Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 15, 2017

ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያና ግብጽ አሜሪካ ለሚኖሩ አፍሪካውያን መጤዎች ዋና መነሻ አገራት ናቸው ተባለ






ፒው ሪሰርች ሴንተር (PWE Research Center) የተባለው አሜሪካ የሚገኝ የምርምር ድርጅት እንደገለጠው እኤአ ከ1970 እስከ 2015 የአፍሪካውያን መጤዎች ቁጥር በአሜሪካ በሶስት እጥፍ አድጓዋል። 80,000 የነበረው ዛሬ 2,060,000 ደረሷል። ይህ ፈጣን እድገትም አስገራሚ ሆኗል።

የ ፒው ሪሰርች ማስረጃ የሶስቱን አገራት የመጤዋች ቁጥር አስተዋጽኦ በግልጥ ያመለክታል። ጥናቱ ባብዛኛው የተካሄደው እኤአ በ2015 በመሆኑ ይህ አሃዝ የዛሬውን ሁኔታ ደህና አድርጎ አጠቃሎ የሚያሳይ አይደለም።

በአሜሪካ የአፍሪካውያን መጤዎች ከሌሎች ክፍለ ዓላማት መጤዎች ሲተያይ አነስተኛ ቢሆንም ብዛቱ በአጭር ጊዜ መጨመሩ ተስተውሏል። በ1970 የአፍሪካውያን መጤዎች ክሌሎች ክፍለ ዓለማት መጤዎች ሲተያይ 0.8% የነበረ ሲሆን በ 2015 ግን 4.8% ደርሷል

ፒው ሪሰርች እንደሚያመለክተው ከአሜሪካ ውጭ ውልደታቸው ከሆነው በአሜሪካ ነዋሪዎች አፍሪካውያን የመነሻቸው ዋና አግራት አምስት ናቸው። እንዚህም ናይጄሪያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ጋና እና ኬንያ ናቸው። የሶማልያውያንም ፍልሰት የሚስተዋል ነው።

አትላንቲክ ውⷃኖስን ተሻግሮ ተንሰራፍቶ ከነበረው የባሪያ ንግድ ዘመን ወዲህ ይህን ያህል አፍሪካውን ወደ አሜሪካ ሲመጡ መታየቱ ነው።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያውያን ወደ መካከለኛው ምስራቅና ወደ ተለያዩ የአውሮጳ አገራት በስደት ይወጣሉ። ካለፉት ስርአቶች ሁሉ ዛሬ በህወሃት መራሹ መንግስት ወደ አሜሪካም ወደ ሌሎችሁም አሀጉራት ስደቱ መጨመሩ ለግምት አስቸጋሪ አይሆንም። በቂ የባለሙያ ጥናታዊ ስራ የሚጠይቅና ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ምሁራን ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ባለፉት ስርአቶች ለከፍተኛ ትምህርት ለመንግስት ተልኮ ብቻ መውጣታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያን ወጣቱ ትውልድ የስራና የህይወት እድሉን የሚያሻሽል መሰረታዊ ለውጥ ካልመጣ በስተቀር የስደቱ ሁኔታ ይከፋል እንጂ አይሻልም የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አያሌ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials