Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 7, 2017

የሕወሓት ጦር ጎንደር ኮዛ አባ ላይ የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ነው | ከዘጠኝ የማያንሱ ቤቶችን አውድሟል

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት በጎንደር እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ፍጅት እንደቀጠለበት መሆኑን ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች አመለከቱ:: ትናንት ጥር 29 800 የሚሆን የሕወሓት ጦር ኮዛ አባ ላይ ሕዝቡን በከባድ መሳሪያ ሲደበድብ ማምሸቱ የተዘገበ ሲሆን ዛሬም ጥር 30/2009 ዓ.ም ቀጥሎ መሣሪያ አምጡ በማለት ቤት ለቤት እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተዘግቧል::
የሕወሓት ጦር በሕዝቡ ላይ በከባድ መሣሪያ እየወሰደው ባለው እርምጃ ስንት ሰው እንደሞተ ዘ-ሐበሻ እያጣራች ሲሆን እስካሁን ከ9 የማያንሱ ቤቶች መውደማቸውን ከአካባቢው ከመጡ መረጃዎች ለመረዳት ችላለች::
የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጦር በበለሳና በወገራም እንዲሁ በሕዝቡ ላይ ተኩስ የከፈተ ሲሆን መሣሪያ አስረክቡ በሚል እርምጃዎችን ወስዷል:: ሕዝቡም አልበገር በማለት በሕወሃት ወታደሮች ላይ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑም የደረሰን መረጃ ያመለከታል:

No comments:

Post a Comment

wanted officials