ ነበር፤
የዐማራ የጎበዝ አለቆች በምዕራብ በለሳ ኖራ ጻድቃን በተባለ አካባቢ በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደረሰውን ግፍ እንዴት ማስቆም እንዳለባቸው በመምከር ላይ ነበሩ፡፡ የጎበዝ አለቆቹ አሉበት ወደተባለው ቦታ አንድ ባንዳ መንገድ እየመራ የወያኔ ወታደሮችን ይዞ ሔደ፡፡ የዐማራ ገበሬዎች በወኔና በጀግንነት የመጡትን ወታደሮች አይቀጡ ቅጣት ቀጧቸው፡፡ ባንዳው በሚያውቀው መንገድ ከመገደል እንዳመለጠ ቢነገርም የመጡት የወያኔ ወታደሮች ግን አልተረፉም፡፡
በቀጣዩ ቀን እሁድ ጥር 28 ቀን 2009 ዓ.ም ምሽት ወደ አንድ ሺህ የሚጠጋ ሜካናይዝድ ከባድ መሣሪያን የታጠቀ የወያኔ ጦር በማክሰኝት በኩል መሔዱ የተሰማ ሲሆን በገበሬዎች ማሳ፣ ቤትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ በትክክል መናገር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡
በአካባቢው ከነበሩ የጎበዝ አለቆች ጋር ለመነጋገር ብዙ የጣርን ቢሆንም ማንንም ማግኘት አልቻልንም፡፡ የጎበዝ አለቆችም በተለያዩ ስልኮች መረጃ ለማድረስ ቢጥሩም የተሳካላቸው አልሆነም፡፡ ስለሆነም ከእሁድ ዕለት ጠዋት ጀምሮ የጎበዝ አለቆችን ለማግኘት ብዙ ጥረን አልተሳካልንም፡፡ መረጃው የተሰባሰበው በአቅራቢያው ያሉ የጎበዝ አለቆች ቀድመው በደረሳቸው መረጃ መሠረት ብቻ ነው፡፡ ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት እያደረግን ሲሆን ዝርዝር መረጃዎች እንደደረሱን ወይም እንዳገኘን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials